ሰላም ለኪ እያለ | Selam leki eyale (የምልክት ቋንቋ/sign language mezmur)

Описание к видео ሰላም ለኪ እያለ | Selam leki eyale (የምልክት ቋንቋ/sign language mezmur)

ሰላም ለኪ እያለ /2/
ሐርና ወርቁን ስታስማማ
የገብርኤል ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ
ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ

ውሃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ
ሊያበስርሽ የመጣው በታላቅ ደስታ
ከሞገስሽ ብዛት /2/ ሲታጠቅ ሲፈታ
አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ
አዝማች--
የምሥራቹን ቃል ምስጢር ተሸክሞ
ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ
እርጋታ ተሞልታ /2/ ነገሩን መርምራ
የመልአኩን ብስራት ሰማችው በተራ
አዝማች--
ይደሰታል እንጂ መንፈሴ በአምላኬ
በምስጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ
ሃሳቤ ልቅፅበት /2/ ሌላ መች ያስባል
ለእኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል
አዝማች--
ከአንቺ የሚወለደው ልዑል ነው ክቡር
የተመሰገነ በሰማይ በምድር
ምስጢሩ ሃያል ነው /2/ ይረቃል ይሰፋል
ካንቺ በቀር ይኼን ማን ይሸክመዋል
አዝማች--
እፁብ ነው ድንቅ ነው አንቺን የፈጠረ
አንቺን በመውደዱ ሰውን አከበረ
አለም ይባረካል /2/ በማህፀንሽ ፍሬ
ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ ዘርዝሬ
አዝማች--

Комментарии

Информация по комментариям в разработке