Ante yemitsetew selam (አንተ የምትሰጠው ሰላም)

Описание к видео Ante yemitsetew selam (አንተ የምትሰጠው ሰላም)

አንተ የምትሰጠው ሰላም
አንተ የምትሰጠው ሰላም
ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም (2)
ፍቅር ነህና መድኃኔዓለም (2)

ልባችን ቢታወክ ብንደክም በስጋ
ለምድራዊው እንጂ አይሆነንም ዋጋ
ይልቅ ለነፍሳችን የምትሰጠን ሰላም
እረፍት ይሆነናል በማያልፈው ዓለም

ከጥፋት ጠብቀን ከክፉ ፈተና
ሰላምህን ስጠን በእምነት እንድንጸና
በዓለም ማእበል ሰጥመን ሳንጠፋ
ሰላምህን ስጠን አንተ የኛ ተስፋ

በመንግስትህ ብዙ ስፍራ አለ የሰጠኸን
ምድራዊ አይደለም በሰማይ ርስት አለን
የሰው እጅ ያልሰራት የሰው አይን ያላያት
በእምነት በምግባር የምንገባባት

በዛ እንዘምራለን ለፍጥረታት አባት
በሰጠኸን ሰላም በሰራልን እረፍት
በበጎ እንሰለፍ መልካሙን እንስራ
በቀኙ እንዲያቆመን ከቅዱሳን ጋራ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке