አባ ጽጌ ድንግል ገዳም ዳግም የተቋቋመው ከሰቆጣ 60ኪሎ ሜትር ይገኛል ለበርካታ ዘመናት አስታዋሽ አጥቶና ተረስቶ ሲኖር በብጹዕ በአቡነ ባርናባስ ተቋቁሟል፡፡

Описание к видео አባ ጽጌ ድንግል ገዳም ዳግም የተቋቋመው ከሰቆጣ 60ኪሎ ሜትር ይገኛል ለበርካታ ዘመናት አስታዋሽ አጥቶና ተረስቶ ሲኖር በብጹዕ በአቡነ ባርናባስ ተቋቁሟል፡፡

አባ ጽጌ ድንግል ገዳም Amba Tsigie Silase የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :1000341308201
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ውድ ንቁ የጸሎትና የንስሐ መርከብ ዛሬም በምናብ ወደ ጥንታዊና ታሪካዊ ወደ ሆነው ወደ አባ ጽጌ ድንግል ገዳም ይዟችሁ ሊጓዝ ነው አባ ጽጌ ድንግል ታላቅ አባት ናቸው። የእመቤታችን ይቅድስት ድንድል ማርያም ፈቅሯ በዝቶላቸው በታላቅ ምስጋና ያመሰገኑ ታላቅ አባት ከብዙ ምስጋናዎች ውስጥ ደግሞ በየዓመቱ ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 የሚቆመው ማህሌተ ጽጌ አንዱ ምስጋናዋ ነው፡፡
ታዲያ በእኚህ ታላቅ አባት የተመሰረተው ገዳም ከሰቆጣ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል ለበርካታ ዘመናት አስታዋሽ አጥቶና ተረስቶ ሲኖር በድጋሚ በብጹዕ አባታችን በአቡነ ባርናባስ አማካኝነት በ2011ዓ/ም ተቋቁሟል፡፡
የአባ ጽጌ ድንግል ገዳም እጅግ አስቸጋሪና ገደላ ገደል በሆነ ስፍራ የሚገኝ ሲሆን ገዳሙ በቅርብ በድጋሚ እንደመቋቋሙ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ያሉበት ገዳም ነው በገዳሙ ውስጥ ይህንን ከንቱ ዓለም ጥለው የመነኑ ጥቂት መናንያን የሚገኙ ሲሆን በገዳሙ ጸንተው ለመቆየት በከፍተኛ ተጋድሎ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ምንም እንኳ ይህንን ዓለም ጥለው ቢመንኑም አብዛኛውን ጊዜአቸውን በጾምና በጸሎት ቢያሳለፉም ስጋቸውን ለማቆያ የምትሆን ለብን የሚደግፍ ምግበ ስጋም ያስፈልጋቸዋል ለዚህም ከፍተኛ የውሀ ችግር በገዳሙ ውስጥ ያለ ሲሆን የሚገለገሉበትም ቤተክርስቲያን እጅግ ትንሽ እና ከሁለትና ከሶስት ሰዎች በላይ የማታስገባ ናት፡፡
ገዳማውያኑ ቋሚ ገቢ ለማግኘት የራሳቸውን ጥረት በማድረግ የንብ ማነብ ስራ የጀመሩ ቢሆንም ነገር ግን በብዙ መንገድ መደገፍ ይገባቸዋል፡፡
በመሆኑም እኛ የንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎትና የንስሀ መርከብ አባላት ቦታውን አይተን በረከትም አገኝተን የተመለስን ቢሆንም ቦታው ግን በሚከተሉት ስራዎች ሊደገፍ ይገባዋል እንላለን፡፡
1.ቦታው ላይ አዲስ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ሊሰራ ያስፈልጋል፡፡
2.ከፍተኛ የውሃ ችግር በመኖሩ ይህ የውሃ ችግር ሊቀረፍ ይገባል
3.መነኮሳቱ የጀመሩት የንብ ማነብ ስራ ባህላዊ በመሆኑ ይህንን በዘመናዊ መልክ በመለወጥ ቋሚ ገቢ እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋ፡፡
የተወደዳችሁ በመላ ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳያን በሙሉ እኛ የንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎትና የንስሀ መርከብ አባላት በቦታው ተገኝተን ከማያልቀው በረከት እንድትሳተፉ እነሆ የበረከት መንገድ ብለናል ስለዚህ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጅ የሆናችሁ የአባታችን የአባ ጽጌ ድንግል ፍቅር ያገበራችሁ ሁሉ በጋራ አቤት ብለን ተነስተን ታሪካችንን እናስቀጥል እንላለን፡፡
ዩቱዩብ ቻናሌ ሰብስክራይብ ያድርጉ    / @nikumidea456   የደውል ምልክቱን ይጫኑ፡፡ቪዲዮች በየቀኑ እንለቃለን።
የቴሌግራም ቁጥሬ ይህ ነው join አድርጉ https://t.me/joinchat/ChpwxELgGpE4djF... የንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎት መርከብ
የማህበሩ አባል መሆን ለምትፈልጉ የበረከት ሥራ ለመስራት በዚህ ሊንክ ይግቡ 👉https://chat.whatsapp.com/JJfoncjwiZi...
Follow me on FB የፌስቡክ ግሩፕ ✅https://www.facebook.com/groups/17478...
ንቁ የፀሎት እና የንስሀ መርከብ ማህበር
ለበለጠ መረጃ የማህበሩን አድሚኖች በወትሳብና በኢሞ ብቻ ይደውሉልን አልያም በተቀመጠው የወትሳብ ሊንክ join አድርገው ይግቡና ያግኙን
+49 1521 37 06 500
+2519 44 274 294
+966 5 37 02 86 64
+966 54 007 9927
+49 1766 68 68 741
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፀሎትና የንስሐ መርከብ የዋትሳፕ ማህበር

Комментарии

Информация по комментариям в разработке