የማለዳ በገና ዝማሬ

Описание к видео የማለዳ በገና ዝማሬ

የማለዳ ጸሎት 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን 
እግዚአብሔር በየማለዳው ለጸሎት ያነቃናል፣  በየቀኑም ሊመራን በአጠገባችን አለ። ስንደክም ወይም በጭንቀት ስንሰቃይ ይደግፈናል አንድ አንዴም ፈተናው ለበረከት ከመጣ ለጥቂት ፈተና አልፈን ብንሰጥም እንኳን እግዚአብሔር መውጫውን ያዘጋጃል ። ከዚህ ሁሉ በኃላ እግዚአብሔር በብዙ በረከት እንደሚጎበኘን እርግጠኛ መሆን አለብን።  ሌላው ቀርቶ በመጪዎቹ ቀናት በማያልቀው ፍቅሩ እና በተትረፈረፈ ለጋስነቱ ይሞላናል። በኢሳይያስ ትንቢት ም 50 ቁ 4 ላይ “ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል” ይላልና። የግል ህይወታችን የቤተሰባችን ህይወት ቄየውና መንደሩ ከተማውና ሃገሩእንስሳትና ሰብሉ አራዊትና ደኑ በሰላም ውለው እንዲያድሩ ጦርነት እና ቸነፈር እንዳይመጣ ካለም እንዲወገድ ሀገር መፀለይ አለባት እንደሚታወቀው ሁሉ
በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን በኢትዮጵያ ሬድዮ ማለዳ ማለዳ ልክ በኢትዮጵያ አቆጣተር ማለዳ 2፡00 በጸሎት ይጀመርና አንድ የበና መዝሙር ይሰማ ነበር። ይህንን የማለዳ መዝሙር የሚያቀርቡት ታዋቂው በገና ደርዳሪ ደምሴ በገና እና ሌሎችም ጠበብት ነበሩ። ስለዚህም በዛ ወቅት ኢትዮጵያ በበረከት ተሞልታ ሰላምዋ ጸንቶ ትኖር ነበር። ያ የአገር ምሰሶ የሆነ ጸሎት ሲቀር ግን የምታዩት የምሰሙት ሆነ:: ከዚህ በኋላ ግን ሞኞች መሆን የለብንም ማለዳ ማለዳ ብሔራዊ የፀሎት ሰዓት ሊኖረን ይገባል:: በዚህ መሰረት በእኛ ቻናል ላይ ዘውትር በኢትዮጵያ አቆጣተር ማለዳ 2፡00 በጸሎት እና በበገና እግዚአብሔር ቢፈቅድ ቀናችንን እንጅምራለን። አባቶች በቡራኬ ቀኑን ይባርኩልናል። ስለዚህም ይህንን የምትሰሙ ሁሉ ስለሃገራችን ሰላም ስለ ዓለምም ሰላም ስለ ቄየውና ስለግል ህይወታችን ለትንሽ ደቂቃዎች አብረን እንፀልይ ስንል በማክበር እንጠይቃለን::

የተዋህዶ_መዝሙራትን_በብዛት_ለማግኘት_ቻናሉን_ሰብስክራይብ_ያድርጉ። እንዲሁም በሱፐር ታንክስ ይደግፉን

Комментарии

Информация по комментариям в разработке