አራቱ ስምምነቶች: The Four Agreements :A Book Review In Amharic with English captions!

Описание к видео አራቱ ስምምነቶች: The Four Agreements :A Book Review In Amharic with English captions!

አራቱ ስምምነቶች በዶንሚጌል ሩይዝ (የመጽሐፍ ማጠቃለያ) ለግል ነፃነትመመሪያ፡- አራቱ ስምምነቶች አእምሯቸውን ለመግዛት እና በሕይወታቸው ላይ የበለጠ ሆነ ብለው እራሳቸውን ለመቆጣጠር ለሚጀምሩ ሰዎች ታላቅ መጽሐፍ ነው። ስለዚህ መጸሃፍ በሺዎች የሚቆጠሩ የመጸሃፍ ማጠቃለያ እና ዳሰሳ ተደርጎበታል፡፡ ቶልቴክ ከሺህ ከሚቆጠሩ ዓመታት በፊት ቶልቴክ በመላው ደቡባዊ ሜክሲኮ የሴቶች እና የወንዶች የጥበብ እና አውቀት ማህበረሰብ ባለቤት በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ የሰው ዘር ተመራማሪዎች ቶልቴኮችን እንደ ማንኛውም ብሔር ወይም ጎሳ ቢቆጥሩዋቸውም ቴልቶኮች ግን ሳይንቲስቶች የነበሩ እና የጥንት መንፈሳዊ እውቀትና ልማዶችን በመፈተሽና በመጠበቅ የኖሩ ታላቅ ማህበረሰብ ነበሩ፡፡ ቶልቴኮች ከሜክሲኮ ከተማ ወጣ ወዳለው እና ጥንታዊ የፒራሚድ ከተማ በሆነችው ቴኦቲሁዋካን ወደ ነበሩት ማስተሮች ወይም መምህራን በእነሱ ቋንቋ ናጋልስ ወደ ሚባሉ ጥበብን ለመማር ተሰበሰቡ። ቶልቴክ እንደ ሃይማኖቶች የተደራጀ ባይሆንም በምድር ላይ ስለ እወነት ያስተማሩ ማስተሮችን ወይም መምህራንን በሙሉ ያከብራል፡፡ ቶልቴክ ከዚህ ከምናየው አለም ባሻገር መንፈሳዊ አለም እንዳለ እና በዚህ መንገድ ላይ የሚጉዋዝ ሰው ተፈጥሩአዊ የሆነ ፍቅር ና ደስታ እንደሚያገኝ ይገልጻል፡፡ ወደ ቶልቴክ የሚወስዱ ሶስት ማስተማርያ መንገዶች አሉ፡፡ አንደኛው ማስተማርያ መንገድ ንቃተ ህሊናን ማዳበር ነው፡፡ በንቃተ ህሊና ትምህርት ውስጥ እንዴት ስለራሳችንን ማንነት ሁሉን አቀፍ ንቃተ ህሊና እንደሚኖረን እና እንዴት በተፈጥሮ ወደተሰጠን ማንነት እንደምናድግ ያስተምረናል፡፡ ሁለተኛው ትምህርት በደረስንበት ንቃተ ህሊና እንዴት ነው ከልማድ ነጻ የምንሆነው የሚለው ነው፡፡ ሶስተኛው ትምህርት የአላማ እና የህይወት ህይላችንን ትራንስፎርም ወይም ወደ ላቀ ደረጃ እንዴት ነው የምንዳርሰው የሚለው ነው፡፡ አንድ ህያው የሆነ ማንነት ፍጥረታትን ሁሉ አስገኝቱዋል፡፡ እናም ይህንን ማንነት ህይወት ያለውን ሁሉ ያስገኘ አምላክ ብለን እንጠራዋለን፡፡ • መሻት በራሱ ሕይወት ነው፡፡ መሻታችን በራሱ ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ነው። • • ስለዚህ በመሻተችን ላይ ስንሰለጥን በህይወታችን ውስጥ እራሳችንን በፍቅር እንገለጻለን። • • " አራቱ ስምምነቶች የሚባሉት በቶልቴክ እሳቤ ህይወታችንን መለወጥ እንዴት እንደምንችል የሚያብራሩ ማጠቃለያ ናቸው። • እናም መንገዶቹን ስናውቅ ማንኛውንም ሲኦል መሰል ሁኔታዎች እንኩዋን ሰአይቀሩ ወደ ገነትነት መለወጥ እንችላለን፡፡ • • የቶልቴኮች ጥበብ የምድሪቱዋን ህልም ወደ እናንተ የግል የመንግሥተ ሰማያትነት ህልም መለወጥ የሚያስችል ነው። ይህ ጥበብ በፍርሃት ላይ የተመሰረቱ ስምምነቶችን በመቀየር እና የእራሳችሁን አእምሮ በራሳችሁ መንገድ በማስተካከል በህይወታችሁ ድንቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ ይላል ። • ከመወለዳችን በፊት የነበሩት ሰዎች ዛሬ ላይ የማህበረሰብ ሕልም ወይም የምድሪቷ ሕልም ብለን የምንጠራውን ትልቅ የውጫዊ ሕልም ፈጥረውልን ነበር ። የምድሪቷ ህልም በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የትናንሽ የግል ህልሞች ሰብስብ ሆኖ የጋራ ህልም ነው ፣ የትናንሽ የግል ህልሞች የሚባሉት ከሚያካትቱት ውስጥ የቤተሰብ ህልም ፣ የአንድ ማህበረሰብ ህልም ፣ የከተማ ህልም ፣ የአንድ ሀገር ህልም ሲሆን እነኚህ በአንድ ላይ የመጨረሻውን የመላውን ሰዎችን ህልም ይፈጥራሉ ። የምድሪቱዋ ህልሞች የሚባሉት ደግሞ ባጠቃላይ ሁሉንም ብህይወታችንን ውስጥ ተጽእኖ ውስጥ የሚከቱንን
የህብረተሰብ ህጎች፣
እምነቶች፣ ድንቦች፣
ሃይማኖቶች፣
የተለያዩ ባህሎች እንዲሁም
መንገዶች፣
መንግስታትን፣
ትምህርት ቤቶችን፣
ማህበራዊ ዝግጅቶችን
እና በዓላትን ያጠቃልላል። •
የተወለድነው እንዴት ማለም እንዳለብን የምንችለበት ችሎታ ይዘን ነበር፡፡ •
፤ ከእኛ በፊት ያሉት ሰዎች ደግሞ ኅብረተሰቡ የሚያልመውን ህልሞች እና
እነዚህን ህልሞቾ ደግሞ እንዴት ማለም እንዳለበት የራሳቸውን መንገድ አስተምረውናል

:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የውጪው ህልም በጣም ብዙ ህጎች ስላሉት ልጅ ገና ከተወለደበት ግዜ ጀምሮ የህጻኑን ትኩረት ከማህበረሰቡ በወረስናቸው ውጪያዊ ህጎች ላይ እንዲሆን ብዙ እንሰራለን። • • . የውጪያዊው ሕልም እንዴት ማለም እንዳለብን ለማስተማር
ቤተሰብን
እናት ና አባትን፣
ትምህርት ቤቶችን
እና የሃይማኖትን ተቋማትን መሳርያ አርጎ ይጠቀማል። • •
ትኩረት ማድረግ ማለት ልንገነዘበው በምንፈልገው ነገር ላይ ብቻ የማድላት ወይም ትኩረታችንን የሚስብ ነገርን የመከተል ችሎታ ነው። • • በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነገሮችን በአንድ ጊዜ ልናይ እንችላለን፣ ነገር ግን ትኩረታችንን ተጠቅመን ልናስተውለው የምንፈልገውን ብቻ መርጠን በአዕምሮአችን በመቅረጽ ወደ ተግባር ልንገባ እንችላለን። • • በዙሪያችን ያሉ በእድሜም ሆነ በእውቀት ከኛ የሚበልጡ ሰዎች ገና ከልጅነታችን ትኩረታችንን እነሱ ወደፈለጉበት አቅጣጫ እንዲሄድ በማድረግ መረጃ እና እውቀት ብለው የወሰኑትን በመደጋገም ወደ አእምሮአችን አስገብተዋል። • • የምናውቀውን ሁሉ የተማርነው በዚሁ ትላልቅ በምንላቸው ሰዎች ባሳዩን መንገድ ነው። • የውጪያውው ህልም ትኩረታችንን የሚስብ እና ከምንናገረው ቋንቋ ጀምሮ ምን ማመን እንዳለብን የሚያስተምረን ነው። • • ቋንቋ ሰዎችን የሚያቀራርብ የመግባባያ ኮድ ነው። • እያንዳንዱ ፊደል፣ እንዲሁም በእያንዳንዱ ቋንቋ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ቃል ስምምነት ነው። • ለምሳሌ ይህንን የመጸሃፍ ክፍል ከመጽሐፉ ገጽ የተወሰደ ብለን እንጠራዋለን; እናም በምሳሌው ውስጥ ገጽ የሚለው ቃል ለመግባባት የተስማማንበት ቃል ነው። • የቋንቋንም መዋቅር ከተረዳን በሁዋላ በሀሳብ ምስረታ ትኩረታችንን የሚስቡ ነገሮችን በመፍጠር የመንፈልገው ሀሳብ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው በቋንቋ አማካኝነት እንዲተላለፍ እናደርጋለን • • በልጅነታችን እምነታችንን የመምረጥ እድል አልነበረንም፣ ነገር ግን የምድሪቱ ህልም ይህን ይመስላል በሚሉ እና ሌሎች ሰዎች ባስተላለፉልን መረጃ መሰረት ተስማምተናል ። • • መረጃን ለማከማቸት ብቸኛው መንገድ ስምምነት ነው. • የውጪው ህልም ትኩረታችንን ሊነካው ይችላል, ነገር ግን ካልተስማማን, ያንን መረጃ አናከማችም. • ልክ እንደተስማማን እናምናለን ይህም እምነት ይባላል። • እምነትን መያዝ ማለት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማመን ነው። እናም ይህን ሂደት የሰውን ልጆች ማግራት እና ማላመድ ብዬዋለሁ። እና በዚህ የማላመድ ስራ እንዴት እንደምንኖር እና እንዴት ማለም እንዳለብን እንማራለን፡፡ . ሰውን በማላመድ ሂደት ውስጥ በውጪያዊው ህልም ያለው መረጃ ወደ ውስጣዊው ህልም ይተላለፋል , ይህም ሙሉ የእምነት ስርዓታችንን ይፈጥራል. • አንድ ህጻን ልጅ በመጀመሪያ የነገሮችን ስም እንዲማር ይደረጋል፡፡ • • ለምሳሌ ፡ እማማ፣
አባቴ፣
ወተት፣ ጠረጴዛ። •
ከቀን ወደ ቀን፣
በቤት፣
በትምህርት ቤት
፣ በቤተክርስቲያን
በመስኪድ
እንዲሁም በሚዲያ እንዴት እንደምንኖር፣ ምን አይነት ባህሪ ተቀባይነት እንዳለው ለህጻኑ ማስተማር ይጀመራል። • የውጪያዊው ህልም እንዴት ሰው መሆን እንዳለብን ያስተምረናል. • • የመላመዱ ሂደት በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ በሕይወታችን ውስጥ በአንድ የተወሰነ ጊዜ እኛን ለማላመድ ማንም ሰው • የማያስፈልገን ደረጃ ላይ እንደርሳለን። • እዚህ ደረጃ ስንደርስ እኛን ለማዳን እናት ወይም አባት፣ ትምህርት ቤት ወይም ቤተ ክርስቲያን አንፈልግም።በወረስነው ልማድ እንመላለሳለን። • በደንብ የሰለጠነ የቤት ጠባቂ ይመስል የራሳችን ደንብ ጠባቂ እነሆናለን። • እናም በራሳችን የተላመድን ፍጡራን እንሆናለን • • • • የእምነት ሥርዓት አእምሮአችንን እንደሚገዛ የሕግ መጽሐፍ ነው።በእምነታችን የሕግ መጽሐፍ ውስጥ ያለው ማንኛውም ነገር • ያለ ምንም ጥርጥር የእኛ እውነት ብለን የምንቀበለው ነው። • እነዚህ ፍርዶች ከውስጣችን ጋር የሚቃረኑ ቢሆኑም እንኳ ሁሉንም ፍርዶቻችንን በሕግ መጽሐፍ መሠረት እናደርጋለን። • • እንደ አስርቱ ትእዛዛት ያሉ ሕጎች እንኳን ወደ አእምሯችን ተዘጋጅተው በመግባት እራስን በማላመድ ሂደት ውስጥ ትልቅ ቦታ ይወስዳሉ፡፡ • • ከቤተሰብ እንዲሁም ከማህበረሰቡ ሁሉ የተቀበልናቸው ስምምነቶች በሙሉ አንድ በአንድ ወደ ሕግ መጽሐፍ ገብተዋል፣ እናም እነዚህ ስምምነቶች በህይወት ውስጥ ያሉንን ሕልሞች ሀሉ ይቆጣጠራሉ • መንግስት የህብረተሰቡን ህልም የሚመራበት የህግ መጽሃፍ እንዳለው ሁሉ የእምነት ስርዓታችንም የግላዊ ህልማችንን የሚቆጣጠርበት የህግ መጽሃፍ ነው።
credit to: www.sloww.co/four-agreements-book/

Комментарии

Информация по комментариям в разработке