ቅርቤ - ይስሃቅ ሰዲቅ // Qirbe - Yishak Sedik

Описание к видео ቅርቤ - ይስሃቅ ሰዲቅ // Qirbe - Yishak Sedik

ቅርቤ - ይስሃቅ ሰዲቅ // Qirbe - Yishak Sedik

''ቅርቤ''

   • ቅርቤ - ይስሃቅ ሰዲቅ // Qirbe - Yishak Sedik  

የሚያስጨንቀኝን ሁሉ ባንተ ላይ ጥዬ
ሸክሜ ተራግፏል
ስጋት አይገባኝም
ልቤም በፊትህ እርፍ ብሏል

ከአይምሮዬ በላይ እጅግ ትልቅ ነህ
ዘልቀህ ታየኛለህ
ካንተ አልሰወርም ውስጤን በርብረህ ሁሉዬን ታውቃለህ

ሊጮህ ሳልይነሳ ምኞቴን ምትሰማው
የውስጤንም ሀሳብ ቀድመህ ምትረዳው
ቅርቤ አንተ ብቻ ነህ ከእስትንፋሴ ይልቅ
ምን እንዲያስፈልገኝ ስለ እኔ የምታውቅ

እግዚአብሔር አምላኬ አንተ አባቴ ነህ
በቅዱስ ማደሪያህ በመቅደስህ ያለህ
ዙፋንህ ሰማይ ነው አላማህ ግን በእኔ
እኔም ወደ ሌላ አላነሳም አይኔን

መላ ሃሳቤን ገና ከሩቅ ሳይደረጅ ነው የምታስተውለው
መቀመጥ መነሳቴም ቢሆን ሁሌም ባንተ የታወቀ ነው
መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ ጎዳናዬን የምታቀና
አይኖችህ በእኔ ላይ ናቸው ሳይሰጋ ይኸው ልቤ ባንተ ፀና

የሚያስጨንቀኝን ሁሉ ባንተ ላይ ጥዬ
ሸክሜ ተራግፏል
ስጋት አይገባኝም
ልቤም በፊትህ እርፍ ብሏል

ከአይምሮዬ በላይ እጅግ ትልቅ ነህ
ዘልቀህ ታየኛለህ
ካንተ አልሰወርም ውስጤን መርምረህ ሁሉዬን ታውቃለህ

ከአይምሮዬ በላይ እጅግ ትልቅ ነህ
ዘልቀህ ታየኛለህ
ካንተ አልሰወርም ውስጤን በርብረህ ሁሉዬን ታውቃለህ

አካሄድን በፊትህ አድርጌ መንገዴን ያቀናህልኝ ጌታ
የእርሱ የሆንኩለት አለ ብዬ በዛ ምድረበዳ ያልተውከኝ ላፍታ
በሄድኩበት መንገድ ሁሉ ከኔ ጋራ የነበርከው
እግዚአብሔር አንተ ብቻ ነህ ሳላይህ እስከዛሬ ስታየኝ የኖርከው 😭😭😭😭

ሊጮህ ሳልይነሳ ምኞቴን የምትሰማው
የውስጤንም ሀሳብ ቀድመህ ምትረዳው
ቅርቤ አንተ ብቻ ነህ ከእስትንፋሴ ይልቅ
ምን እንዲያስፈልገኝ ስለ እኔ የምታውቅ

እግዚአብሔር አምላኬ አንተ አባቴ ነህ
በቅድስ ማደሪያህ በመቅደስህ ያለህ
ዙፋንህ ሰማይ ነው አላማህ ግን በእኔ
እኔም ወደ ሌላ አላነሳም አይኔን

መዝሙረ ዳዊት - ምዕራፍ 139
1 አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም።
2 አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ።
3 ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥
4 የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ።
5 አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
6 እውቀትህ ከእኔ ይልቅ ተደነቀች፤ በረታች፥ ወደ እርስዋም ለመድረስ አልችልም።
7 ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ?
8 ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ።
9 እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥
10 በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።
11 በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤
12 ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና፥ ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና፤ እንደ ጨለማዋ እንዲሁ ብርሃንዋ ነው።
13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል።
14 ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።
15 እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።
16 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ።
17 አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ!
18 ብቈጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ ይበዛሉ፤ ተነሣሁም፥ እኔም ገና ከአንተ ጋር ነኝ።
19 አቤቱ፥ አንተ ኃጢአተኞችን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ ከእኔ ፈቀቅ በሉ።
20 በክፋት ይናገሩብሃልና፤ ጠላቶችህም በከንቱ ያምፁብሃል።
21 አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? ስለ ጠላቶችህም አልተሰቀቅሁምን?
22 ፍጹም ጥል ጠላኋቸው፥ ጠላቶችም ሆኑኝ።
23 አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ፤
24 በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке