ህመሜን ወሰደው | Yadah Choir | Apostolic Church of Ethiopia, Goro

Описание к видео ህመሜን ወሰደው | Yadah Choir | Apostolic Church of Ethiopia, Goro

ህመሜን ወሰደው

በእውነት ህመሜን ወሰደው ኢየሱስ ወሰደው
በእውነት ስቃዬን ወሰደው ጌታ ወሰደው
በእውነት ድካሜን ወሰደው ኢየሱስ ወሰደው
በእውነት ሀጥያቴን ወሰደው ጌታ ወሰደው

በመንገዴ ላይ ጣልቃ የሚገባውን
በመስቀል ስራው ጌታዬ ጠረቀው
ድሉ ታወጀ በአደባባይ
ሞቴን ሞተልኝ ሆነልኝ ሲሳይ

ይመስገን እርሱ በገናን አንሱ/2 በገናን አንሱ/2
ይመስገን ሥሙ ምስጋናን (እልልታን) አምጡ/2 ዝማሬን አምጡ

በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት እንዲያው በፀጋው ፀድቂያለው
በነብስ ተከፍሎልኝ ትልቅ ዋጋ የመንግስቱ መጠቀሚያ ሆኛለው
በሞት ፍርሀት ባርነት ታስሬ የነበርኩኝ
ዛሬ በፊቱ ልዘምር በሞቱ (በኢየሱስ) ተፈታሁኝ

ደዌ ህመምህ የታለ
መውጊያ አይሰራም መውጋትህ
ኃጥያት የታለ ብድራትህ
ሁሉም በመስቀል ተከፍሏል

ሁሉም በመስቀል ተከፍሏል
ሁሉም በኢየሱስ ተከፍሏል
ሁሉም በደሙ ተከፍሏል
ሁሉም በኢየሱስ ተከፍሏል

ከሞት መከራ የተነሳ ለእኔ ከሆነው
የክብርና የምስጋናን ዘውድ በእራሱ የጫነው
ከኃጥያት በቀር በሁሉ ተፈትኖ አልፏል
በመስቀል ስራው ፀጋው ከመጠን በልጧል

የከሳሼን ክስ ዛቻውን ሁሉ አክሽፎ
ወደ እራሱ አስጠጋኝ በፍቅር ስቦ
ከታሰርኩበት ወጣሁኝ ከሞት ፍርሀት
ከመንገዴ ላይ ጠርቆ አስወግዶት

የነፃነት አየር ልተነፍስ እስራቴን ፈቶ ነጻ አወጣኝ
በቀራኒዮ ዋጋ ተከፍሎልኝ በደሙ የተገዛው እኔ ነኝ
ነፃ የወጣሁኝ እኔ ልዘምር በአዲስ ቅኔ
ልቤን ላፍስለት በፊቱ ያርግልኝ መስዋዕቴ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке