Oven Baked Potatoes የድንች ጥብስ

Описание к видео Oven Baked Potatoes የድንች ጥብስ

ድንች ጥብሱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና የአበሳሰል መመሪያ

ግብዓቶች፡
በደንብ የታጠበ ድንች
እርጥብ የሮዝሜሪ ቅጠል
እርጥብ የበሶብላ ቅጠል
እርጥብ የጦስኝ ቅጠል

ድንቹን ለመቀቀል
የድንቹን አሰር በውሃ አንዴ ለቅለቅ ካደረጋችሁት በሃላ
ውሃ ውስጥ ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ጨው፣ እርጥብ የሮዝሜሪ ቅጠል፣ እርጥብ የበሶ ብላ ቅጠል እና 4 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ጨምራችሁ መቀቀል

የመቀቀያ ሰዓት ፡
በከፍተኛ ሙቀት ለ10 ደቂቃ መቀቀል
ድንቹን በቢላ ስትወጉት በቀላሉ የማይወጋ/የማይፈረከስ ከሆነ ለተጨማሪ 2 ደቂቃዎች መቀቀል

የአበሳሰል መመሪያ፡
1 የሾርባ ማንኪያ የገበታ/የአትክለት ቂቤ እና 3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት የመጋገሪያ ትሪ ላይ አድርጋችሁ ምድጃ ውስጥ በ200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ከ3-5 ደቂቃ ማጋል
ከጋለ በሃላ አውጥታችሁ ድንቹን ጨምራችሁ በቅባቱ መለወስ
ደረቅ የጦስኝ ቅጠል መነስነስ
ወደ መጋገሪያ ምድጃው መልሳችሁ ታስገቡ እና ለተጨማሪ 10 ደቂቃ ማብሰል እነ ማውጣት
አሁንም መልሳችሁ ድንቹን ከቅባቱ ጋር በደንብ መለወስ እና መልሶ ወደ መጋገሪያ ምድጃው ታስገቡና ለ20 ደቂቃ በደንብ መጥበስ እና ማውጣት
ካወጣችሁት በሃላ ድንቹን ከቅባቱ ጋር በድንብ ትለውሱት እና እርጥብ ቅመሙን ፣ አንድ ቁንጥር ጨው እና 1 የቡና ማንኪያ የነጭ ሽንኩርት ዱቀት ጨምራችሁ መልሳችሁ ወደ ምድጃው አስገብታችሁ ለተጨማሪ 15 ደቂቃ በደንብ አድርጋችሁ ትጠብሱታላችሁ

የማባያ ስልስ አማራጮች
ቆጭቆጫ
ኬች አፕ
ማዮኔዝ እና ኬች አፕ
ተሂኒ ስልስ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке