የ1 እና 2 ተሰሎንቄ መልእክታት ታሪካዊ ዳራ

Описание к видео የ1 እና 2 ተሰሎንቄ መልእክታት ታሪካዊ ዳራ

ይህ ቪድዮ እነዚህን መጻሕፍት በዐውዳቸው እንድትረዷቸው ያግዛችኋል! ጳውሎስ የ1እና 2 ተሰሎንቄ መልእክታትን የጳፈው ለምንድን ነው? የተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ዐዲስና ለጋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን በልዩ ልዩ ስደቶች ውስጥ እያለፈች ነበር፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት ተስፋ አጽንተው ይጠባበቁ የነበሩ ቢሆንም ነገር ግን አንዳንዶቹ ባሕላዊ አመለካከታቸው የዳግመኛ መምጣቱን አንዳንድ ገጽታዎች በተሳሳተ መንገድ እንዲረዱ አድርጓቸው ነበር፡፡ የተሰሎንቄን ታሪካዊ ዳራ ማወቅ እነዚህን ቅዱሳት መጻሕፍት በተሻለ መንገድ ለመረዳት ያስችላችኋል፡፡ የመጻሕፍቱ መልእክትም የክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት ያለ ነቀፋ በመኖር በትዕግሥት ተጠባበቁ የሚል ነው!
የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አስደሳችና ለሁሉም ተደራሽ ሊሆን ይገባዋል እንጂ አሰልቺ ሊሆን አይገባም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ሂደት ውስጥ ሥነ ጽሑፋዊ ዐውዱንና ታሪካዊ ዐውዱን መረዳት በጣም ወሳኝ ክፍል ከመሆኑም በላይ አስተሳሰባችንና አኗኗራችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንዲሆን ያስችለናል፡፡ እነዚህ ቪድዮዎች የተዘጋጁት በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን በቀላሉ ሊረዱ በሚችሉበት መንገድ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ቪድዮዎቻችን የግልም ሆነ የቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን የሚግዙ ናቸው፡፡

ተኣማኒ የኾኑ ክርስቲያናዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች፣ ቪድዮዎችና መጻሕፍት ለማግኘት http://www.Yeamlak.com ድረ ገጽን ይጎብኙ

http://www.thebibleeffect.com
  / experiencethebibleeffect  
  / thebibleeffect  

#ተሰሎንቄ #ጳውሎስ #መጽሐፍቅዱስጥናት #መጽሐፍቅዱስ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке