ኦሾ ና ከጀርባው ያለው አስደንጋጭ ሚስጥር | ዘጋቢ ፊልም 2023

Описание к видео ኦሾ ና ከጀርባው ያለው አስደንጋጭ ሚስጥር | ዘጋቢ ፊልም 2023

ኦሾና የመርዛማ ትምህርቶቹ አስደንጋጭ ሚስጥሮች
▼ FOLLOW ME ▼
• Instagram :   / henokhirboro  
• Facebook :   / henokhirboro  
• Telegram : https://t.me/henokhirboro
• TikTok :   / henokhirboro  


Undercover Vampire Policeman by Chris Zabriskie is licensed under a Creative Commons Attribution 4.0 license. https://creativecommons.org/licenses/...

መግቢያ

ጾታ፣ ዘር፣ ኃይማኖት ሳይኖር ሰዎች ለስሜታቸውና ለውስጣዊ ሰላማቸው እንጂ ለገንዘብ የማይሠሩበት ቦታ።
ይህ ቦታ ሰዎች ህይወታቸውን ረስተው እንደገና እራሳቸውን ለማግኘት ጉዞ የሚጀምሩበት ስፍራ ነው። ይህን ስፍራ ገነት ከሚለው ቃል በቀር ሌላ ምን ሊገልጸው ይችላል?
እ. ኤ. አ በ 1981
እንደዚህ አይነት ገነት የሆነን ስፍራ ማለትም ከጾታ ዘርና ሃይማኖት የጸዳ ሰዎች ውስጣዊ ሰላማቸውን በመጠበቅ ያለፈ ህይወታቸውን የሚረሱበትና እራሳቸውን ለማግኘት ፍለጋ የሚያደርጉበትን ስፍራ በምድር ለመገንባት የተወሰኑ ሰዎች ጸሃያማ ብለው የሚጠሩትን ልብስ ለብሰው ወደ አሜሪካ ኦሪገን ከተማ ደረሱ።
እነዚህ ሰዎች ዛሬ ኦሾ ተብሎ የሚጠራው የመንፈሳዊ አስተማሪው ብሃግዋን ሽሪ ራጄኒሽ ታማኝ ተከታዮች ነበሩ።
ነገር ግን ከህንድ ወደ አሜሪካ ኦሪገን ከሄዱ በኋላ ሊገነቡት ያሰቡት የምድር ገነት ከተማ ቀስ በቀስ የሲኦል ቅርጽ መያዝ ጀመረ። ኦሪገን ከተማ ከደረሱ ከሶስት አመት በሁላ ማለትም
እ.ኤ.አ. በ1984 በዋስኮ ካውንቲ ውስጥ የተፈፀመ እና በጅምላ

መመረዝ ፣ ልቅ ጋብቻ ፣ማጭበርበር ፣ወሲባዊ ጥቃት እንዲሁም በርካታ የሴራ ንድፈ ሃሳቦች አካል የሆነ የወንጀል ድርጊቶች ተፈጸሙ።
ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ከጾታና ዘር ብሎም ከሃይማኖትም ሆነ ገንዘብ የጸዳ ገነት እንገነባለን ብለው ከሩቅ ምስራቋ ህንድ ተጉዘው አሜሪካን ኦሪገን የከተሙት የብሃግዋን ሽሪ ራጄኒሽ(ኦሾ) ታማኝ ተከታዮች
በመጨረሻ እንዴት ሲኦል ሊገነቡ ቻሉ?
ብሃግዋን ሽሪ ራጄኒሽ ወይም (ኦሾ) ማን ነው?
የኦሾ ማራኪና ተወዳጅ የሚመስሉ ትምርቶች ቀስ በቀስ እንዴት የሲኦል ቅርጽ ያዙ?

ኦሾ ማን ነው?

ማ አናድ ሺላ
የተወለደችው ሺላ አምባላል ፓቴል ህንድ ውስጥ ሲሆን
የኦሾ የቅርብ ሰውና እንደ ቃል አቀባይ ነበረች።
ከሙምባይ ወደ ፑኔ እንዲሁም አሜሪካ ውስጥ እስከምትገኝ
ትንሽ ከተማ ድረስ የኦሾ ደቀ መዝሙር እና ቀይ ለባሽ በመሆን ከፍተኛ ሚና ነበራት።
ኦሾ ማን ነው?
ኦሾ በማድያ ፕራዴሽ ውስጥ ባሬሊ በሚባል ስፍራ በቻንድራ ሞሃን ጄን ተወለደ።
ከልጅነቱ ጀምሮ በጣም ብሩህ እና ጥበበኛ ነበር።
እ.ኤ.አ. ከ1960-1968 በብዙ ተቋማት ውስጥ ፍልስፍናን ያስተምር ነበር።
እናም በሰዎች አኗኗር ፣ባህል እንዲሁም በብዙ ሀይማኖቶች ላይ ጠንካራ አስተያየትና ትችቶችን ይሰነዝር ነበር።
ብዙዎችም በዚህ አስተያየትና ንግግሩ ቢበሳጩም አብዛኞቹ ግን
በንግግሩ ና ትችቱ በሚያነሳቸው አንኳር ሂሶቹ ይገረሙ ነበር።
በዚህ ምክንያት በብዙዎች ዘንድ ተጽዕኖ ማሳደር ቻለ።
ብዙም ሳይቆይ በ1970 የራሱን ተከታዩችና ደቀ መዛሙርት ቡድን አቋቋመ።

ላክስሚ ኩርቫ የኦሾ የመጀምሪያ ተከታይና የግል ፀሃፊው በመሆን ሁሉንም የአስተዳደር ስራዎችን ታከናውን ነበር።
ኩርቫ በህንድ ሙምባይ በነበረችበት ወቅት የ16 ዓመቷ ጓደኛዋ ሺላ ኦሾን ለመገናኘት ከአባቷ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሙምባይ መጥታለች።
ለመጀመሪያ ጊዜ ከኦሾ ጋር በተገኛኙ ጊዜ በትምህርቱ በቀላሉ ተማረከች እንዲህ ስትልም በራሷ ቃል ገልጻ ነበር።
ስለነበረች ራሷን ለእሱ ሰጠች። በእራሷ አንደበትም እንዲህ ብላ ነበር፥- “ ህይወት አሁን ብታቆም እንኳ፣ ምንም እንዳላጣው ይሰማኛል። “
ይህቺህ ሴት 18 አመት ሲሞላት ለከፍተኛ ትምርቷ ወደ አሜሪካ አመራች፣ አሜሪካም እያለች ማርክ ሲልቨርማን
የተባለ አሜሪካዊ ዜጋ አገባች።
ከጋብቻው በኋላ እንደገና ወደ ህንድ ኦሾን
ከባለቤቷ ጋር ተመለሰች።
ሁለቱም የኦሾ ደቀ መዛሙርት ሆኑ።
በኦሾ አስተምህሮ መሰረትም ያለፈውን ህይወታቸውን ትተው መሄዳቸውን እና ከአሁን በኋላ አዲሱን ሕይወታቸውን እንደሚጀምሩ ለማሳየት ስማቸውን ቀየሩ።
እንዲህ እንዲህ እያለ የኦሾ ተጽእኖ በጣም እየጨመረ
ስለነበር ከመላው አለም የመጡ ሰዎች ሞንባይ ድረስ እየመጡ ይጎበኙት ነበር።
ዛሬ ላይ እንኳ በዓመት ከ30,000 በላይ የውጭ አገር ሰዎች ይጎበኙታል።
በመጽሃፎቹንና ንግግሮቹ የተነኩ ብዙዎች ይህን ጉዞ ለማድረግ ቀዳሚዎች ናቸው።
ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ዶክተሮች፣ ጠበቆች፣ የጉዞው አብዛናውን ቁጥር ይይዛሉ።
በጉብኝታቸውም ወቅት ብዙውን ጊዜ፣በማሰላሰልና በተመስጦ አይኖቻቸውን በመጨፈን ይተነፍሳሉ፣
ይህ ብቻ ሳይሆን የኦሾ ተከታዮች ብዙ መዝለል፣ መጮህና መደነዝ እንዳለባቸው ታዘዋል። ለዚህም ምክንያት ኦሾ እንዲህ ኦሾ እንዲህ ይላል “ በሰው ውስጥ ያሉት ሁሉም ድምፆች ሲወጡ፣ ያኔ እውነተኛ ጸጥታና ጥልቅ ስሜቶችን ማዳመጥ እንችላለን።”
ይህ ዓይነቱ ማሰላሰል/meditation ተለዋዋጭ ሜዲቴሽን ይባላል።
ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የኦሾ ዋና የገቢ ምንጭ የሆነው የቴራፒ ክፍለ ጊዜዎች ተጀመሩ።
ከአሜሪካ ከባለቤቷ ጋር ወደ ኦሾ የመጣችው ሺላ
የኦሾ በጣም ታማኝ ከሆኑት ደቀመዛሙርት አንዱ በመሆን
ቀስ በቀስ የኦሾ ማንኛውም ጉዳይ በእርሷ እጅ ላይ ነበር ።

00:00 - መግቢያ
02:20 - ክፍል 1: ኦሾ ማን ነው?
06:36 - ክፍል 2: አስነዋሪ ድርጊቶች
08:30 - ክፍል 3: ከህንድ ወደ አሜሪካ
10:01 - ክፍል 4: ራንቾ ኦሾ ከተማ
12:10 - ክፍል 5: ሰላማዊ አመጸኞች
14:14 - ክፍል 6: ሽብርና ግድያ ሙከራዎች


---------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
#henok_hirboro #inspireEthiopia #EthiopianBookClub #EthioBooks #WaliaBook #EthiopianMotivational #HowToMotivate #howtobehappyinlife #ethiopia #ethopian #ebs#kanatv
inspire ethiopia, enspire ethiopia, inspire ethiopia new video, manyazewal, manyazewal ehetu, dallol einterteinment, android app development, Amazon, Amazon USA, amazon, how to, ethiopian motivation, ethiopian motivational speech, donkey tub, seifu on ebs, ale tube, ስነወርቅ Dertogada, ራማቶሐራ, Ethiopian Novel, Arts
Tv World, ተስፋሁን ከበደ, ፍራሽ አዳሽ, ethiopian audiobook, TEDEL TUBE, Mehreteab Asefa / ምህረተአብ አሰፋ, Netsebraq TV, GETSI 21 Entertainment, Yeneta Media News, Zehabesha Original, Yeneta Tube የኔታ ቲዩብ, Feta Daily, Nahom Records Inc, Seifu ON EBS, Hope Music Ethiopia, የብራና ገፅ / Page of Birana, Donkey Tube, Fana Television, EBS TV WorldWide, Abel Birhanu, ትረካ, sheger shelf, tereka, ሙሉ ትረካ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке