የቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኽኝ (ድ/ር) ሽኝት ፕሮግራም በጎፋ አጥብያ | Bishop Teklemariam's Memorial Service at Gofa Church

Описание к видео የቢሾፕ ተክለማርያም ገዛኽኝ (ድ/ር) ሽኝት ፕሮግራም በጎፋ አጥብያ | Bishop Teklemariam's Memorial Service at Gofa Church

መጎናጸፊያ ተቀበል ለምታስቀጥለው

አንድ ብቻውን ሳለ የጠራው
እንደ ምድር አሸዋ እንደማይቆጠረው
እንደሰማይ ከዋክብት እንደማይገመተው
ገና እባርክሃለሁ ገና አበዛሃለሁ ያለው
መንገዱ ቢከብድም በቃሉ ታማኝ ነው

አብርሃም በመታዘዝ ልጁን በመሰዋት
ይስሐቅ የተደፈኑ ጉድጓዶችን በመክፈት
ያዕቆብ ታግሎ ተቀብሎ በረከት
አሸንፎ አሻገረ የአባቶቹን እምነት

ሙሴም ተተካ ሊቆም ለነፃነት
ቀኑ ጨልሞ ሰማዩ ድም በተፋበት
አዳኝ ጠፍቶ ተስፋ በጨለመበት
ብዙ አሳለፈ መከራና ጭንቀት
እጅ ሳይሰጥ ሳይንበረከክ ቆመ ለተጠራለት

የእግዚአብሔር ባሕርይ
ሲጠራ አገልጋይ
በመጀመሪያ መጨረሻውን የሚናገር ነው
የመሀሉ ጉዞ ታግሎ በማሸነፍ ነው

የእግዚአብሔር አገልጋይ ሕይወቱ
ከእግዚአብሔር የሚያታግል ለሕዝቡ
አለው መከራ ማይታለፍ ሚመስል
ጠቦት መጠበቁ ግልገልና በግ ማሰማራት
ጥበብ ይፈልጋል ያስከፍላል መስዋዕትነት
ዘጠና ዘጠኙ ተትቶ አንዱ እንዳይጠፋ
ሁሉን በፍቅር መያዙ እይታን እያሰፋ
መከራና ችግር ማጣቱ እየጎሰመ
ስጋን በጥርስ ነክሶ ይኖራል ተስፋን እያለመለመ

ጉዞው ሲከብድ አቅም ሲታጣ
መከራው ችግሩ ከብዶ ሲያንገላታ
ረሀብ ቸነፈሩ እጅጉን ሲቀጣ
ፈተናው በዝቶ እንደ ዘይት ሲያንጣጣ
እኔ አለሁልህ አይዞህ እያለ ሚያፅናና
ከመንፈሱ የሚያፈስ ጠማማውን ሚያቃና
አለ እግዚአብሔር ለአገልጋዩ ልቡ ለቀና

እንዲህ እያሉ ኢየሱስን አገልግለው ያለፉ
እድሜያቸውን በሙሉ በወንጌል ያሳለፉ
የመዳንን ወንጌል የሰበኩ ለጠፉ
ለኛ ለዚህ ትውልድ የሚያስተላልፉት
አለ እንድ ነገር በደማቸው የፃፉት
አለ መጎናፀፊያ ዕጥፍ ቅባት ያለበት ከኋላቸው የጣሉት
ለእውነት ወንጌል እነሱ ለተጠሩት
እንዲህ ነው ሕይወታቸው በእግዚአብሔር የተጠሩት

ብዙ ብል ብዙው ይቀራል ስለአገልጋዩ
ያሳለፈውን ባነሳ ገና ሚያሳልፈው
ገና ይቀራል /2*
የሕይወታቸው መንገድ ከየሱስ ጋር ያሳለፉት
ለኛ ለዚህ ትውልድ የሚያስተላልፉት
መጎናጸፊያ አለ በእጥፍ የተቀባ
ትውልድ ንቃና ትኩር ብለህ ተመልከት
አንተም ለምታስቀጥለው ወንጌል ለእውነት
ራስህን አዘጋጅ በልመና በፀሎት
ራስህን አዘጋጅ በእጥፍ ለመቀባት
ራስህን አዘጋጅ አንተም ለማስቀጠል

የኤልያስ ዘመን አሁን ተፈፀመ
ኤልሳዕ ተተካ በእጥፍ መንፈስ ታተመ
መጎናጸፊያው እንዳያልፍህ በርታ ተነሳ
ምታስቀጥል ትውልድ በአባቶች እጥፍ መንፈስ
ስለዚህ ንቃ በፀሎት ልብህ ይፍሰስ ተቀበል እንደ ኤልሳዕ መጎናጸፊያ
አስቀጥል በዘመንህ በሁለት እጥፍ መንፈስ።



2ኛ ነገሥት 2:11_14
ሲሄዱም፦ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።
ኤልሳዕም አይቶ፦ አባቴ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላና ፈረሰኞች፥ ብሎ ጮኸ። ከዚያም ወዲያ አላየውም፤ ልብሱንም ይዞ ከሁለት ተረተረው።
ከኤልያስም የወደቀውን መጐናጸፊያ አነሣ፥ ተመልሶም በዮርዳኖስ ዳር ቆመ።
ከኤልያስም የወደቀውን መጎናጸፊያ ወስዶ ውኃውን መታና፦ የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? አለ፤ ውኃውንም በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።


#BishopTeklemariam, #BishopTekle, #apostolicchuchsongs, #apostolicchurchofethiopia, #apostolicsongs, #hawaryawitmezmur, #

Комментарии

Информация по комментариям в разработке