New Ethiopian Nasheed 2022 | Munshid Tofik Yusuf - Yelebie Tegagn | አዲስ ነሺዳ በሙሺድ ተውፊቅ ዪሱፍ - የልቤ ጠጋኝ

Описание к видео New Ethiopian Nasheed 2022 | Munshid Tofik Yusuf - Yelebie Tegagn | አዲስ ነሺዳ በሙሺድ ተውፊቅ ዪሱፍ - የልቤ ጠጋኝ

New Ethiopian Nasheed 2022 | Munshid Tofik Yusuf - Yelebie Tegagn | አዲስ ነሺዳ በሙሺድ ተውፊቅ ዪሱፍ - የልቤ ጠጋኝ
Like , share, follow
★  / tewfiqyusuf  
★   / tewfiqyusuf  
★  / tewfiqyusu  
★https://t.me/tewfiqyusuf
#ethiopia
#newnasheed
#Nasheed
#ylbetegange

★ የልቤ ጠጋኝ ★
መፍትሄ ባጣ ለፍላጎቴ ግራ እየገባኝ
አቅመቢስነት፣ደካማነቴ አንገት ቢያስደፋኝ
ፀሀይ ጨረቃ ባይደምቁ ለኔ በብርሃናቸው
የተሰበረ ቀልቤን ባይገዙት በውበታቸው
እጄን አልሰጥም ተስፋ ቆርጨ አልሆንም ባካኝ
መች ይረሳኛል ጀባሩ ከላይ የልቤ(ቀልቤ) ጠጋኝ፡፡

አሏሁ አላሁ ያጀባሩ ባንተው ልጠገን ከስብራቴ
አቅሜ ሲደክም ሁነኝ ብርታቴ፡፡

ለጠየቀው ቸር ለምኖ አያፍርም ስሙን ያወሳ
ረዛቅ ነው እሱ እልፍኙ አይጠብም ጓዳው አይሳሳ
ልኑር በስሙ ቀልቤን አጽድቼ ቀን ሳልል ሌሊት
ወንጀሌን አባሽ በተውባ መላሽ ለኔ መዳኒት፡፡

ጉልበቴ ይራድ ላንተ ይገዛ ጅስም ጀሰዴ
ይህ ሁሉ ራህመት ይህ ሁሉ ኒዕማ ባንተ አይደል እንዴ?
ለዱአ አቅርበኝ ቀልቤን አርሳት በዝነት ጠብታ
ቀሪ ዘመኔን በፍቅርህ ልኑር ባንተ ልረታ፡፡

አሏሁ አላሁ ያጀባሩ ባንተው ልጠገን ከስብራቴ
አቅሜ ሲደክም ሁነኝ ብርታቴ፡፡

ፍቅርህን ሽተው ባንተ ጉያውስጥ ለሚመሽጉ
ወሰን የሚባል ድንበር የለውም ውዴታህ ጥጉ፡፡
ለትዕዛዞችህ ደስታየ በዝቶ ሁሌ ላጎንብስ
እርም ካረከው ልቤን ለጉማት እግሬም ይገዘት
እንዳይገሰግስ፡፡

ስራየ ቢያንስም ከብናኝ ክብደት ሚዛን ባይደፋ
ካንተ ደጅ እዝነት ከምህረትህ አልቆርጥም ተስፋ፡፡
ኢባዳው አምሮ ላግራራለት ሰው ውስጡ ለፀዳ
ሱስ ነው ያንተ ስም አይጠገብም በቀልብ ጓዳ፡፡
አሏሁ አላሁ ያጀባሩ ባንተው ልጠገን ከስብራቴ
አቅሜ ሲደክም ሁነኝ ብርታቴ፡፡

ምንዳህ ስፋቱ የእዝነትህ ጥግ ዳር የለው ልኩ
ዱኒያን ያስንቃል በኢስቲቃማ አንተን ማምለኩ፡፡
አልቦዝን ባንተ ሁሌ ላስታውስህ በስምህ ልፍካ
መዳኛየ ነህ ቀልቤ ሲቆሽሽ ልቤ ሲነካ፡፡

በስምህ ልቃኝ ለቀልቤ ዙፋን በጥኡም ዜማ
ብርታቴ ይዛል፣ ላንተ ማነሴ ጥበብ ነው ሂክማ፡፡
በስምህ ልኑር ተቀላቅየ ከሚያውቁህ ተርታ
እጄን ሰጥቼ አንተን አንተን ስል ሳላመነታ:

አሏሁ አላሁ ያጀባሩ ባንተው ልጠገን ከስብራቴ
አቅሜ ሲደክም ሁነኝ ብርታቴ፡፡

Комментарии

Информация по комментариям в разработке