ለካ አለህ | Yadah Choir | Apostolic Church of Ethiopia, Ayer Tena Kara

Описание к видео ለካ አለህ | Yadah Choir | Apostolic Church of Ethiopia, Ayer Tena Kara

ማንም በማያልፍበት በደረቅ ምድረበዳ
የሞት ጣርም ሲከበኝ ጉልበቴ እኔን ሲከዳ
የሀሩሩ ንዳድ በላዬ ሲበረታ
ለካ አለህ አጠገቤ ልትሆንልኝ ጥላ

ለካ አለህ ጊዜ ዘመን ሳይለውጥህ
ለካ አለህ ለዘለዓለም ህያው ነህ
ለካ አለህ በግርማ በማስፈራትህ
ለካ አለህ አጠገቤ እጆቼን ይዘህ

1ነፍሴ ህይወቴን ስትሰለቻት
ሲከበኝ ድካም ልቤን ፍርሀት
የውስጤ ሀዘን በበዛ ጊዜ
ሲሰማኝ ሸክም ሲይዘኝ ትካዜ

አንተን ሳስብህ ልቤን ደስ አለው
ስምህን ስጠራ ጭንቀቴን ረሳሁ
አንተን ሳስብህ ውስጤን ሰላም ሞላው
ኢየሱሴ ስልህ ታሪኬን ለወጥከው

2 በደልና ሀጢአቴን ሳትቆጥር
እድሜን ሰተህ ስትጨምርልኝ ቀን
ሊያዋርደኝ ሲከሰኝ ጠላቴ
ሳታፍርብኝ ስትቆም ከጎኔ
የእዳዬን ፅህፈት ስትቀደው
ደግሞ እኔን ምቆጥረኸኝ እንደ ሰው
ማልገባ ባርያህ እንኳ ልሆን
ልጅ አረከኝ ለውጠህ እኔነቴን


3 ቅርቤ ነህ/3* ከእስትንፋሴ ይልቅ የምትጠጋጋኝ ቅርቤ ነህ
እረኛዬ/3* እንደ አይኖች ብሌን የምትጠብቀኝ
ጉልበቴ ነህ/3* ስደክም ስዝልም የምታበረታኝ ጉልበቴ ነህ
ወዳጄ ነህ/3* እስከ መስቀል ድረስ በፍቅር የወደድከኝ ወዳጄ ነህ

|yadahchoir|

Комментарии

Информация по комментариям в разработке