መንፈሳዊ ውጊያና የድል ምሥጢር

Описание к видео መንፈሳዊ ውጊያና የድል ምሥጢር

የክርስትና ሕይወት የድል ሕይወት ነው። ነገር ግን ድል የሚመጣው ከውጊያና ከፍልሚያ በኋላ መሆኑ አሌ የማይባል ሐቅ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ በመስቀል ሞቱ ተጋድሎ፣ በትንሳኤው ባስመዘገበው ድል ከጨለማው ሥልጣን ድነን፣ ክፉ ከሆነው ከአሁኑ ዓለም አምልጠን የእግዚአብሔር ልጆች ሆነናል። ይህን ታላቅ መዳን ለማግኘት እሱ ተዋጋልን እንጂ እኛ አልተዋጋንም። ነገር ግን ይህንን የሕይወት ርስት ለማስጠበቅ እንድንዋጋ ጥሪ ቀርቦልናል። ውጊያ የትርፍ ጊዜ መዝናኛ አይደለም። የሞት የሽረት፣ የሕልውናና የነፃነት ጉዳይ ነው። "መጋደል" ማለት፣ ለመግደልም ሆነ ለመሞት ጨክኖ መነሳት ማለት ነው። በእኛና በዲያቢሎስ መካከል ሊታረቅ የማይችል ቅዱስ ጠላትነት አለ። እሱ እኛን ከዚህ ሕያው፣ የማይጠፋ፣ ዕድፈት የሌለበት፣ ዘላለማዊ ርስት ሊለየን የማይምሰው ጉድጓድ፣ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ምክሩን ከንቱ ለማድረግ እኛም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዣችን የሆነውን የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝ እየተቀበልን ልንዘጋጅ፣ ልንታጠቅ ይገባናል።
ይህ መልዕክት ኤፌ. 6፥10-20 ያለውን ክፍል መሠረት በማድረግ፣ በተለይም በቁጥር 10 ላይ በማተኮር በጌታና በኃይሉ ችሎት መበርታት ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ያሳየናል።
መልዕክቱ የቃሉ አገልጋይ ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን በፎር ኮርነርስ የኢትዮጲያ ወንጌላዊያን ቤተክርስቲያን ሲልቨር ስፕሪን ሜሪላንድ ያቀረበው ነው።
ተባረኩ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке