የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ | የማቴዎስ ወንጌል (ክፍል 1) | ፓስተር አስፋው በቀለ

Описание к видео የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ | የማቴዎስ ወንጌል (ክፍል 1) | ፓስተር አስፋው በቀለ

ስለ ኢየሱስ ሕይወትና አገልግሎት የሚናገረውን አስደሳች መልዕክት የጻፈው ማቴዎስ ነው። ማቴዎስ የኢየሱስ ክርስቶስ የቅርብ ወዳጅ ሲሆን በአንድ ወቅት ቀረጥ ሰብሳቢ ነበር። በመጀመሪያ በዕብራይስጥ የተጻፈውና በኋላም ወደ ግሪክኛ የተተረጎመው የማቴዎስ ወንጌል ተጽፎ ያለቀው በ41 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ነው። ይህ መጽሐፍ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን ከግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ጋር በማገናኘት ረገድ እንደ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።

ማቴዎስ በዋነኝነት ያተኮረው በእግዚአብሔር መንግሥትና በኢየሱስ ትምህርቶች ላይ ነበር፤ ይህ ደግሞ የጊዜ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ እንዳይጽፍ አድርጎታል። ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ የተራራውን ስብከት የሰጠው ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነባቸው ዓመታት አጋማሽ ላይ ቢሆንም ይህ ስብከት በመጽሐፉ ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው መጀመሪያ አካባቢ ነው።

ኢየሱስ በገሊላ ባገለገለበት ወቅት ብዙ ተአምራትን ፈጽሟል፤ ለ12ቱ ሐዋርያት አገልግሎትን የሚመለከቱ መመሪያዎችን ሰጥቷል፣ ፈሪሳውያንን አውግዟል እንዲሁም ስለ መንግሥቱ የሚገልጹ የተለያዩ ምሳሌዎችን ተናግሯል። ከዚያ ከገሊላ ተነስቶ “ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደ።” (ማቴ. 19:1) በመንገድ ላይ ሳለ ኢየሱስ ‘ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፣ በዚያም የሰው ልጅ ሞት ይፈረድበታል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሣል’ በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ነገራቸው።—ማቴ. 20:18, 19

ለሌላ ተጨማሪ ትምህርቶች፦

https: //www.operationezra.com
   • www.operationezra.com ምቅላት የመማጸኛ ከተማ ...  
   • www.operationezra.com ምቅላት የመማጸኛ ከተማ ...  

© Operation Ezra Bible College

Комментарии

Информация по комментариям в разработке