#AASTU

Описание к видео #AASTU

#AASTU #Info


አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን በተመለከተ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ

✍️✍️✍️✍️✍️
[ይህን መረጃ ያጋራው ዩንቨርሲቲው ነው]

1. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ(አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ) እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (አ.አ.ዩ) አንድ ናቸው ?

⚡️አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፡፡ ሁለቱም የተለያዩ ተቋማት ናቸው፡ ፡ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2003 ዓ.ም ተቋቁሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የትምህርት መስኮች ምሩቃንን እያፈራ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ነው፡ ፡

2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የት ይገኛል ?

⚡️አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ የሚገኘውም አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 በተለምዶ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ጎን

3. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በምን ይለያል?

⚡️አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚለይባቸው ዋና ዋና ነጥቦች ?

⚡️ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የትምህርት እድል ተሰጥቷቸው የማስተርስ እና የመጀመሪያ ዲግሪ(fast-track) እድል ተጠቃሚ ማድረጉ፡ ፡

⚡️የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርቶች ብቻ የሚሰጡበት ትምህርቶች ብቻ የሚሰጡበት መሆኑ

⚡️ዘመናዊ እና የተሟላ የላብራቶሪ ግብአቶች የተሟሉለት እና የአይሲቲ መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ የተዘረጉለት በመሆኑ

⚡️ተማሪዎች ከኢንዱስትሪዎች የጠበቀ ትስስር እንዲኖራቸው በማድረግ የተግባር ልምምድ እና እውቀት የሚያገኙበት ብሎም የሚቀጠሩበትን ስልት ነድፎ የሚሰራ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ

⚡️የሳይንስ ተማሪዎች ሶስተኛ አመት ላይ የምህንድስና ተማሪዎች አራተኛ አመት ላይ ጥምር የምህንድስና (integrated engineering project ) ጥምር የሳይንስ (integrated science project) የስርዓተ -ትምህርቱ አካል አድርጎ የሚሰጥ ብቸኛ ተቋም መሆኑ

⚡️በፈጠራ እና ማበልጸጊያ ማዕከል አማካኝነት የፈጠራ ውጤቶች ወደገበያ የሚገቡበትን ትስስር የፈጠረ እና ለፈጠራ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ተቋም መሆኑ፡፡

⚡️ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው በተጨማሪ የልዩ ልዩ ክህሎቶች ባለቤት እንዲሆኑ የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ በየሳምንቱ ረበዕ ከሰዓት ተጋባዥ እንግዶችን በመጋበዝ ለተማሪዎች ልምድ የሚያካፍሉበትን ባህል ያዳበረ ተቋም በመሆኑ፡ ፡

⚡️ለተማሪዎችን ደህንነታ እና ሰላም ሲባል በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሲሲቲቪ ካሜራ የተገጠሙለት ተቋም መሆኑ ከሌሎች ተቋማት የተለየ ያደርጉታል፡ ፡

4. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ምን ምን ናቸው?

⚡️ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ ዲግሪ 13 ፕሮገራሞችን ይሰጣል የሚሰጡ ፕሮግራሞች

➡️በምህንድስና ዘርፍ
 ⚡️አርክቴክቸር
 ⚡️ሲቪል ኢንጂነሪንግ
 ⚡️ኬሚካል ኢንጂነሪንግ
 ⚡️ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
 ⚡️ኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢነጂነሪንግ
 ⚡️ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ
 ⚡️ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ
 ⚡️ኢንቫይሮመንታል ኢንጂነሪንግ
 ⚡️ማይኒንግ ኢንጂነሪንግ

➡️በአፕላይድ በሳይንስ ዘርፍ
 ⚡️ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ
 ⚡️ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን
 ⚡️ጂኦሎጂ
 ⚡️ባዮ ቴክኖሎጂ

5. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሪሜዲያል ተማሪዎችን ይቀበላል ?

⚡️ለጊዜው አይቀበልም

6. ወደ ዩኒቨርሲቲው ለመግባት ምን ያስፈልጋል ?

⚡️በመጀመሪያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተማሪ ለመሆን ትልቅ ፍላጎት ያስፈልጋል።በመቀጠል ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች (አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ እና አ.ሳ.ቴ.ዩ) የሚሰጡትን ፈተና ማለፍ ይጠበቅባችኋል፡፡

7. ዩኒቨርሲቲ ለምዝገባ እና ለትምህርቱ ክፍያ ያስከፍላል ?

⚡️ምንም አይነት ክፍያ የለውም በቀጥታ መመዝገብ ይቻላል፡፡ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች (አ.አ.ሳ.ቴ.ዩ እና አ.ሳ.ቴ.ዩ) የሚገቡ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር የሚመድባቸው ሳይሆኑ የዩኒቨርሲቲዎችን ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

(አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ዩኒቨርሲቲ)

ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Комментарии

Информация по комментариям в разработке