🔴አዲስ ዝማሬ"ብርሃናዊው መልአክ" ዘማሪት ሕንጸተ ምንዳ New mezemur zemarit hensete menda @danielniguse

Описание к видео 🔴አዲስ ዝማሬ"ብርሃናዊው መልአክ" ዘማሪት ሕንጸተ ምንዳ New mezemur zemarit hensete menda @danielniguse

🔴አዲስ ዝማሬ"ብርሃናዊው መልአክ" ዘማሪት ሕንጸተ ምንዳ New mezemur zemarit hensete menda @danielniguse

ብርሃናዊው መልአክ ጥበብ ልታጠጣኝ
ከእግዚአብሔር ተልከህ ፈጥነህ ደረስክልኝ
ቅዱስ ዑራኤል ሞገሴ ክብሬ
አለኝ ለክብርህ ቅኔ ዝማሬ/2/

ለእዝራ ሱቱኤል እውቀት ልታድለው
ከዐይን ጥቅሻ ፈጥነህ ከላይ የመጣኸው
በረከትህ ይደር ይፍሰስ በእኔም ላይ
መልአኩ ዑራኤል የአምላክ አገልጋይ

ሀዘኔ ይሸሻል ስምህን ስጠራ
ጠላቴ ይርዳል ስትሆን ከእኔ ጋራ
የቤቴ ድምቀት ነህ የኑሮዬ ዋልታ
አወድስሃለሁ በዜማ በእልልታ

በቤተመቅደስህ አድጌ በደጅህ
እስከ ዛሬ ድረስ አለሁኝ በቅጥርህ
አምላኬን እንዳከብር ጸጋው እንዳይርቀኝ
ቅደም በመንገዴ ጥበቃህ ይጋርደኝ

የከሳሼ ዛቻ እንደጉም ይተናል
ስምህን ስጠራ ጭንቄ ይበተናል
አላፍርም ጠርቼህ ታብሷል እንባዬ
አንተ ነህ ዑራኤል ዋሴ ጠበቃዬ

#viral
#Orthodox mezemur

Комментарии

Информация по комментариям в разработке