የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል መዝሙሮች ስብስብ || የገና መዝሙር || Gena mezmur collection

Описание к видео የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል መዝሙሮች ስብስብ || የገና መዝሙር || Gena mezmur collection

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ!!!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ወዳጆች
ሁላችሁም፡፡
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ፡፡ ልሁል እግዚአብሔር እነሆ ፈጣሪያችን ፍጹም አምላክ
ስሆን በፍጥረቱ የማይጨክን ርኅሩኅ የባሕርይ አምላክ እንደመኾኁ መጠን ሊያድንነን ስለፈቀደ
ፍጹም ሰው ሆኖ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዷልና ዛሬ የልደቱን በዓል ለምናከብርባት ዕለት
እንኳን አደረባችሁ፡፡ ወሰን የሌለውን ቸርነቱንና ምሕረቱን እያሰብን፣ እግዚአብሔር አምላካችንን
በፍቅር፣ በሰላምና በአንድነት ሆነን እያመሰገንን መንፈሳዊውን ደስታችንን በማብሠር ነው፡፡
ሱባኤ ተቆጥሮ፣ ትንቢት ተነግሮ ካለ በኋላ ማለትም ቅዲሳን ነቢያት ይመጣል፣ ከቅድስት
ድንግል ማርያም ይወለዳል ብለው ተናግረው ከጨረሱ በኋላ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል
ሊቀ መላእክት ቅድስት ድንግል ማርያምን አምላክ ከአንቺ ይወለዳል ብሎ አበሠራትና ጊዜው
ሲደርስ ማለትም 5500 ዘመን ሲፈጸም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተልሔም
በተባለው ቦታ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ ኲነኔ፣ ፍዳ፣ መርገም፣ ኀዘን፣ ኃጢአት
ሁሉ ተደመሰሰ፡፡
አንድነት፣ ስምምነት፣ ርኅራኄ፣ ሰላምና ፍቅር ሰፈነ፡፡ ዕልል በሉ ይህን ያደረገላችሁን
ፈጣሪያችሁን እግዚአብሔርን አመስግኑ በማለት አሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ትላችኋለች
እናታችሁ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፡፡
ጥያቄ:-
ልደት ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ:-
ልደት ብዙ ምሥጢር ይለበት ሲሆን ቀጥተኛ ትርጉሙ ከማኅፀን መወለድ ከጨለማ ወደ ብርሃን
መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢራዊ ትርጉሙም፣ ካለመኖር ወደ መኖር መምጣት፣ መኖር፣
መፀነስ፣ መወለድ፣ ከእናት ኾድ ወደ ብርሃን መውጣት፣ መገኘት፣ ተገልጾ መታየት ነው፡፡
ጥያቄ
የጌታችን ልደት ከሌላው በምን ይለያል?
መልስ
ሰው ሁሉ በአባትና በእናት መካከል በሚፈጸመው ሩካቤ ሥጋ፣ (በሥጋ ግንኙነት) በዘርዓ ብእሲ
ወብእሲት /በወንድና በሴት ዘር/ ምክንያት ተጸንሶ የሚወለድ ሲሆን ጌታችን ግን ይለአባት፣
/ያለወንድ/ ያለ ዘርዐ ብእሲ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡
እንደዚሁም ሌሎች ሰዎች ልጅን ከወለዱ በኋላ ድንግልናቸው እንደማይኖር የታወቀ ስሆን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ግን አምላክን ከመጽነስዋ በፊት፣ አምላክን በምትወልድበት
ጊዜም ሆነ አምላክን ከወለደች በኋላም ሁሉ ጊዜ ድንግል፣ ንጽሕት፣ ቅድስት ናት፡፡ ስለዚህም
የጌታችን ልደትና የእናቱ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልና፣ ንጽሕና እና ቅድስና ከሌሎች
ሁሉ የተለየ ነው ማለት ነው፡፡
ጥያቄ:-
የመልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክትና የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ
ሁናቴ እንዴት ነበር?
መልስ:-
ወበሳድስ መርኀ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር ኀበ ድንግል ሉቃ.1÷26፡፡
መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር አገልጋይ የኾነውን ካህነ ኦሪት ዘካርያስን
እግዚአብሔርን ወደሚያገለግልበት ቤተ መቅደስ ኼዶ ዘካርያስ ሆይ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት
ደርሷልና አትፍራ መካን የምትባለው ኤልሳቤጥ ሚስትህም ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች ስሙንም
ዩሐንስ ትለዋለህ ይኸውም ፍጹም ደስታ ማለት ነው ብሎ ካበሠረው በኋላ በ6ኛ ወሩ ናዝሬት
ገሊላ ወደነበረችው ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ተላከ፡፡ ኼዶም እግዚአብሔር
ከሥጋሽ ሥጋን ከነፍስሽም ነፍስን ነሥቶ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ይሆናልና /አምላክ ከአንቺ
ይወለዳልና/ በነቢያት ትንቢት፣ በላእክት ተልእኮ ደስ ያለሽ ምልዕተ ክብር ሆይ ተፈሥሒ ደስ
ይበልሽ አላት፡፡
እርሷም ከዕንግዳ ሰላምታውና ከንግግሩ የተነሣ ለጊዜው ደንግጣ ነበር፡፡ ፍራትንና ድንጋጤን
እያስወገደ ማብሠር ልማዱ የሆነ ቅዱስ ገብርኤል ግን ማርያም ሆይ አትፍሪ መንፈስ ቅዱስ
መጥቶ በአንቺ ላይ ያድራል ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ይለብሳል አምላክ ከአንቺ ይወለዳል
አላት፡፡
ማርያምም ንጽሕት ፍጽምት ናትና ይህ ነገር እንዴት ይሆናል? እኔ እንደሆንኩ እንኳንስ የገቢር
የኀልዮም የለብኝም፡፡ ለመሆኑ መሬት ያለዘር ስታበቅል ሴት ያለወንድ ስትወልድ የት አየህና ነው
እንደዚህ የምትለኝ አለችው፡፡
መልአኩም መልሶ ከአንቺ የሚወለደው ፍጡር ተራ ሰው ሳይሆን፣ ከአንቺ የሚወለደው ዕሩቅ
ብእሲ ሳይሆን ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለው ከሚመሰገኑት ከሦስቱ ወይም ከሥላሴ አንድ ነው፡፡
ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና ይህ የምነግርሽ ሁሉ ይሆናል አላትና እርሷም ይኲነኒ
በከመ ትቤለኒ እንደቃልህ ይሁንልኝ ይደረግልኝ አለችው፡፡
ከዚህ ብሥራት በኋላ ጌታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ
ሰው ሆነ፡፡ እንደእኛ አቆጣጠር መጋቢት 29 ቀን ትስብእቱ ወይም ፅንሰቱ ሆኖ ታኅሣሥ 29 ቀን
++++
ውድ ተመልካቾች እግዚአብሔር ፈቅዶና ወዶ እንኳን ወደ ቅዱስ ዘተዋሕዶ ቻናል በሰላም መጣቹ !!!
++++
#KidusZetewahedo #Mezmur #OrthodoxMUZMUR #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ethiopia #orthodox #share #like #subscribe #christmas #ገና #ልደት #ኢየሱስ #ክርስቶስ #በዓል #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር

Daniel kibret,ዳንኤል ክብረት,Kesis doctor memihir zebene lema, የመናፍቃን ጥያቄ,zebene vs protestant,memihir pawlos new sibket,memihir mihiretab,ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ,ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ብለው ያመሰግኑሻል,like mezemran tewodros yosef,zemary tedy,Maryam mezmur,dingil Maryam mezmur,new Ethiopian orthodox muzmur lyrics,like zemary yilma haylu,የዕየሱስ ክርስቶስ ሙሉ ፊልም ስቅለት, ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ, ስግደት,ስቅለት ፊልም,JESUS FULL MOVIE IN AMHARIC,SIKLET FILM,ህማማት,አብይ ፆም,MEMIHIR GIRMA NEW,MEMIHIR ZEBENE LEMA,SIBKETE WENGEL,SIBKET ORTHODOX,SIBKET AMHARIC,ORTHODOX MUZMUR,ቤተክርስትያን፣የስላሴ መዝሙር,የሚካኤል መዝሙር,የገብርኤል መዝሙር,የማርያም መዝሙር,protestant muzmur,Zerfe muzmur,Silase mezmur,Lideta,Gebriel muzmur,Mickael muzmur,covid 19,Maryam muzmur,Teddy muzmur,Minday muzmur,Mihiretab sibket,Pawlos sibket,Zebene sibket,New Ethiopian music,New Ethiopian muzmur,ቀሲስ ዘበነ ለማ ,new Ethiopian music,new Ethiopian movies,New Ethiopian orthodox muzmu,ዘማሪ ቀሲስ ምዳይ ብርሀኑ,minday birhanu,menday bihanu,tselote hamus,siklet,በፀሎተ ሀሙስ ዘማሪ ቀሲስ ምዳይ ብርሀኑ,jusus on the cross,nsebho muzmur,best orthodox muzmur,*NEW* | "በርባን እኔ ነኝ" | ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ,*NEW* | "ETHIOPIA" | የመናፍቃን ጥያቄ እና የ ዶ/ር ቀሲስ መምህር ዘበነ ለማ መልስ

Ethiopian Orthodox songs and Educations Only in ©Kidus Zetewahedo you tube channel

Комментарии

Информация по комментариям в разработке