Egg Curry የእንቁላል ከሪ

Описание к видео Egg Curry የእንቁላል ከሪ

ኤግ ከሪውን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና ቅመማ ቅመሞች አይነት እና መጠን
4 እንቁላል (የፈረንጅ ወይም የሃበሻ የተመቻችሁን)
2 ራስ ደቆ የተከተፈ ሽንኩርት
2 በትንንሹ የተከተፈ ቃሪያ
1 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቂቤ
2 ትልልቅ ታጥቦ ተልጦ የተፈጨ ቲማቲም
1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት
1 የሾርባ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት ስልሱን ለማዘጋጀት
1 የሾርባ ማንኪያ ዘይት እንቁላሉን ለመጥበስ

የማጣፈጫ ቅመሞች በቡና ማንኪያ ልኬት
1 ተምሪክ ዱቄት (ከሪ / የእርድ ዱቀት መጠቀም ይቻላል)
1 ሚጥሚጣ
1 ከሙን
እና የምትፈልጉት ያህል ጨው
እንደ አማራጭ በተጨማሪ 1 የቡና ማንኪያ የፓፕሪካ ቅመም ማስገባት ትቻላለችሁ
የፓፕሪካ ቅመም ከሌላችሁ የድንብላል ዱቄት ማስገባት ይቻላል
እንዲሁም ሁለቱንም አለማስገባትም ትችላላችሁ

እንቁላል ለመቀቀል
ውሃ ድስት ውስጥ እንቁላሉን በደንብ እስኪሸፍን ድረስ ጨምሮ መጣድ
1 ቁንጥር ጨው ከላይ መጨመር
የምንፈልገው በደንብ የበሰለ እንቁላል ስለሆነ ውሃው ልክ መፍላት ከጀመረበት አንስቶ ለ 15 ደቂቃ ያህል መቀቀል
ከ15 ደቂቃ በሃላ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ አቆይቶ መላጥ

እንቁላሉን ለመጥበስ
እንቁላሉን ዙሪያውን በከፊል መሰንጠቅ
መጥበሻ ላይ 1 ሾርባ ማንኪያ ዘይት እና 1 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቂቤ ማጋል
ቂቤው የተነጠረ መሆን አለበት
ቂቤው ሲቀልጥ 1 የቡና ማንኪያ ሚጥሚጣ ጨምሮ እንቁላሉን ከ5-7 ደቂቃ ቀለሙን በከፊል እስኪቀይር መጥበስ

ማባያ
ቂጣ ፣ ዳቦ እና እንጀራ
አብሮት የሚቀርብ
ሩዝ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке