ለመጀመሪያ ጊዜ የነብዩ ሄኖክ እና የዲሜጥሮስ የቀን አቆጣጠር ልዩነት ለተጠየቁት ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ

Описание к видео ለመጀመሪያ ጊዜ የነብዩ ሄኖክ እና የዲሜጥሮስ የቀን አቆጣጠር ልዩነት ለተጠየቁት ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ

ለመጀመሪያ ጊዜ የነብዩ ሄኖክ እና የዲሜጥሮስ የቀን አቆጣጠር ልዩነት
ለተጠየቁት ጥያቄዎች የተሰጠ ምላሽ
ስሙንም ሄኖክ አለው፤ እርሱም አስቀድሞ በምድር ላይ ከተወለዱ ሰዎች ይልቅ መጽሐፍንና ትምህርትን ጥበብንም ተማረ።
ሰዎች በየወራቸው እንደ ሥርዐታቸው የዘመናትን ጊዜ ያውቁ ዘንድ እንደ ወራቸው ሥርዐት የሰማይን ምልክት በመጽሐፍ ጻፈ። እርሱም አስቀድሞ ምስክርን ጻፈ። ለሰው ልጆችም በየወገናቸው አሰማባቸው፤ እርሱም በሱባዔ የሚቈጠሩ ቍጥሮችን ተናገረ፤ የዘመኖችንም ቀኖች እርሱ ተናገረ፤ ወሮችንም ሠራ፤ እኛም እንደ ነገርነው ዘመኖችን የሚቈጥሩባቸው ሱባዔዎችን ተናገረ። የተደረገውንና ገና የሚደረገውን ቍጥር ፍርድ እስከሚደረግበት ቀን ድረስ በዘመናቸው በሰው ልጆች ላይ የሆነውንና የሚሆነውን ሌሊት በራእይ አየ፤ ዐወቀም። ለምስክርነትም ጻፈው። በሰው ልጆችም ሁሉ ላይ በየትውልዳቸው በምድር ምስክር ሊሆን አኖረው።
በዐሥራ ሁለተኛውም ኢዮቤልዩ በሰባተኛው ሱባዔ ሚስት አገባ። ስምዋም አድኒ ይባላል፥ ይህችውም የዳንኤል ልጅ የአባቱ እኅት ልጅ ናት፤ ለእርሱም ሚስት ልትሆነው አገባት። በዚህም ሱባዔ በስድስተኛው ዓመት ወንድ ልጅ ወለደችለት። ስሙንም ማቱሳላ ብሎ ጠራው። ከዚህም በኋላ ከአምላክ መላእክት ጋር ስድስት የኢዮቤላት ዘመኖችን ኖረ። በምድርም ያለውን ሁሉ፥ በሰማይም ያለውን የፀሓይን ሥልጣን አሳዩት። ሁሉንም ጻፈ። ከሰው ልጆች ጋር በኀጢአት አንድ ሆነው በደል በሠሩት በትጉሃንም አዳኘባቸው። እነዚህ ከሰው ልጆች ጋር ይረክሱ ዘንድ፥ በግብርም አንድ ይሆኑ ዘንድ ጀምረዋልና፤ ሄኖክም በሁሉ ላይ አዳኘባቸው።
ከሰው ልጆችም መካከል ተወሰደ። ለጌትነትና ለክብርም ወደ ኤዶም ገነት ወሰድነው፤ እነሆ፥ እርሱ በዚያ የዘለዓለም ቅጣትንና ቍርጥ ፍርድን ፥ የአዳምንም ልጆች ኀጢአት ሁሉ ይጽፋል። ለሰው ሁሉ ልጅ ያሰማዘንድ፥ ቍርጥ ፍርድም እስከሚደረግባት ቀን ድረስ የሰውን ሁሉ ሥራ ይናገር ዘንድ እርሱ ለምልክት ተሰጥቶአልና ስለ እርሱ በኤዶም ምድር ላይ ሁሉ የጥፋት ውኃን አወጣ። እርሱም እግዚአብሔር የሚቀበለውን ዕጣን በሠርክ አስቀድሞ ዕጣን በሚቃጠልበት በተቀደሰው ተራራ ላይ ዐጠነ፤ ለእግዚአብሔር በምድር አራት ቦታዎች አሉትና፥ እነዚህም የኤዶም ገነትና ደብረ ዘይት፥ ይህም ዛሬ አንተ በውስጡ ያለህበት ደብረ ሲናና ምድርን ለማንጻት ነሚደረግ በአዲስ ፍጥረት የሚነጻ ደብረጽዮን ናቸው።

Комментарии

Информация по комментариям в разработке