/ክፍል ሁለት/ ለመጀመሪያ ጊዜ የነብዩ ሄኖክ እና የዲሜጥሮስ የቀን አቆጣጠር ልዩነት

Описание к видео /ክፍል ሁለት/ ለመጀመሪያ ጊዜ የነብዩ ሄኖክ እና የዲሜጥሮስ የቀን አቆጣጠር ልዩነት

ለመጀመሪያ ጊዜ የነብዩ ሄኖክ
እና
የዲሜጥሮስ የቀን አቆጣጠር ልዩነት
ሁሉም ሊመለከተው የሚገባ
በተለይ የተዋህዶ ልጆች።
ክፍል ሁለት
በነብዩ ሄኖክ ዘመን አቆጣጠር
ነሐሴ ፳፩ ፳፻፲፯ ዓ.ም

እግዚአብሔርም አለ በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ በቀንና በሌሊትም ይሌዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ ለምልክቶች ለዘመናት ለዕለታት ለዓነታትም ይሁኑ።
ዘፍ ፩፥፲፬ (አንድ፥ዐሥራ አራት)
መርከቢቱም በሰባተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።
ዘፍ ፷፥፬ (ሥምንት፥አራት)
እግዚአብሔር በግብፅ ሀገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ይህ ወር የወሮች መጀመሪያ ይሁናችሁ የአመቱም መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ። ለእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ተናገሩ፤
ዘጻ ፲፪፥፩-፫ (ዐሥራ ሁለት፥አንድ-ሦስት)
በሰባተኛውም ወር ከወሩ በመገመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች እለት የቀደሰች ናት ፤የተግባር ሥራ አትሥሩባት ምልክት ያለባት ቀን ትሁንላችሁ።
ዘኁ ፳፰፥፩
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ፡- በሰባተኛውም ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት በመለከት ድምፅ መታሰቢያ የተቀደሰች ጉባኤ ትሁንላችሁ የተግባር ሥራ ሁሉ አታድርጉባት ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ።
ዘሌ ፳፫፥፳፬-፳፭ (ሃያ ሦስት፥ሃያ አራት - ሃያ አመስት)
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ፡-በዚህ በሰባተኛው ወር ከአሥራ አምስተኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእግዚአብሔር የዳስ በዓል ይሆናል ።
ዘሌ ፳፫፥፴፬ (ሃያ ሦስት፥ሠላሳ አራት)
በሰባተኛውም ወር ከወሩ የመጀመሪያዋ ቀን ለእናንተ ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት የተግባር ሥራ ሁሉ አትሥሩባት ፤
ዘኁ ፳፱፥፩ (ሃያ ዘጠኝ፥አንድ)
በሰባተኛውም ወር ዐሥራ አምስተኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ ፤
ዘኁ ፳፱፥ ፲፪(ሃያ ዘጠኝ፥ዐሥራ ሁለት)
በአራተኛውም ወር ሰፊ የሆነ የጥልቁ ምንጮች ተገቱ። የሰማዩም ሻሻቴ ተገታ። በሰባተኛውም ወር መባቻ የምድሩ ጥልቅ አፍ ሁሉ ተከፈተ። ውኃዎችም ወደ ታችኛዪቱ ጥልቅ ይወርዱ ጀመር።
ኩፋ ፮፥፴፫ (ሥድስት፥ሠላሳ ሦስት)
ስለዚህም በዘመኑ ሁሉ ለአዲስ ኪዳን በየአመቱ አንድ ጊዜ በዚህ ወር የሱባዔያትን በዓል የሚያደርጉ ይሆሁ ዘንድ ተሠራ፤. . .
. . . በሰማይ ጽላት ተፃፈ። . . .ይህችም በዓል ከፍጥረት ቀን ጀምሮ እስከ ኖኅ ዘመን ድረስ በሰማይ ስትሠራ ኖረች፤. . .
ኖኅና ልጆቹም ኖኅ እስከሚሞትባት ቀን ድረስ ሰባት ኢዮቤልዩና አንድ የዓመት ሱባዔ ጠበቁት ። ኖኅ ከሞተ በኋላም እስከ አብርሃም ዘመን ድረስ ልጆቹ ሕግን አፈረሱ፤ ነገር ግን አብርሃም ብቻ ሕግን ጠበቀ፤ይስሐቅና ያዕቆብም እስከ አንተ ዘመን ድረስ ጠበቁት። በዘመንህም በዚህ ተራራ እስካድሳቸው ድረስ የእስራኤን ልጆች ሕግን ዘነጉ። . . .
፳፪ በመጀመሪያው ወር መባቻ በአራተኛውም ወር መባቻ፣ በሰባተኛው ወር መባቻ፣ በዐሥረኛውም ወር መባቻ እነዚህ የመታሰቢያ ቀኖች ናቸው፤በአራቱም ክፍለ ዓመት፥. . .
፳፬ በመጀመሪያው ወር መባቻ ለራሱ መርከብን ይሰራ ዘንድ ተነገረው፣ በእርስዋም ምድር ደረቀች መስኮቱንም ከፍቶ ምድር አየ በአራተኛው ወር መባቻ የታችኛው የጥልቁ ምንጭ አግ ተዘጋ፡፡ የሰማዩም ሾሾቴ ተገታ፡፡ በሰባተኛው ወር መባቻ በምድር ያለ የምንጭ ውሃ ጉድጎድ ሁሉ ተከፈተ፤ ውሃዎችም ወደ ታችኛው ጥልቅ ይወርዱ ጀመር፡፡
በዐሥረኛውም ወር መባቻ የተራሮች ራሶች ታዩ ኖኅም ደስ አለው፤ ስለዚህ እነሱን እስከ ዘለዓለም ድረስ ለመታሰቢያ በዓላት አደረጋቸው፡፡
. . .እነዚህ እንዲህ የተሰሩ ናቸው፤ወደ ሰማይ ጽላትም ያወጡአቸዋል።
. . .ከእነርሱም እያንዳንድዋ ከዚችኛዪቱ እስከዚያችኛዪቱ መታሰቢያ፥ ከመጀመሪያዪቱ እስከ ሁለተኛዪቱ፥ ከሁለተኛዪቱ እስከ ሦስተኛዪቱ፥ ከሦስተኛዪቱ እስከ አራተኛዪቱ ዐሥራ ሦስት ሱባዔ ናቸው። . . .
. . . ፳፱ የትህዛዛት ቀኖች ሁሉ ቀን የሚቈጠርባቸው አምሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናሉ፡፡ፍጹም የሆነ ዓመቱ ሁሉ እንዲህ ተቀርፆና ተቈጥሮ በሰማይ ጽላት ተጻፈ፡፡ . . .
. . . አንድ ዓመትና ሁለት ዓመት ሦስት ዓመትም መተላለፍ የለውም።. . .
. . . አንተም የእስራኤልን ልጆች በዓመቱ በዚህ ቍጥር ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀንን ይጠብቁ ዘንድ አዘዛቸው፣ፍጹም ዓመትም ይሆናል፡፡. . .
. . .ጊዜውንም በቀኑና ከበዓሉ አሳልፈው አያጥፋ፡፡ ሁሉ እንደ ምስክርነታቸው ይደርስባቸዋልና ቀኑን አያስቀሩ ፤በዓሉንም አያጥፉ፡፡ ቢተላለፋአቸውም፣ እንደ እርሱ ትእዛዝም ባያደርጉአቸውም ያን ጊዜ ሁሉም ጊዜዋቻቸውን ያጠፋሉ፡፡ ኣመታትም ከዚህ ወደ ዚያ ይለዋወጣሉ ፣ ጊዜያትም ይጠፋሉ፣ ዓመታቱም ይለዋወጣሉ፣ ሥርዐታቸውም ያፈርሳሉ፤
. . . የእሰራኤልም ልጆች ሁሉ ይዘነጋሉ፡፡ የዓመታትንም መንገድ አያገኑም፤ መባቻውን ይረሳሉ፤ ጊዜውንና ሱባዔውን፥ የዘመኑንም ሥርዐት ሁሉ ያፈርሳሉ፡፡ እኔ አውቃለሁና፥ እንግዲህ ወዲህ እኔ እነግርሃለው፤ እንዲህ ያለ መጽሐፍ በፊቴ ተጽፎአልና፥ የምነግርህ ከልቤ አይደለም፤ ከሳቱ በኃላ አእምሮአቸውንም ካጡ በኃላ የቃል ኪዳኑን በዓል እንዳይረሱ፥ በአሕዛብ በዓላትም እንዳይሄዱ የዘመኑ አከፋፈል በሰማይ ጽላት ተጻፈ፡፡
፴፬ እርስዋ ጊዜያትን ትለውጣለችና፣ ከዓመታትም ለዓመት ዐሥር ቀን ትቀድማለችና፣ በጨረቃ አጎዳደል ጨረቃን የሚመለከተ ይሆናሉ፡፡
. . . ስለዚህ ሥርዐትን ከለወጡ በኃላ ዓመታት ይመጡላቸዋል፣ ምስክር የምትሆን ቀንንም የተናቀች ያደርጋሉ፡፡ . . .
የረከሰችውንም ቀን በዓል ያደርጋሉ፣ ሁሉንም ይቀላቅላሉ፣ የተቀደሱትን ቀናት የረከሱ፣ የረከሱትንም ቀናት ለቅድስና ያደርጋሉ፣ . . . . . . . ወራቶችንና ሱባዔዎችን፣ በዓላቱንና ኢዮቤላቱን ይስታሉና፡፡ ስለዚህም እኔ አዝዝሃለው፤ልጆችህ አንተ ከሞትህ በኋላ ሦስት መቶ ስድሳ አራቱን ቀን ብቻ ዓመትን እንዳያደርጉ ሥርዐትን ይለውጣሉና ታዳኝባቸው ዘንድ አዳኝብሃለው። ስለዚህም የወሩን መባቻና ሱባዔውን፣ ጊዜውንና በዓላቱን ይስታሉ፤ ከሰው ሁሉ ጋር ብርንዶውን ሁሉ ይበላሉ
ኩፋ ፯፥፲፮-፴፯ (ሠባት፥ዐሥራሰባት-ሠላሳ ሰባት)
ዓመቱም በሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀን ይፈጸማል፤ ነገሩም እወነት ነው፥ የተጻፈውም ቍጥሩ የተጠነቀቀ ነው።
ሄኖ ፳፰፥፲፩ (ሃያ ስምንት - አስራ አንድ)

Комментарии

Информация по комментариям в разработке