how to play begena in 10 minutes

Описание к видео how to play begena in 10 minutes

አባታችን

"እግዚአብሔር ወልድ በመጣ ጊዜ ለካሣ።
"እንበለ ዘርዕ እንደ ንብና እንደ ዓሣ።"

... እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያለወንድ ዘር(እንበለ ዘርዐ ብእሲ) ፣ ያለ ሩካቤ(እንበለ ሩካቤ) በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት፤ በመንፈስ ቅዱስ በማይመረመር አምላካዊ ጥበብ እና ሰማያዊ ምሥጢር አማካኝነት አምላክን ያለ ወንድ ዘር ጸንሳ ወልዳዋለች። "...እግዚአብሔር አብ በማይመረመር ምሥጢር ያለ እናት የወለደውን ማርያም በማይመረመር በሥጋ ወለደችው።"(ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ ሊቀ ጻጻሳት፤ ሃይማኖት አበው ም ፹፭ ፥ ቁ ፴፯)

°°°
የእመቤታችን ጌታን በድንግልና ጸንሳ በድንግልና
የመውለዷ ምስጢር ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ!!
"...የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው።"(ማክሰኞ ውዳሴ ማርያም)

°°°
ከእስራኤል ፈጣሪ በቀር ሰው እንዳልገባበት ነቢዩ ሕዝቅኤል እንዳያት ደጃፍ ማኅተመ ድንግልዋ ሳይለወጥ በኅቱም ድንግልናዋ ተፀንሶ ተወለደ፤ እናንት አላዋቆች የእመቤታችን የማርያምን ፅንሷንና መውለዷን እንደ ሌሎች ሴቶች ኹሉ አታስመስሉ፤ ለእመቤታችን ለማርያም በፅንስና በወሊድ በሌሎች ሴቶች መመሰል አይገባትም፤ የእግዚአብሔር ቃልን ያለወንድ ዘር ፀነሰቺው፤ ያለ ጭንቅና ያለምጥም ወለደቺው እንጂ፤ በመውለድ ጊዜ የሚኾን ምጥ ፈጽሞ አላገኛትም፤ ስለዚኽ መፅነሷ በጣም ይደነቃል፤ የመውለዷ ምስጢር ኀይልም አይመረመርም፤ ማንም ማን ባሕርዩን የማያውቀው ርሱን ወለደችው፤ ማኅተመ ድንግልናዋም አልተለወጠም።(ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘእንዚናዙ)

°°°
"ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፡፡ ኋላ ግን ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እርሷ ግን ቅድመ ፀኒስ፣ ጊዜ ፀኒስ፣ ድኅረ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ፣ ጽንዕት ናት፡፡"(ውዳሴ ማርያም አንድምታ)

°°°
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዳግማዊ አዳም ክርስቶስን ከመፅነሷ በፊት (ቅድመ ጸኒስ)፣ በፀነሰችውም ጊዜ (ጊዜ ጸኒስ)፣ ከፀነሰችውም በኋላ (ድኅረ ጸኒስ)፤ እንዲሁም ከመውለዷ በፊት (ቅድመ ወሊድ)፣ በወለደችው ጊዜ (ጊዜ ወሊድ)፣ ከወለደችውም በኋላ (ድኅረ ወሊድ) ተፈትሖ ማኅፀን ሳያገኛት ማለትም ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ በድንግልና ጸንታ የኖረች ወትረ ድንግል ማርያም (ዘለዓለማዊት ድንግል
ማርያም) ናት።

°°°
🐠 የባሕር ዓሣ ለመራባት ሲያስብ እንስቲቱ ዓሣ እንቁላሎቿን ከባሕር ውስጥ ጥላ ስታበቃ ተባዕቱ ዓሣ የተጣሉት እንቁላሎች ላይ ጥላውን ያጠላባቸዋል እንቁላሎቹም ይቀፈቀፋሉ። (...ዓሣዎች የሚራቡት እና የሚባዙት በደመና ነው የሚሉም አባቶች አሉ።)

°°°
🐝 በተመሳሳይ መልኩ ንግሥቲቷ ንብ እንቁላሎቿን በሰም ከዳ ውስጥ ጥላ ስታበቃ ወንዴው ንብ እነዚህን እንቁላሎች በድምጹ እንዲያጩ ያደርጋቸዋል።

"...ፅንስ እንበለ ሩካቤ ከመ ንህብ ዘእምቃል ንባብ፡፡ ንብ ካውራው ድምፅ የተነሣ እንዲፀንስ እንበለ ዘርዕ ጌታን ለመፅነሷ ወዮ እንክሮ ይገባል፡፡ ንህብ አውራው ድምፅ ባሰማው ጊዜ እንበለ ዘርዕ እጭ ሠርቶ ያድራልና ከመ ንህብ አለ፡፡ ወተአነዝር እግዝእቶን ለአንህብት እንዲል።"(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

°°°
ከእነዚህ ሁለት ፍጥረታት ያለሩካቤ ዘርን የመተካት አስደናቂ ክንውን የእመቤታችን ጌታን የመጽነሷና የመውለዷ ምስጢር ይበልጥ ድንቅ እና ረቂቅ ነው። እመቤታችን ያለወንድ ዘር እና ያለ ሩካቤ በድንግልና ጸንሳ በድንግልና መድኅን ዓለምን የማስገኘቷን ድንቅ ነገር ከፍጥረታት ሁለቱን "ንብን እና ዓሣን" መርጦና ጠቅሶ ሊቁ ሲያመሠጥር "እንበለ ዘርዕ (ያለ ዘርዕ) እንደ ንብና እንደ ዓሣ" በማለት እመቤታችን ጌታን እንበለ ዘርዕ ፣እንበለ ሩካቤ መጽነሷን እና መውለዷን ገለጸ።

°°°

🔰ከእናንተ መካከል “ልደቱ በዘርዕ ያላደረገው እንበለ ዘርዕ(ያለዘርዕ) ያደረገው ስለ ምንድነው❓” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን።

🚩“ልደት ቀዳማዊ ተዐውቀ በደኃራዊ” እንዲል ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደ ተወለደ ለማጠየቅ።

🚩ሊቃውንቱ እንደሚነግሩን በዘርዕ በሩካቤ ተወልዶ ቢኾን ኖሮ መናፍቃን “ዕሩቅ ብእሲ ነው” ባሉት ነበርና ነው፡፡ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ሲያብራራው “ሰውም በኾነ ጊዜ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ አልተወለደም፤ አምላክ ሰው ኾነ እንጂ፡፡ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢኾንስ ብዙ ሰዎች በተሳሳቱ ነበር፤ አምላክ ሰው መኾኑንም ሐሰት ባደረጉት ነበር” ይላል። (ሃይማኖት አበው ም ፷፡ ቁ፲፱)

... ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም “እንደ እኔስ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢኾን ብዙ ሰዎች ዕሩቅ ብእሲ ባሉት ነበር፤ አምላክነቱንም በካዱት ነበር” ይላል።(ሃይማኖት አበው ም ፷፮፡ቁ ፴፪)

°°°

🔰አሁንም ከእናንተ መካከል“ያውስ ቢሆን ተፈትሖ ካላት ያላደረገው፣ ተፈትሖ ከሌላት ያደረገው ስለ ምንድነው❓” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን።

🚩አንደኛ “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች” ተብሎ የተነገረውን ትንቢት (ኢሳ.፯፡፲፬) ለመፈጸም ሲኾን።

🚩ኹለተኛው ደግሞ ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፤ ይኸውም

❇️ አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል (ዘፍ.፩፥ ፳፮) ፤ ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል። (ሕዝ.፵፬፥፩)
❇️ሔዋን በኅቱም ገቦ (ጐን) ተገኝታለች (ዘፍ.፪፥፳፩) ፤ ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል፡፡
❇️ቤዛ ይሥሐቅ የሚኾን በግዕ ከኅቱም ጉንድ ተገኝቷል (ዘፍ.፳፪፡፲፫) ፤ ቤዛ ዓለም ክርስቶስም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል፡፡
❇️ጽምዐ እስራኤልን ያበረደ ውሃ ከኅቱም እብን (ዐለት) ተገኝቷል (ዘጸ.፲፯፥፮) ፤ ጽምዐ ነፍሳትን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡
❇️ጽምዐ ሶምሶንን ያበረደ ውሃ በኅቱም መንሰከ አድግ (የአህያ መንጋጋ) ተገኝቷል (መሳ.፲፭፥፲፱) ፤ ጽምዐ ኃጥአንን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡

°°°
የዚህ ኹሉ ምሳሌ ፍጻሜው አንድ ነው፡፡ ይኸውም ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከመ ትኩን መራሒተ ለሃይማኖት ዐባይ - ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ" (ሃይማኖት አበው ም፷፮፥ ቁ፴፪) እንዲላት፤

°°°
እመቤታችን ጌታን ብትወልደው ማኅተመ ደንግልናዋ እንዳልተለወጠ ኹሉ እርሱም ሰው ሲኾን አምላክነቱ ላለመለመጡ ምሳሌ ነው፡፡ ዳግመኛም እርሷ “ድንግል ወእም” ስትባል መኖሯ እርሱም “አምላክ ወሰብእ” ሲባል ለመኖሩ ምሣሌ ነው፡፡

begena lesson
how to play begena
በገና
በገና ትምህርት
አባታችን መዝሙር

Комментарии

Информация по комментариям в разработке