ሕይወት ቀያሪው መፅሐፍ አልኬሚስቱ / Life changer book (THE ALCHEMIST)BOOK REVIEW

Описание к видео ሕይወት ቀያሪው መፅሐፍ አልኬሚስቱ / Life changer book (THE ALCHEMIST)BOOK REVIEW

በፖውሎ ኮኤልሆ የተፃፈው ዘ-አልኬሚስት (The Alchemist) የተሰኘው ድንቅ መፅሃፍ አንድ ግሩም ቁብነገር አስፍሮልናል። እርሱም እንዲህ ይላል፣ " ህልማችን እንዳይሳካ የሚያደርገው አንድ ነገር ብቻ አለ፤ እርሱም የውድቀት ፍራቻ ነው። " ማናችንም በትልቁ ማሰብ አይከብደንም፤ ማናችንም ስለ አስገራሚ ነገሮች ማውራትና መተንተን አይከብደንም ነገር ግን የላይሳካ ይችላል ፍረሃት፣ የውድቀት ፍረሃት፣ የይሉኝታ ፍረሃት ትልቅ ሆኖ ትልቅ ሊያደርገን ከሚችል ግሩም ሃሳብ ጋር እንድናረጅ ያደርገናል። ከዚህ በፊት ሰርተህ የማታውቀውን ስራ ልትጀምር ነው። እናም ልትከስር እንደምትችል እያሰብክ ተጨንቀሃል? ይህን አስታውስ መክሰርም ማትረፍም በእጅህ ላይ ነው። እርሱን የምታውቀው ደግሞ ወደስራ ከገባህ ብቻ ነው። ፍረሃት በእራሱ የሌለውን ኪሳራ ወይም ትርፍ አምጥቶ አይሰጥህም። የሚታይ ተግባር በሌለበት ቦታ ስለ ውድቀት፣ ስለ ኪሳራ፣ ስለ ውጫዊ ጫና፣ ስለ መገለል ማውራት አይቻልም።

አዎ! ጀግናዬ..! ሳትጀምር አትሸነፍ፤ እግርህን ሳታነሳ አትሰበር፤ ባልሆነው አትሸበር፤ ባልተከሰተው አትታሰር፤ ገና ለገና ሊመጣ ይችላል በተባለ የወረደ መላምት ትልቁን ሃሳብህን አትቅበረው። ውድቀትም ይግጠምህ ስኬት ሞክሮ ማየትን የመሰለ ነገር የለም። ምንም ነገር ልታልም ትችላለህ መሳካቱን ልታውቅ የምትችለው ግን ስታደርገውና ስታደርገው ብቻ ነው። ምንም ነገር ሊሆንም ላይሆንም የሚችልበት መንገድ እኩል ነው። የህይወትህ ሚዛን እምነትና አመለካከትህ ነው። እንዲሳካ የምትፈልገው ነገር ቢኖር በፍረሃት ውስጥም ሆነህ ማድረጉ ካለማድረግ የተሻለ ነው። ድፍረት፣ እድገት፣ መነቃቃት፣ ስኬትና ተፅዕኖ ፈጣሪነት በድርጊት ውስጥ ሆነህ የሚፈጠሩ ነገሮች ናቸው። የበይ ተመልካች የምግቡን ጠዓም ሊያውቅ አይችልም፤ በፍረሃት ታስሮ፣ በስጋት ውስጥ ወድቆ ሳይሞክር የቀረም ሊገጥመው የሚችለውን መልካም ነገር ሊያውቅ አይችልም።

አዎ! ትርፍና ኪሳራውን፣ ውድቀትና ስኬቱን፣ አድናቆትና ስድቡን፣ ፍቅርና ጥላቸውን የምታውቀው ወደ ተግባር ከገባህ ብቻ ነው። ውጪ ሆነህ ሲያስጨንቁህ የነበሩ ነገሮች ከጅማሬህ ቦሃላ በእርግጥም መኖራቸውን ታረጋግጣለህ፤ ሲያስፈራህ የነበረው ውድቀት በተግባር ውስጥ ሆነህ በእውን መከሰቱን ታውቃለህ። ያለና ተጨባጭ የሆነን ነገር መፍራት ምክንያታዊ አመክንዮ ይኖረሃል፤ ባለሆነና ለመሆኑም ላለመሆኑም እኩል እድል ባለው ነገር ምክንያት መጨነቅና ሃሳብን ወደኋላ መግፋት ሁለተኛውን ውድቀት ያስከትላል። ውድቀትን ፈርትህ ህልምህን ካለመኖር የላቀ ውድቀት እንደሌለ አስተውል። ያላየሀውን የማይጠቅምና እንቅፋት የሚሆን ውድቀት ማመንህን ትተህ ያየሀውንና የምታውቀውን እውነተኛ ሃሳብና ህልምህን አምነህ ተግባርህን ጀምር።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке