በመጀመሪያ / BEMEJEMERYA by KETI JESUS 2017/2024

Описание к видео በመጀመሪያ / BEMEJEMERYA by KETI JESUS 2017/2024

“በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”
— የዮሐንስ ወንጌል 1:1-3

በመጀመሪያ

በመጀመሪያ ቃል ነበረ
ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ
ቃልም እግዚአብሔር እሱ ነበረ
ሁሉ በእርሱ ተፈጠረ
ከአማልክት ማነው ሚወዳደርህ
አቻ የሌለህ አንተ ነህ
አንተ ግን አንተ ነህ ሚመስልህ የሌለህ
ትናንትም ዛሬም ዘላለም ያው ነህ

በጨለማ አለም በድቅድቅ ላለው
ብርሀን መጣ ሒወት የሆነው
መንገድ እውነት ህይወት
ከእርሱ ውጪ የለም
ለተቀበሉት አዳኝ ዘላለም
በበደላችን ሙታን ለነበርን
ለዚ አለም ገዢ የተሰጠን
ክርስቶስ ነብሱን ቤዛ አድርጎልን
ከአብ ጋር እኛን አስታረቀን

በአምላክነቱ ልቆ የኖረው
በማይታይ ብርሀን በክብር ያለው
ለኛሲል ወርዶ ፍቅሩን ያሳየ
እርሱ አምላካችን እጅግ ልዩነው
ከፍ ከፍ ያለ ልእልና ያለው
ስሙም ቅዱስ ቅዱስ የሆነው
እንደተፈራ ያለ በክቡሩ
ሁሉን ሚገዛ በጽኑ ሀይሉ

ይህ ኢየሱስ የመዳን አለት
ለተቀበልነው የሆነ ህይወት
እናውጃለን ለፍጥረት ሁሉ
ከሞት መውጊያ ቀስት እንዲከለሉ
ዛሬም በእርሱ እታመናለሁ
አዳኝነቱን ዘምራለሁ
ለወንድሞቼም እናገራለሁ
ኢየሱስ ጌታ ነው እላለሁ
በጺዎን ላለው ለእምላክ እንዘምር
ላህዛብ ሁሉ ድንቁን እንመስክር
ሀያል ድንቅ አምላክ ሆኖ የኖረ
ከቶ እንደ እግዚአብሔር ከየት ነበረ (2x)

Connect with Keti Jesus:
https://www.tiktok.com/@keti_jesus_of...
https://www.instagram.com/keti_jesus_...

Комментарии

Информация по комментариям в разработке