ለእጆቻችን ፋጥነት በገና ትምህርት ክፍል 12 Begena lesson part 12

Описание к видео ለእጆቻችን ፋጥነት በገና ትምህርት ክፍል 12 Begena lesson part 12

ልበ_አምላክ_ቅዱስ_ዳዊት
🤲#ሀብተ_ፈውስ፦ በገናን እየደረደረና መዝሙር እየዘመረ ድውይን ህሙምን መፈወስና የመንፈስን ጭንቀት ማስወገድ።በዚህ በተሰጠው ሀብተ ፈውስ በገና በመምታትና መዝሙር በመዘመር ጊዜና ሰዓት እያየ በርኩስ መንፈስ ይሰቃይ የነበረ ሳኦልን ይፈውሰው እንደነበር ሁሉ ዛሬም ቢሆን በርኩስ መንፈስ ተይዘው የሚሰቃዩትን ሲፈውሳቸው ይታያል። (መዝሙረ ዳዊት አንድምታ መቅድም )

👉ቅዱስ ዳዊት በተሰጠው ሰማያዊ ጸጋ እና ሃብት መዝሙሮችን አዘጋጅቷል። ኁልቁ መዝሙሩ ፻፶ ነው። ፻፶ ውንም መዝሙር በ ፲ አርእስት በአራት ለይኩን ፣በአምስትኛ ለይበሉ ከአምስት ከፍሎታል። ምክንያቱም ለጊዜው #በአምስቱ_መጻህፍተ_ሙሴ ምሳሌ ነው ፍጻሜው ግን ከጊዜው ሳይደርስ እንደ ደረሰ ሆኖ በትንቢት ለተናገራቸው #አምስቱ_አዕማደ_ምሥጢር ምሳሌ ሆኖ ለመቆየት ነው።

👉ቅዱስ ዳዊት ፪፻፹፰ መዘምራን ካህናት ነበሩት፤ እነዚህ ፪፻፹፰ መዘምራን በ ፬ አለቆች ይመሩ ነበር፤ የአለቆቹም ስም እንደሚከተለው ነው።

👉#አሳፍ (መዝ ፡ ፹፯፣ቊ፡፵፱ ፡ቊ፡፹፩)
👉#ቆሬ (መዝ ፡ ፹፯፣ቊ፡፵፰)
👉#ኤማን
👉#ኤዶትም

👉መዝሙር ሰማንያ ስምንት (፹፰) ከላይ የተጠቀሱት ፪፻፹፰ ቱ መዘምራን በየአለቆቻቸው ከ ፬ ተከፍለው አንዱ ወገን በበገና፣ አንዱ ወገን በመሰንቆ ፣ አንዱ ወገን በከበሮ፣ አንዱ ወገን በቃጭል፣ አሥራ ሁለት አሥራ ሁለት እየሆኑ በሃያ አራቱ ጊዜያት በደብተራ ኦሪት እየተሰበሰቡ በንባብ የሚሆነውን ምስጋና በንባብ፤ በዜማ የሚዘመረውን በዜማ ይዘምሩ ነበር፤ ዳዊትም ከአደባባይ በማይውልበት፣ ነገር በማይሰማበት ጊዜ እየተገኘ ከእነርሱ ጋር በበገና ይዘምር እንደ ነበር ተጽፏል። (፩ኛ ዜና መዋዕል ፡ ም፡ ፮ ቊ: ፴፩ ፵፬) (፪ኛዜና መዋዕል ፡ ም፡ ፳፱፣ ቊ፡ ፳፭- ፴፩)(ነሕምያ ፡ ም፡ ፲፪፣ ቊ፡ ፳፰- ፵፯)



👉ለእኛም ለኢትዮጵያ ሰዎች በቀዳማዊ ምኒልክ ጊዜ ታቦተ ጽዮንና መጻሕፍተ ነቢያት ሲመጡ መዝሙረ ዳዊቱ መጥቶልናል፣ነገር ግን ንባቡ ብቻ መጥቶልናል እንጅ መዘምራኑ ይዘምሩት እንደነበረው ሆኖ የመዝሙሩ ግጥም የዜማው ጣዕም ከበገናው ተስማምቶ አልመጣንልም። ምክንያቱም ቅዱስ ዳዊት የደረሰው በቋንቋው በዕብራይስጥ ነበረ። ለእኛ ግን የመጣልን ከዕብራይስጥ ወደ ግዕዝ ተመልሶ ስለ ሆነ አንድ ንግግር ከአንድ ልሳን ወደ አንድ ልሳን ሲመለስ ንባቡ ተመዛዝኖ ቤቱ ተመጣጥኖ ሊገኝ የማይቻል በመሆኑ ይመስላል።ስለዚህም እስከ አጼ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት በበገና መደርደሩ በዜማ ስልት ከከበሮና ከጽናጽል መተባበሩ ቀርቶ በንባቡ ብቻ የሚጸለይ ጸሎት ሆኖ ኖረ ሊባል ይችላል።(መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ)





#begena #ermiasbegena #church #በገና #በገና_መዝሙር #artwork #bass #creative #handmade #ኤማንበገና #emanbegena #ermiashaylay #kebronbegena #begena #በገና #church

Комментарии

Информация по комментариям в разработке