ሞገደኛው ነውጤ ትረካ ከመፃፍት ዓለም Mogedegnaw Newte

Описание к видео ሞገደኛው ነውጤ ትረካ ከመፃፍት ዓለም Mogedegnaw Newte

#ፍቃዱተክለማርያም
#አበራለማ
#ሞገደኛውነውጤ
©Video credit Ethiopia today YouTube channel👇👇👇
   • Видео  
ሞገደኛው ነውጤ

(ከመጽሐፍት ዓለም - ድርሰት አበራ ለማ - ተራኪ ፍቃዱ ተ/ማሪያም - በኢትዮጵያ ሬዲዮ)

‹‹ስምህ?›› እንዳቀረቀሩ ጠየቁት ዳኛው፡፡

‹‹ነውጤ ደስታ›› መልስ ሰጠ - ተረጋግቶ፡፡

‹‹እድሜህ?›› ቀና ብለው የጎድን አስተዋሉት፡፡

‹‹ደጃች ገለታ ኦርቾ ለብአ ኢየሱስ ላይ ግብር ያጋቡለት ነው የተወለድኹት፡፡

እንግዲህ ዘመኑን ያስሉት የትና የት መሰለዎት? ሩእ ነው ሩእ . . . ›› እንደሚያሰላ ሰው አመልካች ጣቱን በጆሮ ግንዱ ላይ ደግፎ መለሰላቸው፡፡

‹‹ዓመተ ምሕረቱን አታውቀውም?›› ፊት ለፊት በጥያቄቸው አፈጠጡበት፡፡

‹‹ምን የምህረት ዘመን አንዴ ይመጣል አንዴ ይሄዳል ምን ተይዞ ነው ብለው ነው ጌታው? ሲለው አዝመራው የሰጠ ይሆናል ሲለው ውርጩና አረሙ በቡአያው ያስኧረዋል ምኑ ቅጡ ብለው ነው . . . ›› አለና የቅርታ ድምፅ አሰማ፡፡

ባማርኛችን አልተግባባንም መሠለኝ እኔ ያልኩህ . . . ›› ሲሉ አቋረጣቸው ተከሳሹ ነውጤ፡፡

‹‹እርግ! እርግ! . . . ይጫወቱ! ተከተማ ሰው ጋር መጫወትን እንደው ታንጀቴ ነው የምወደው፡፡››

ምንጭ፡ (አበራ ለማ፤መቆያ፣1981)

Комментарии

Информация по комментариям в разработке