ኹዝ ቢየዲ ያ ረሱለሏህ || በ ፉአድ ሸምሱ አዲስ መንዙማ || Fuad shemsu khuz biyedi ya resullah

Описание к видео ኹዝ ቢየዲ ያ ረሱለሏህ || በ ፉአድ ሸምሱ አዲስ መንዙማ || Fuad shemsu khuz biyedi ya resullah

☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆☆
Like እና Share በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
የYoutube ቻናላችንን Subscribe በማድረግ በየጊዜው የሚለቀቁ Videoዎችን ይመልከቱ ||
   / alfaruqtube  
የፌስቡክ ገፅ ||
  / ​​...​  
ቴሌግራም ||
https://t.me/alfaruqtube
።።።።።።
ያ ሰይዲ  ኹዝ ቢየዲ
።።።።።።
።።።።።።።።

ያሚፍታሃን ሊኩኑዚላህ
ያ ሂጃበን ሊዓዛቢላህ

ያ ከሪመን ሚን ከረሚላህ
አንተል ባቡ ሊዓጧኢላህ
።።
አንተ አንተ ያረሱለሏህ
አንተል መቅሱድ ያሃቢበሏህ
ፈአጊስና ያ ረሱለሏህ
።።።።።።።።።።።።።።።።።

ላመስግንህ ዳኢም ጌታየ ሶመዲ
ፉአዴን ነወርከው በማሂ መንገዲ
አህመድን የኔ አርገህ እኔን የአህመዲ
ላይወልቅ አለበስከኝ የአንዋሩን ለምዲ
 በረክቷል በኛ ላይ የኒዕማህ ዐደዲ
።።።።
  
አደም ከስህተቱ ኑህ ከጡፋን ጉዲ
ኢብራሂም ከእሳቱ ኢስማኢል ከእርዲ
የየዕቁብ ልጅ ጀማል ሚዝማር የዳውዲ
ሲሩ አንቱ ኖት ለካስ የሙርሰሎች ዘውዲ
ቀድ ዛበ ፉአዲ፣  ቀልሚ ወሚዳዲ
።።።።።
  
ከንቅልፍ አለም ርቄ አንቱን ብወዳጂ 
ያጣሁት አንድ የለም ያገኘሁት እንጂ
አዎን ማጣት የለም ወለው እንኳ ላንዲ
አንቱን እያነሳ ላንቱ አድሮ ፉአዲ
 ለቀድ ተሸረፍና ቢኩም ያ ሰይዲ
።።።።።።

።።።።
ሰማሁ ዳና መንደር ያንቱ ስም ሲጠራ
ደርሷል የኔም ተራ ልጥራዎት እንግዲ
።።።።

ቢያድለኝ ነው እኮ ቢመርጠኝ ሶመዲ
   በስምሁ ነግሼ በዚክርሁ ምከብዲ
።።።።።።።

ምን ስሙን ባቆላምጥ ሳባብለው ብኖረው
ላሳምረው ስጥር እኔው ነኝ የማምረው
።።።።
አምረው ሚያሳምሩ ልቀው የሚያልቁ
  ተጠርተው ማይርቁ የጠና ለት ጉዲ
።።።።።።

እሰየሁ ሰይዲ ሞላልኝ የልቤ
መራቄን አራቅኩት ካንቱ ተቃርቤ
አልፈትርም ላፍታ ስምሁን አልለቅም 
እያየሁት አይደል ሲያነግስ ሲጠቅም
ወሏህ እኔ አልርቅም ወዴትም አልሄዲ
።።።።።።

አንቱን ቢያነሳ አይደል ቀለም አንደበቴ
ጣፍጦልኝ የዋለው ዜማ ከሊማቴ
ልጥራዎት ፈንታየ ልጥራዎት ሹመቴ
አንቱንማ ትቼ መች ሊያምር ሃያቴ
ፈመን ሊ ሲዋኩም መን የእኹዝ ቢየዲ   
።።።

የቅጣት ነበልባል ተካምሮ ሲነዲ
ቀልብና አንደበቱ ያለለት አሃዲ
ቢላሉል ሃበሺይ ስምኩን ተሰንቆ
ወይ ፍንክች አላቸው መቀጣቱን ንቆ
የተሰማው ደምቆ ኮቴው ጀነት ኹልዲ
።።።።።።

እንዳልነበር ሎሌ ሰው ሁላ ሚንቀው
ሊያነግሰው ቢከጅል ካንቱ አስተዋወቀው
መቃሙ ሲታደል ያዛን ሹመት ደርሳው
ከፍ ያረገውን ስም ከፍ አድርጎ አነሳው
 ያ ጥቁር አንበሳው አልቃሻው ዛሂዲ
።።።።።።።።

  ትመስክር መዲና ይግራላት ቃላቱ
  በአንዋር የሞላት ማን እንደሁ ምክኒያቱ
  ጦር ሜዳው ሳይሸሽግ ዘመቻው ሳይክዲ
  ይመስክር  ሑነይኑ ኸንደቁም ይፍረዲ
  ጀግና ከሱ ወዲያ አይቶ እንደሆን አንዲ
።።።።።።

 ይናገር ያ ጀበል ይመስክር ኡሁዲ
ታላቅ እንዳላየ እንደ ሙሀመዲ
ይታደለው ልሳን ያውራ ዲንጋ ዛፉ
ምን ተሰማው ነቢ ባጠገቡ ሲያልፉ
ረሂሙ ረኡፉ ኑሩሏሂል ሃዲ

።።።።
በሂሚዩ ሸዕሪ ፣ ዐዚሙል ሃመቲ
ኑኒዩል ሃጂቢ፣ አንዋሪዩ ዛቲ
አሊፊዩል አንፊ፣ ሚሚዩ ሸፈቲ
ረውነቁል አስናኒ፣ ሚዛቡ ረህመቲ
ሸምሲዩል ጀቢኒ፣ በድሪዩል ጀብሃቲ
ሒላሊዩ ጦርፊ፣ ሙሽሪቁል ወጅነቲ
ካሚሉል ፊጥረቲ  ሩሃን ወጀሰዲ
።።።።።።

ያሃቢበሏሂ፣ ያሶፍወተል ዒባድ
  ሁቡኩም ደፊኑን፣ ፊ መይዳኒል ፉአድ
  ወከም ሚን ዊዳዲን፣ ዓሹ ቢሂ ሱዓድ
   ሙሐመዱል ሃዲ ረፊኡ ደረጃት
   ሷሂቡል ዓላማት፣ ወሙስቢ ላሃዟት
ሒላሊዩል ወጅሂ፣ መርዲዩል መቃላት
   መዝሃሩ ኑሪላህ፣ በይነል ሙሻሃዳት
   ወሲሩ ቀለሚ፣ ፊ ጀሚዒል አውቃት
አፍዶሉል መኽሉቃት፣ ሚስሉክ ላ ዩጀዲ
።።።።።።።።
።።።።።።።

እኒያ ያሏህ ሰዎች፣ ዛሬ አንዱ ነገ አንዱ
ደጋጎች  አሪፎች፣ ኸለዊይ ዓቢዱ
ተከታትለው ተራ፣ ባዶ አርገውን ሄዱ
ጨለመብን ወቅቱ፣ ጠፋብን መንገዱ
ሚያጠብቀው አጣናም፣ ላላብን ገመዱ
የቲም መስሎ ኑሮን፣ አቅቶናል መልመዱ
ይያዙን አህመዱ፣ ስንል ኹዝ ቢየዲ
።።።።።
 
ምነው ወቅቱ ከፋ፣ ተሸበረስ ሆዴ
ከደጎች ጋር አብሮ፣ ደግነት ሄደ እንዴ

ወዴት ሄደ ረህመት፣ የት ገባ ትዝዝን
ወንድም ሆኗልሳ፣ ወንድምን ሚያሳዝን

የሸይኾቻችን ሲር ቆሞ እንዳላቆመን
ዛሬስ ዘመም ብሎ እንደ ጤፍ ዘመመን
በኛው ግፊት ወድቋል የኛውማ ዘመን
   ያንቱው እጅ ያክመን ፣ ካሳመመን ጉዲ
።።።።።

ልብስ ብቻ ፀድቶ ልብ እየቆሸሸ
እራቀን መዋደድ፣ ፍቅር ጥሎን ሸሸ
ለኔ ለኔ ስንል በኛ ላይ ቀን መሸ
የደጋጎች መራቅ ስንቱን አበላሸ
የኛው ዘመን ላሸ፣ ድረሱ ሰይዲ
።።።።።።
እንደው ድንገት ደርሶ ሆዴን ሆድ ሲብሰው 
ሰው ጠማኝ ይለኛል ተከብቤም በሰው  
ከቶ ምንድን ነካን ወቅቴን ምን ወረሰው
ያባቶቼን ኪታብ አፈር እስኪያለብሰው
ላንሳው ላባብሰው፣ ይዶላል መንገዲ
   ።።።።።።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке