እንዴት እንጸልይ?

Описание к видео እንዴት እንጸልይ?

መጽሐፍ ቅዱስ ይልቁንም አዲስ ኪዳን ጸሎትን በተመለከተ ግልጽና የማያሻማ ንድፍ አስቀምጦልናል። ጸሎት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ አብ እንጸልያለን። ይህ እውነት ግራጫ በሌለው መንገድ ጥቁርና ነጭ ሆኖ ተቀምጧል። በመንፈስ ቅዱስ ሃይል መጸለያችን የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት አጉልቶ ያሳያል እንጂ እያሳንሰውም። በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መጸለያችን የኢየሱስን አምላክነት ያጎላል እንጂ አያሳንሰውም። ወደ አብ በመጸለያችን አብን ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ መንገድ መለኮት አያደርገውም። በቅድስት ሥላሴ አብም፣ ኢየሱስ ክርስቶስም መንፈስ ቅዱስም አንዱን መለኮት የሚካፈሉ ሦስት አካላት ናቸው። የአብ የሆነ ሁሉ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ነው። የወልድ የሆነ ሁሉ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ነው። የመንፈስ ቅዱስ የሆነ ሁሉ የአብና የወልድ ነው።
እዚህ ጋ መጠየቅና መመለስ ያለበት አንድ ጉዳይ አለ። ምንም እንኳ በአዲስ ኪዳን በግልጽ የተቀመጠ ሥርዓት ሆኖ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ አብ ብንጸልይም። ወደ ወልድ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ወይም ወደ መንፈስ ቅዱስ አንጸልይም ማለት አይደለም። ሁለቱም አካላት ሁሉን የሚያውቁ፣ ሁሉን የሚችሉና በሁሉ ሥፍራ የሚገኙ ናቸውና። ስለዚህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር እንነጋገራለን። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንነጋገራለን። ምንም እንኳ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንደምንጸልይ በቀጥታ የሚነግሩን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ባይኖሩም ለዘለዓለም ከእኛ ጋር ሊኖር የመጣ፣ በእኛም ዘንድ የሚኖሮ ጴራቅሊጦስ (ጠበቃ፣ አጽናኝ) ነውና ማንኛውም በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ አማኝ ሳያነጋግረው ሊውል ሊያድር የሚችልበት ሁኔታ አይኖርም።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке