Ethiopian Tibs የምድጃ ጥብስ

Описание к видео Ethiopian Tibs የምድጃ ጥብስ

እንኳን አደረሳችሁ
ጥብስ ስጠብሱ ስጋው እየገነተረ ካስቸገራችሁ በመለኛ ገፅ ቆንጆ መላ ይዘንላቹሃል ።

ጥብሱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና የማጣፈጫ ቅመም አይነቶች

700 ግራም የበሬ ስጋ እና ጎድን
4 ፍሬ የተላጠ ነጭ ሽንኩርት

ስጋውን ለመቀመም :
4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት ( በዘይቱ ፋንታ ስጋው ላይ ያለ ሞራ ካለ እሱን መጠቀም ትችላላችሁ )

የማጣፈጫ ቅመሞች በቡና ማንኪያ ልኬት
1 ሮዝሜሪ
1 ከሙን
1 ቀረፋ
1 የነጭ ሽንኩርት ዱቄት
ግማሽ የዝንጅብል ዱቄት
1 ቁንዶ በርበሬ
1 ጨው ( የጨው መጠኑ እንደምትፈልጉት መጠን ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ )

እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ግብዓቶች ጨምራችሁ እጃችሁን በመጠቀም ወይም በማንኪያ በደንብ ማሸት ። እያንዳንዱ የስጋው ክፍል በቅመም መለወሱን እርግጠኛ ሁኑ ።

በሰሃን ወይም በላስኪክ ሸፍናችሁ ለ1-2 ሰዓት ያህል ማቀዝቀዣ ቤት ውስጥ ማቆየት (ካልፈለጋችሁም ቀጥታ መጥበስ ትችላላችሁ )

የአበሳሰል መመሪያ
የመጋገሪያ ምድጃውን ለ5 ደቂቃ አስቀድሞ በ220 ዲግሪ ለ5 ደቂቃ ማጋል
የመጋገሪያ ምድጃ ውስጥ በ 220 ዲግሪ የላይኛውን እና የታችኛውን አብርታችሁ ለ20 ደቂቃ መጥበስ።

ከምድጃው እንዳወጣችሁት
የአትክልት ግብዓቶች
2 ቀይሽንኩርት
2 አረንጓዴ ቃሪያ
1 ፍሬው የወጣለት ቲማቲም መጨመር እና መቀላቀል

Комментарии

Информация по комментариям в разработке