Atronos: Tizta by Hadis Alemayehu ትዝታ በሀዲስ አለማየሁ፡፡ ኪሮስ ሀይለስላሴ እንደተረከው፡፡

Описание к видео Atronos: Tizta by Hadis Alemayehu ትዝታ በሀዲስ አለማየሁ፡፡ ኪሮስ ሀይለስላሴ እንደተረከው፡፡

ትዝታ በሀዲስ አለማየሁ፡፡
ኪሮስ ሀይለስላሴ እንደተረከው፡፡
የተወደዳችሁ የአትሮኖስ ታዳሚያን፣ በዚህ የአትሮኖስ ዝግጅት የምንገልጠው “ትዝታ” የተሰኘውን የሀዲስ አለማየሁን መጽሀፍ ነው፡፡ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ በ1902 እንደእኛው አቆጣጠርበደብረማርቆስ ከተማ የተወለዱ፣ በኢትዮጲያ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ትምህርት ብዙ ርቀት የተጓዙ፣ ቅኔ የተማሩና፣ በኋላ ወደአዲስ አበባ መጥተው ዘመነኛውን ትምህርት የቀሰሙ ኢትዮጲያዊ ነበሩ፡፡ጣልያን ኢትዮጲያን በወረረችበት ወቅት ከ1928 እስከ 1930 ድረስ ከራስ እምሩ ጦር ጎን ተሰልፈው በአርበኝነት ሲዋጉ ከቆዩ በኋላ፣ ተማርከው ወደጣልያን ተወስደው ፖንዝና ሊፓሪ በተባሉት የሜዲቴራንያን ደሴቶች ውስጥ ለ7 አመታት ታስረዋል፡፡ በተባበሩት ሀይላት ድል ምክንያትም ነጻ ወጥተው ወደሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ሀዲስ አለማየሁ ፍቅር እስከመቃብርን፣ ወንጀለኛው ዳኛን፣ የእልም እዣትን፣ ተረት ተረት የመሰረትንና በዚህ ዝግጅት በአትሮኖሳችን የምንገልጠውን “ትዝታን” ጽፈዋል፡፡ በትምህርት ሚኒስቴርና በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በልዩ ልዩ እርከኖች ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን፣ በእየሩሳሌም የኢትዮጲያ ተወካይ፣ በዩናይትድ እስቴትስና በተባበሩት መንግስታት የኢትዮጲያ ልዩ ልኡክ፣ በብሪታንያና በኔዘርላንድስ የኢትዮጲያ አምባሳደርም ሆነው ሰርተዋል፡፡ ሀዲስ አለማየሁ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት አግኝተዋል፡፡
ታድያ ዛሬ በአትሮኖስ፣ አስቀድመን እንዳመለከትነው፣ ከሁለተኛው የጣልያን ወረራ ቀደም ካለው ጊዜ አንስቶ የአርበኝነትና የእስር ዘመናቸውን በውብ ለዛ፣ በዝርዝርና በታማኝነት የYሚተዝቱበትን ይህንን “ትዝታ” የተሰኘውን መጽኀፋቸውን ገልጠን፣ ምእራፍ 16ን እናቃምሳችኋለን፡፡
በዛሬው አትሮኖስ የሀዲስ አለማየሁን ትዝታ የሚያቀርብልን፣ በመድረክ፣ በቴሌቪዥንና በፊልም ትወናዎቹ በሚገባ የምታውቁት አንጋፋው ተዋናይ ኪሮስ ሀይለስላሴ ነው፡፡ ኪሮስ እስቱድዮአችን ተገኝቶ ከአትሮኖሳውያን ጋር ይህንን መጽኀፍ ለመካፈል ስለፈቀደ ከልብ እናመሰግነዋለን፡፡
ዝግጅቶቻችንን ሼርና ላይክ እንዲሁም ሰብስክራይብ ማድረግ አትዘንጉ፡፡ ከርእዮት ጋር ሁኑና አትርፋችሁ ተዝናኑ፡፡
#ትዝታ #ሀዲስአለማየሁ #አርበኞች #HadisAlemayehu #EthiopianLiterature #FikerEskemekabr #Tizta #ClassicNovel #Memory

Комментарии

Информация по комментариям в разработке