የዓለም ዜና፤ የግንቦት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞ

Описание к видео የዓለም ዜና፤ የግንቦት 5 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ሰኞ

DW Amharic አርሰተ ዜናዎች
-በኬንያ በተከሰተዉ ዝናብና ጎርፍ ሳብያ ለሁለት ሳምንት ተዘግተዉ የነበሩት ት/ ቤቶች ዛሬ ተከፈቱ። በጎርፍ አደጋዉ በትንሹ 277 ሰዎች ሞተዋል።
-እስራኤል በጋዛ ከሃማስ ጋር በምታካሂደዉ ጦርነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች ስትል ደቡብ አፍሪቃ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ ያቀረበችውን ክስ ግብፅ በይፋ ለመደገፍ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች።
-በአውሮጳና በአሜሪካ የሚኖሩ ከቻይናና ከሆንግ ኮንግ የመጡ ተማሪዎች በቤጂንጉ መንግስት ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን አምነስቲ አጋለጠ።
-በጀርመን በዉጭ ተዋናዮች የሚደርሰዉ የሳይበር ጥቃት መጨመሩን የጀርመን ባለስልጣናት ዛሬ ገለፁ።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке