Gomen Kitfo ጎመን ክትፎ

Описание к видео Gomen Kitfo ጎመን ክትፎ

የፆም ጎመን ክትፎ የግብዓት እና የማጣፈጫ ቅመም ዓይነት
1. ጎመን (የሃበሻ፣ ጥቁሩ እና ሲመሮ ጎመን መጠቀም እችላሉ)
2. ከ30-45 ደቂቃ ጎመኑን መቀቀል (እንደ ምድጃ አይነቱ ይለያያል ስለዚህ ውሃውን እስኪጨርስ በትዕግስት ይጠብቁ ፤ እንዲሁም እንዳያር ቶሎ ቶሎ ይመልከቱት)
ጎመን ከተቀቀለ በሃላ ከ30-45 ደቂቃ ሙሉ ለሙሉ እሲቀዘቅዝ ማስቀመጥ ከዛ በሽንኩርት/በስጋ መፍጫ መፍጨት ወይም በእጅ ድቅቅ አድርጎ መክተፍ፡፡
3. በቡና ማንኪያ ልኬት
የሩብ ግማሽ ማንኪያ አብሽ ጨምሮ በደንብ ቡኒ እሰኪሆን መጥበስ
1 የቡና ማንኪያ ውሃ ጨምሮ እሳቱን ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት
የዌራ ዘይት ወይም ማንኛውም የምግብ ዘይት መጨመር የማትፆሙ ከሆነ ቂቤ መጠቀም
ግማሽ ሚጥሚጣ እና ኮረሪማ መጨመር
ከዛ የፈጨነውን ኮመን ጨምሮ በደንብ መለወስ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке