■በገና ለመማር ምን የስፈልጋል ●የበገና ትምህርት ክፍል 1 ●begena lesson part 1

Описание к видео ■በገና ለመማር ምን የስፈልጋል ●የበገና ትምህርት ክፍል 1 ●begena lesson part 1

🙏⚜🙏⚜🙏⚜ምስጋና🙏⚜🙏⚜🙏⚜

👉ምስጋና የባሕርይ ገንዘቡ የሆነ እግዚአብሔር ዓለማትን ከመፍጠሩ አስቀድሞ በአንድነት በሦስትነት ሆኖ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነትና በሦስትነት ሲቀደስ፣ ሲመሰገን ይኖር ነበር፡፡ምስጋናውም አልተጓደለም፤ ባሕርዩ ባሕርዩን ያመሰግን ነበር፡፡ (“ፍጥረትን ሁሉ ከመፍጠሬ በፊት ምስጋናዬ ከእኔ ጋር ነው፤ ከፈጠርነው ፍጥረት መመስገን የምንሻ አይደለንም ምስጋናችን የባሕሪያችን ነው።” (መጽሐፈ አክሲማሮስ)፡፡
👉ፍጥረትን ኹሉ ሳይፈጥር የአብ፣የወልድ፣ የመንፈስ ቅዱስ ምስጋና አልተቋረጠም፡ጌታችንም በዮሐንስ ወንጌል ላይ “አሁንም አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር ከአንተ ዘንድ በነበረኝ
ክብር አንተ በራስህ አክብረኝ” ብሏል፡፡ ዮሐ.፯፥፭
👉ስለዚህ ምስጋና በዚህ ጊዜ ተጀመረ ማለት አይቻልም፡፡
👉እግዚአብሔር ክብሩ በባሕርዩ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ስሙን እንዲቀድሱና ክብሩን እንዲወርሱ መላእክትንና ሰውን ለባውያን፣ ነባቢያንና ማእምራን /አስተዋዮችና ዐዋቂዎች/ አድርጎ ፈጠራቸው፡፡

#ምስጋና_በሰው_ልጆች_ዘንድ

👉የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ዓላማ አንዱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “የመላእክትን እንጀራ የሰው ልጅ በላ” መዝ ፸፯(፸፰)፤፳፭ ብሎ እንደተናገረው። አዳምና ሔዋን እንደተፈጠሩ በቅዱሳን መላእከት ምስጋና ያመሰግኑ ነበር፡፡
👉ለአዳም የመጀመሪያውን ምስጋና ያስተማሩት ቅዱሳን መላእክት እንደሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ያስተምራሉ፤ ነገር ግን አዳምና ሔዋን ንጽሐ ጠባያቸው ሲያድፍባቸው በኃጢአት ሲወድቁ ከእግዚአብሔርና ከቅዱሳን መላእክት ተጣሉ፤ ከመላእክት ምግብም ተለዩ።እግዚአብሔር ግን እንደብሊቀ ነቢያት
ሙሴ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ፣ እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል የመሳሰሉትን ነቢያት እያስነሣ ይህን የቅዱሳን መላእክትን ምስጋና እንዲሰሙ ያደርግ ነበር፡፡ የሰው ልጅ ግን ሰማ እንጂ አብሮ ለመዘመር አልቻለም ነበር። ነገር ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም እንደ ሕፃናት በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ተወልዶ ባዩት ጊዜ ተለያይተው የነበሩት ሰውና መላእክት በአንድነት አመስግነዋል፡፡ ሉቃ. ፪፥፬

🛎እግዚአብሔርን የምናመሰግንባቸው ምክንያቶች በጥቂቱ

🤲እግዚአብሔር ስለፈጠረን፣ ሕልውና ስለሰጠን እናመሰግነዋለን፡፡
🤲እግዚአብሔር ስለሰጠን ተፈጥሮአዊ ተሰጥኦዎች እናመሰግነዋለን፡፡
🤲 ስላለንበት ስለምንኖርበት እምነት እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን፡፡
🤲እግዚአብሔር እስከዚህ ሰዓት እንድንኖር ስለፈቀደልን እናመሰግነዋለን፡፡
🤲እንደ ኃጢያታችን ስላላደረገብን እናመሰግነዋለን፡፡
🤲 እግዚአብሔር ስለጠበቀን፣ ስለመራን፣ ስለረዳን፣ ፍቅሩን ስለሰጠን እናመሰግነዋለን፡፡
🤲በውስጣችን ስለሚሰራው ጸጋ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን፡፡

🛎ስለ ማመስገን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነሱ ጥቅሶች

🤲ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔርን ባርኪ አጥንቶቼም ሁሉ፣ የተቀደሰ ስሙን፡፡መዝ ፻፫
🤲ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔር፣ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ።መዝ ፻፫

🛎እንዳናመሰግን የሚያደርገን ምንድነው❓

👉የተሰጠን በጎ የሆነውን ነገር አለማወቅ
👉የወደፊቱን አለመመልከታችን ዕብ ፲፩፥፩
👉የተቀበልናቸው ነገሮች ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከእኛ የተቀበልነው አድርገን ማሰብ












#በገና #በገና_መዝሙር
#ኤርምያስበገና #ዝክረበገና
#ኦርቶዶክስ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ለዘለዓለም_ፀንታ_ትኑር #Begena #Ermiasbegena #Orthodoxtewahedo #Oriental
#church #photo
#photography #creative
#artistic #artwork
#bass #instrumental
#Begena #hilling
#meditation #strings
#harp #handmade

Комментарии

Информация по комментариям в разработке