#AASTU

Описание к видео #AASTU

#ASTU & #AASTU

በ2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡


⚡️የምዝገባ ጊዜ፡-
ከመስከረም 06 እስከ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም

⚡️ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡-
መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ይሆናል፡፡

⚡️የምዝገባ ቦታ:
የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online https://stuoexam.astu.edu.et ०९ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡ www.aastu.edu.et; www.astu.edu.et

⚡️ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡ በድህረ ገጻችን የምዝገባው ቀን ካበቃበት በኋላ እናሳውቃለን።

⚡️ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
በምዝገባ ወቅት በመረጡት ዩኒቨርሲቲ (የፈተና ጣቢያ) በአካል በመቅረብ ይሆናል።

⚡️ማሳሰቢያ፡-
የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

⚡️በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡

⚡️ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣

ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡- www.aastu.edu.et: www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በe-mail የሚገለፅ ይሆናል፡፡

⚡️አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፤ ማለትም (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡

ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡

አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

⚡️የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም፡፡

በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል፡፡

⚡️በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል።

በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ ፈተና ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው፡፡

በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድረ-ገፆች መጎብኘት ይቻላል፡፡

www.aastu.edu.et ; www.astu.edu.et

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፡፡

[ከላይ የተያያዘዙትን ምስሎች ይመልከቱ]

ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Комментарии

Информация по комментариям в разработке