ክርስቲያናዊ ጋብቻ ክፍል (1) - በመጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

Описание к видео ክርስቲያናዊ ጋብቻ ክፍል (1) - በመጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ

የጋብቻ ሕይወት፣ የሰው ልጅ ፈቃደ ሥጋዉን እንዲፈጽምበት፣ ዘሩን እንዲተካበትና እንዲረዳዳበት እግዚአብሔር አምላካችን ያዘጋጀው ሥርዓት ነው፡፡ በስእለት ወይም በሌላ ምክንያት ለመመንኰስ ከወሰኑ አባቶችና እናቶች በቀር ለሰብአዊ ፍጡር ዂሉ ጋብቻ አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ወይ በጋብቻ አለዚያም በድንግልና መጽናት እንጂ እንዲሁ እየዘሞቱ መኖር ኀጢአት ነው፡፡ ትዳር ለመመሥረት ወስነን ዝግጅት ላይ የምንገኝ ምእመናንም የጋብቻ መሥፈርታችን ሃይማኖትን፣ ክርስቲያናዊ ምግባርንና መልካም ሰብእናን መሠረት ያደረገ ሊኾን ይገባዋል፡፡ ሀብትን፣ ዝናንና ውበትን ምክንያት አድርጎ መተጫጨት መጨረሻው አያምርምና፡፡ እነዚህ ቁሳውያን መሥፈርቶች ከጊዜ በኋላ ሲጠፉ ጋብቻም አብሮ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ስለዚህም መሥፈርታችን ከሃይማኖትና ከምግባር ጋር የተገናኘ መኾን ይኖርበታል፡፡ እነዚህ ከተሟሉ ሀብቱና ሌላው ጉዳይ በጊዜ ሒደትና በጥረት የሚመጣ ነውና፡፡

Комментарии

Информация по комментариям в разработке