ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 | NEW ETHIOPIAN MENZUMA\NESHIDA | አዲስ መንዙማ\ነሺዳ

Описание к видео ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 | NEW ETHIOPIAN MENZUMA\NESHIDA | አዲስ መንዙማ\ነሺዳ

ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 | NEW ETHIOPIAN MENZUMA\NESHIDA | አዲስ መንዙማ\ነሺዳ
_____________
   • ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 ...  
   • ኑር አምባ | ዋሪዳ 6 | NUR AMBA | WARIDA 6 ...  
*************
Warida is the ultimate next generation Ethiopian Menzuma & Nasheed Groups

YouTube:    / @waridatubeoffcial  
Telegram: t.me/WARIDATUBEOFFCIAL
Facebook:   / waridatubeoffcial  
⤵️⤵️⤵️➖➖⤵️⤵️➖➖⤵️⤵️
በYoutube:    / muazhabibofficial  
በFacebook:   / muazhabibofficial  
በTelegram:
t.me/MuazHabibOfficial
*
ከላይ በተጠቀሱት አድራሻዎች Subscribe Like እና Join በማድረግ የስራዎቼ ተከታታይ ይሁኑ!

ሙዓዝ ሐቢብ ነኝ እወዳችኋለሁ !

#ኑር-አምባ ነሺዳ ግጥም

ከደጅዎ ሲጠጋ ሰባራ እኔነቴ፣
አልቃና አለኝ ተደፍቶ አንገቴ፣
እኔስ መጣሁ እንጂ ደፍሬ መዲና፣
መች ይገባኝ ነበር ይህ ክብር ይህ ዝና።



ተጠራሁ ልቤ ተነሳ
ደርሶልኝ ያ’ላህ ቀጠሮ፣
እግሬ ቢያንስብኝ ለጉዞ
ክንፍ አሻኝ ለመሄድ በርሮ፣

ኑር አምባው መሐል ደርሼ
ከጅዬ ‘ንዲሽር ህመሜ፣
ምን ጉድ ነው ሸውቁ ባሰብኝ
ሲፈታ የዘመን ህልሜ።

ሰምሮልኝ ዕድል ዕጣዬ
ብወፈቅ መድረስ ኑር አምባ፣
ወኔ አጣሁ ደፍሮ ለመዝለቅ
ከቅፅርዎ ከቶ እንዴት ልግባ፣

ታስሬ ሃያእ ጠፍሮኝ
ቆሜያለሁ ሰብሬ አንገቴን፣
ተስኖኝ ደጅዎ መጠጋት
አዝዬ ምስጢር ናፍቆቴን።

ከቀዬው ሳለ ወዳጅዎ
ናፍቆቱን ሠርክ ቢሰድም፣
አማናው የጎደለበት
እንዳሻው አይራመድም።

ቢከጅል መጠጋት ደጅዎ
ጥፋቱን ጉያው ሸሽጎ፣
እንደምን ከበርዎ ይድረስ
ተሳስሮ ኧረ እንዴት አድርጎ።


አልፊ ሰላለህ ዓለይካ
አልፊ ሰላሚ ዓለይካ
አንቱ የከውኑ ነጋሴ
ናፍቆትሁ የለውም ዲካ

ከረውዳው ለመድረስ ቢከጅልም ልቤ፣
ከቶ እንዴት ልጠጋ እንደምን ተስቤ፣
ቃል ማውጣት ተስኖኝ ታስሮ አንደበቴ፣
ደጅሁን አያለሁ ቢታገስ ናፍቆቴ።

ሃያትን በሚዘይነው
የስክነት ሸማን አልብሶ፣
በኑር መስክ ላይ መገኘት
መድመቅ ነው ብርሃን ተውሶ።

ዕጣው ቢደርሰኝ ከረህማን
በደጅዎ ‘ሚያመላልሰኝ፣
እንዲያ ናፍቄ እንዳልከነፍኩ
እውነቱን ማመን ተሳነኝ።

ሲከንፍ የመጣ ናፋቂ
ጨክኖ ካገርዎ ደርሶ፣
ሲያነባ ይነጋበታል
ላይወጣ ናፍቆት በልቅሶ፣

ምን አለኝ ብዬ ልጠጋ
ጎድሎብኝ ያንቱ አማና፣
እንደምን ልድረስ ከደጅዎ
በፀፀት እንዴት ልቃና፣

ቆሜያለሁ ህመም ታቅፌ
የሩቅ ሰው ባይተዋር ሆኜ፣
ቁጭቴን ጉያዬ አኑሬ
ኑር አምባ መሃል መንኜ።

ተመኘሁ ወኔውን መዋስ
ከሰልማን ከፋርሱ አበባ፣
ዘይሬሁ እንዲወጣልኝ
በናፍቆት ረውዳ እንድገባ።

ብትከዝ ቀኔ ጨልሞ
ሃለቴ ካንቱ ቢርቅም፣
የረህማን እዝነት ኪዳን ኖት
አፍሬስ ቤትዎን አለቅም።

ሞልቶልኝ ጦይባ ደርሼ
ብቆምም ጠርዙን ታክኬ፣
ቢያቅተኝ እግሬን ማላወስ
ቁዘማው ቢሆንም ልኬ፣

ሊምረኝ ሽቶ ነው እንጂ
ያመጣኝ ልቤን ቀስቅሶ፣
አዳልጦኝ ብወድቅ እንደሰው
መች ቀጣኝ ረሂም ታግሶ፣

ሙሂቡ ከሚነግስበት
ዓለሙ ሙራዱ ሞልቶ፣
ቆሜያለሁ ተራ እስኪደርሰኝ
ቢያይልም ብርቱ ናፍቆቶ።

ቁስለኛው አማና አጉዳዩ፣
የቆመው ሃረምዎ ላይ፣
አፍሮ እንጂ ሃሉ ቢዛነፍ
ነበረው ብርቱ ጉዳይ፣


አልፊ ሰለላህ አለይካ አልፊ ሰላሚ ዓለይካ
አንቱ የከውኑ ነጋሴ ናፍቆቶ የለውም ዲካ×2




የሸውቅዎ ወጀብ ወርውሮት
ስላንቱ ሰርክ እንዳለመ፣
ኸበርዎን እያደመጠ
ሳያዮት እንደታመመ፣

ሚለብሰው እራፊ አጥቶ
በሀሩር እየተቀጣ፣
መሃባ እያንሳፈፈው
ጆንያ ታጥቆ እንደወጣ፣

የዐይኑን ረሃብ ሊያስታግስ
ኬላውን ጥሶ ድንበሩን፣
እረፍቱ ትጋቱ ሆኖ
ሰይዲን እስኪያይ ጀንበሩን፣

ዘለቀ ጦይባ ከተመ
ሞልቶለት ደጆ ደረሰ፣
ናፋቂ ምን አካል አለው
ጆንያም ሃርም ለበሰ፣

ናፍቆቱን የዓይኑን ሲሳይ
በስስት እያየ አሻግሮ፣
ተጠጉት ሰይዲ መጡ
ምን ይሁን ቆመ አቀርቅሮ፣

ባገለደመው ጆንያ
በሸውቁ ህመም ማህተሙ፣
ዙል ቢጃ ደይን ብለው
ሰየሙት ሰይዲ ልቡን አከሙ፣

የናፍቆት ህመሜ ሲያይል
መሃባው ደርሶ ሲንጠኝ፣
ስናፍቅ የኑር አምባዎን
አጀሌ ሲያስደነግጠኝ፣

የዙልቢጃደይን ወዳጅዎ
እየታወሰኝ ሃለቱ፣
ሸውቅ ላስጌጠው ጆንያው
በሆንኩኝ ዝምዝም ጥለቱ፣

ባረገኝ የሸውቁ ወራሽ
የሚያከንፍ ወደ ኑር አምባ፣
ስም እንዲያወጡልኝ ሰይዲ
በስኬት ቤቴ እንድገባ!!

ግጥም:- ሙሀመድ ፈረጀ
ዜማ :- ሙዓዝ ሀቢብ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке