ጥሩ ሚስት መሆን የምትችይባቸው 10 መንገዶች | The way how to become a good wife

Описание к видео ጥሩ ሚስት መሆን የምትችይባቸው 10 መንገዶች | The way how to become a good wife

1. አፍቃሪ ልትሆን ይገባል፦
ይህ ማለት ፍቅር ሰጪ ሚስት ልትሆኚ ይገባል ማለት ነው። ከጥሩ ሚስት ባህሪያት ውስጥ አንዱ ለባሏ ፍቅርን እንዴት ማሳየት እንዳለባት ማወቋ ነው። አፍቃሪ መሆን እጅግ ጠቃሚ ነው። ብዙውን ጊዜ ስሜታችንን ወደ ጎን እንገፋለን እና በዕለት ተዕለት ፣ ስራዎች ወይም ሌሎች ነገሮች ላይ እናተኩራለን። በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ለእነሱ ምን ያህል እንደምንጨነቅ ማሳየት ይኖርብናል። እናም ለባልሽ በፍፁም ስሜትሽን መደበቅ የለብሽም ። እናም ሁሌም እንደምቶጂው ግለጪለት ወይም ንገሪው። ቃላት እጅግ ሃይል አላቸውና። ያንቺን ስሜት ማወቁ ደግሞ ሁሌም ባንቺ እንዲሳብ እና እንዲገዛ ያደርገዋል።
2. እሱን ልትረጂ ይገባል
አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳ ባልሽን ለመረዳት መሞከር ይኖርብሻል። ምንም እንኳን አንቺን በሚያሳምም ሁኔታውን መታገስ ይኖርብሻል። መረዳት መቻል በጣም አስፈላጊ ባህሪ ነው. ማናችንም ብንሆን ፍጹም አይደለንም, እና ባሎችም እንዲሁ አይደሉም። እናም የባለቤትሽን ድክመቶችና ጉድለቶች መረዳት ይኖርብሻል።
እስቲ የብዙዎችን ባለትዳር ሲጣሉ የሚያነሱትን ምክንያት ስሙአቸው። አትረዳኝም !! ምንም ባደርግ ልትረዳኝ አትችልም ሲል ነው ምትሰሙት። እናም ባለመረዳት ብዙ ነገር ይበላሻል። ጥል የሚነሳው የውስጥ ስሜቶችን ባለመረዳት ምክንያት ነው። ዛሬ ስሜቱ ጥሩ ካልሆነ ስሜቱን ተረጅው። አረፍት ከፈለገ አሊያም እስኪረጋጋ ድረስ ጊዜ ስጪው።ከዛም ከስሜቱ ሲነቃ ወይም ንዴቱ እና ብስጭቱ ሲለቀው መልሶ በፍፁም ፍቅር ያናግርሻል። እና የሰውን ስሜት መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው።
3. ክብር ስጪው
መከባበር እና ፍቅር ሁለቱም ባለትዳሮች አስፈላጊ አስፈላጊ ነው። አክብሮት አድናቆት እና ክብርን ያሳያል። በተለይ በውጪ በምትሆኑበት ጊዜ ባለቤትሽን ክብር ስጪው። በሌሎች ፊት ባልሽን አለማክበር ባልሽን እንዲያፍር፣ ሼም እንዲይዘው፣ እንዲናደድ ወይም በራስ መተማመኑን እንዲያጣ ያደርገዋል። ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት ይባላል። ይህም አባባል የሚያሳየው ሚስቱ ኩራቱ እንደሆነች ነው። መተማመኛው ማለት ነው። ስለዚህም ይህን እንዲያስብ ልታደርጊው ይገባል። ባንቺ አክብሮት ልበ ሙሉነት ይሰማዋል። ያገባሽው ባል ምንም ሊሆን ይችላል ። ጥቁር ቀይ ፣ወፍራም ፣አጭር ረጅም ወይንም ደግሞ አካል ጉዳተኛ ሊሆንም ይችላል ። ነገር ግን ምንም ይሁን ምን ፍቅር ስትሰጪው በቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጪም እኩል ፍቅር ልትሰጪው የገበል። አክብሮትሽ በሌሎችም ፊት እኩል ሊሆን ይገባል። ይህ የሚያሳየው የፍቅርን ፅናት እና ሃያልነት ነው። እናም ባንቺ ፍቅር ጠንካራ ይሆናል።
4. ፍላጎትሽን ንገሪው፦
አንዲት ሴት ጥሩ ሚስት መሆን የምትችልበት መንገድ ፍላጎቶቿን እና ምኞቶቿን ለባሏ ማሳወቅ ስትችል ነው። ለሱ ፍላጎትሽን ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ በዚህም ምክንያት ባልሽ ስላንቺ ግራ መጋባት ፣ ወይም ብስጭት ሊሰማው ይችላል። እናም ምን እንደሚሰማሽ ፣ ፍላጎትሽን በግልፅ ንገሪው ይህ ማለት በየ እለት ተለት ኑሮአችሁ ውስጥ ደስታሽንም ፣ ቢሆን መከፋትሽን ሳትደብቂ ንገሪው። ስሜን መደበቅ ጥሩ አይደለም ።አንዳንድ ጊዜ ደግሞ መነጋገር የሚኖርባቹ ጉዳዮች ይኖራሉ። በዚህ ጊዜ ታድያ ከሱ ምን እንደምትፈልጊ ወይም የትኛው ባህሪው እንዳልተመቸሽ በግልፅ እና በተረጋጋ አንደበት አውሪው። ያንጊዜ እሱም ካንቺ ይማራል። ወደፊት እሱም ስሜቱን እና ፍላጎቱን አይደብቅሽም። ማድረግ ያለብሽ ነገር አንቺ ለሱ ግልፅ ሆነሽ እሱም ካንቺ ግልፅነት እንደመማር ማድረግ ይኖርብሻል።

5. ትናንሽ ነገሮችን ተወት አድርጊ
ይህ በግ ግጭት ጊዜ ወይም በንግግር ጊዜ ማድረግ ያለብሽ ነገር ነው። ሁሉም ትዳር ፍፁም አይደለም ።ምንም ፍቅር ቢኖር መጣላት የግድ ነው። ጥል እንኳን ባይፈጠር አለመስማማት ይኖራል። ታድያም ጥሉ ሳይፈጠር በፊት ለጥሉ መነሻ የሆነው ነገር ዋነኛው ነገር ነው። አንዳንድ ጥሎች ወይም አለመግባባቶች ምክንያታቸው የማይረባ ነገር ነው። በዚህ ጊዜ ታድያ ይህን የማይረባ ወይም ትንሽ ነገር አግዝፈን ማየት የለብንም። የጥል ምክንያቱ ትልቅ ቢሆንም እንኳን ማቅለል እንጂ ይበልጥ ማተለቅ የለብንም። እናም በግጭት ጊዜ እሱ ይበልጥ ተናዶ ቢሆን አንቺ ደግሞ በልኩ በረድ ልትይ ይገባል። ምክንያቱም ልክ እንደ ድንጋይ ሲጋጭ እሳት እንደሚፈጥረው ሁሉ ሁለታችሁም በሃይል በመነጋገር እሳት መፍጠር የለባችሁም። ቢያንሱ አንዱ አካል ሊበርድ ይገባል።ለምሳሌ ዛሬ ለምን ምሳ አልሰራሽም ብሎ ሊበሳጭብሽ ይችላል። በዚህ ጊዜ ታድያ አንቺ በተረጋጋ አንደበት ለምን እንዳልሰራሽ ምክንያትሽን አስረጂው። የህ ብስጭቱን ያበርድለታል። እንዲረዳሽም ያደርገዋል።

6. ወሲብ
ወሲብ የአብዛኞቹ ትዳሮች አስፈላጊ አካል ነው፣ እና ለሁለቱም ጥንዶች አስፈላጊ ነገር ነው። ከየትኛውም ግንኙነት በላይ ወሲብ ስሜትን በሃይል ይገልፃል። ባልሽን አስተውይው ወሲብ በመኝታ ቤት ውስጥ ባል የሚፈልገው ነገር ነው። እናም ይህን ስሜትን መለዋወጫ መንገድ መዘንጋት የለብሽም።
7. ቤተሰቡን አክባሪ እና ተንከባካቢ ሁኚለት
ይህን ነገር ሁለቱም ባለትዳሮች ማድረግ ያለባቸው ነገር ነው።ቤተሰቦቹን የምታከብሪለት ከሆነ በበተለይ እናት እና አባቱን የምታከብሪለት ከሆነ እጅግ ላንቺ ፍቅር እንዲኖረው ያደርጋል።
እዚህ ነገር ላይ በተለይ ሁለታችሁም ባለትዳሮች ተጠንቀቁ ። ይህ ማሰሪየም መንገድ ነው። ምን አልባት እሱ ላንቺ ደንታ ባይኖረውና ፍቅር ባይሰማውም እንኳን ወይም ብትጣሉ እንኳን አንቺ ለሱ ቤተሰብ ፍቅር ካለሽ በፍፁም የሱ ወገን አይሆኑም። እናም ትዳራችሁን ለማዳን ይጥራሉ። እንድትፋቱ አይፈልጉም። እናም ይህንን ማድረግ ይኖርብሻል
8. ትርፍ ጊዜሽን ከሱ ጋር አሳልፊ ወይም ጊዜ ስጪው
ለምሳሌ በቤት ውስጥ ለመሆን ይችላል፣ ወይም ወክ በማድረግም ሊሆን ይችላ፣ ወይም በመዝናናትም ይሁን ብቻ ጊዜ ሊኖርሽ ይገባል። ሁሌም ልክ እንደ አዲስ ፍቅረኛ መሆን ይኖርባችኋል። ይህን የምታደርጉበት መንገድ ደግሞ ጊዜ በመሰጣጣት ነው። እሱም ላንቺ አንቺም ለሱ ጊዜ በመስጠት ፍቅርን ማደስ እና ውብ ማድረግ ይቻላል።
9. ሳቂታ እና ተጫዋች ሁኚ
ይህ በተለይ በቤት ውስጥ ስትሆኑ ሁሌም ደስተኛ ሳቂታ ልቶኚ ይገባል። ቀልድ እንኳን ባይወድ እንዲወድ አድርጊው። ይህን ማድረግሽ በተለይ በተደበረበት ጊዜ ወይም ስሜቱ ጥሩ ባልሆነበት ጊዜ ባንቺ ሳቅ ሁሉን እንዲረሳ ያደርገዋል። እነም ፈገግታሽ ሁሌም በልቡ እንዲቀር እና አንቺን እንዲያስብ ያደርገዋል። ሳቅ ሁሌም የደስታ እና የፍቅር ምንጭ ነው። ሰው ተጣልቶ በፍፁም ሊስቅ አይችልም። እየሳቀም አይጣላም። ስለዚህ ሳቅ ንና ጨዋታ ጥልን ማባረሪያ መሳሪያ ነውው ማለት ነው። እናም ይህን መሳሪያ ከትዳር ህይወት ውስጥ ልታጡት አይገባም።
10. መልካም አንደበት ይኑርሽ
ይህ እጅግ ዋነኛው ነገር ነው። መልካም አንደበት እና የተረጋጋ ሰው መሆን ይኖርብሻል።
መልካም አንደበት ስንል አንደበተ ርቱዕ እንደማሐት ነው። ሁሌም ንግግርሽ የተረጋጋ ይሁን ሃይለቃል አይኑረው። ቁጣ እና ጩኸት የረብሻ እንጂ የሰላም ምልክት አይደለም። አንደበትሽ ሰላማዊ ሊሆን ይገባል። ሁሌም ቢሆን በትህትና አነጋግሪው ። በጥልም ጊዜ ቢሆን ሰላምም ብትሆኑ አንደበት ትሁት ሊሆን ይገባል። ትህትና ቁጣና ጥልን ያበርዳል።

#youtube
#pschology
#ትዳር

Комментарии

Информация по комментариям в разработке