እንዳንቱ 2 - የህብረት መን+ሺዳ - መዛሚር ሊቃ መድረክ #1

Описание к видео እንዳንቱ 2 - የህብረት መን+ሺዳ - መዛሚር ሊቃ መድረክ #1

#mezamir
#liqa
#neshida

እንዳንቱ #2 ግጥም ሀሰን አራጋው

صلى عليك الله يا علم الهدى *** واستبشرت بقدومك الأيامُ
هتفت لك الأرواح من أشواقها *** وازينــت بحديثك الأقلامُ

ፍቅርሁ መቼ ያውቅና የነገ ቀጠሮ፣
በዕለት እየወጋኝ ልቤ ላይ ተቋጥሮ።

አወዳሽ አድርጎኝ ከዓለም አስፈንጥሮ፣
እንዳንቱ አላየሁም ሙሉ ሰው ተፈጥሮ።
……………………

ሸሽጌ ያኖርኩት የሙሀባ ግርዶ፣
ለአደባባይ ሰጠኝ በናፍቆት ተቀዶ።

አሁን ምን ይባላል ሃድራ ለዶቆሰው፣
ምሱን መቀበል ነው ወዶ የገባ ሰው።

በወዳጄ ናፍቆት ነፍስያዬ ታማ፣
ይሄ ሰው ምን ሆነ ተብዬ ብታማ።

ማን ይደርስልኛል ርቆኝ መንገዱ፣
እሽራለሁ እንጂ ሲያጠጣኝ ከሀውዱ።
……………………
Choir
ፍቅርሁ መቼ አገኘ ምትክ ተጋሪ፣
ለናፋቂ ጭፍራ ከርሞ አደናጋሪ።

ቀምሼው ቢጣፍጥ ተውሂድ ተደግሶ፣
እንዳንቱ ማን ፀና በልቤ ላይ ነግሶ
-------------

صلى عليك الله يا علم الهدى *** واستبشرت بقدومك الأيامُ
هتفت لك الأرواح من أشواقها *** وازينــت بحديثك الأقلامُ

የመውደዱ ፈንጂ መዲና ተጠምዶ፣
በሪሳላው ጥይት ሸፍዓው ተገምዶ።

ተኩሶ እንዳይገለኝ ሱናውን ታጥቄ፣
ተረፍኩኝ እንዳልል መሞቴን ናፍቄ።

የዘላለም ክስረት በተውሂዱ ከሽፎ፣
ዑመቱ አደረገኝ ቀደር አሸንፎ።

አንቱን የሚጠጋ ባይኑ እንዳላለፈ፣
ሀሰን የከተበው ለእኛ እየተረፈ።
……………………

እንዳንቱ ከማለት ልሳን ያላረፈው፣
ምርኮኛ ሆኜ ነው ፍቅር የጠለፈው።

እኔ የጡሃ ሰው ዑመት ተሰላፊ፣
ጡሃን የላከልኝ እዝነቱን ጨላፊ።

ላኪውን ለመንኩት ናፍቄው እንዳልቀር፣
ምኑን አፈቀርኩት ካላየሁት በቀር።

…………………………
صلى عليك الله يا علم الهدى *** واستبشرت بقدومك الأيامُ
هتفت لك الأرواح من أشواقها *** وازينــت بحديثك الأقلامُ

ፍቅርሁ መቼ ያውቅና የነገ ቀጠሮ፣
በዕለት እየወጋኝ ልቤ ላይ ተቋጥሮ።

አወዳሽ አድርጎኝ ከዓለም አስፈንጥሮ፣
እንዳንቱ አላየሁም ሙሉ ሰው ተፈጥሮ።
……………………

ዕንቁ መሆንዎን ለዓለም ለመመስከር፣
ቀለባችን ሆኗል ማወደስ መዘከር።

ላንቱ ያለን ቦታ በምን ተወስፎ፣
በስስት የሚያይሁ ዑመት ተንሰፍስፎ።

አንቱን አንቱን ብሎ ከአቅሉ ተነጠለ፣
በኢሽቅ አውደ ውቂያ እየተቃጠለ።

እንዳንቱ የምለው ከሌላው ለይቼ፣
ሳላይ ወድጄው ነው ዝናውን ሰምቼ።
---------

ዕንቁ መሆንዎን ነብዬ
ለዓለም ለመመስከር ውድዬ፣
ቀለባችን ሆኗል ነቢ
ማወደስ መዘከር ውዴ

ላንቱ ያለን ቦታ ነቢ
በምን ተወስፎ ውዴ፣
በስስት የሚያይሁ ነቢ
ዑመት ተንሰፍስፎ ውዴ

አንቱን አንቱን ብሎ ነቢ
ከአቅሉ ተነጠለ ውዴ
በኢሽቅ አውደ ውቂያ ነቢ
እየተቃጠለ ውዴ

እንዳንቱ የምለው ነብዬ
ከሌላው ለይቼ ውዴ፣
ሳላይ ወድጄው ነው ነቤ
ዝናውን ሰምቼ ውዴ



--------------------------

ከመዛሚር ሊቃ #1 መድረክ

ግጥም
ሀሰን አራጋው

ዜማ
ዓብዱሰላም

ቅንብር
ኤሉና ስቱድዮ

አዘጋጅ
በያን ሚድያ
መዛሚር ነሺድ
ፕሮጀክት ማኔጀር
ዓብዱሰላም

ፕሮዳክሽን
ብራይት ፕሮዳክሽን

ሙንሺዶች
ዓብዱሰላም
ሰላሐዲን ዘይኑ
ዳዊት ታረቀኝ (ዴቭ)
ሰዓድ አህመዲን
አደም ያሲን
ኦሳማ ኢብራሂም
አብዱልጀባር ያሲን (አቡጃ)
ፈይሰል ሰመር
አሊ አከመል (አሉሽ)
አቡበከር ሰፊዩ
ማዲህ ሙኽታር ኸድር

ካሜራ
ሚፍታህ መሀመድ
መሀመድ አብደላህ
ሙአዝ መሀመድ
መሀመድ አወል
ሙባረክ ጀማል

ኤዲቲንግ
ሙአዝ መሀመድ
ሙባረክ ጀማል

ምስጋና
ቢላል ቲቪ
ጀይሉ ቲቪ
ኑጁም
ኮሌታ
ኑር አዲስ ዲዛይን
ረኒን የስልክ ጥሪ ማሳመርያ
ኢስሀቅ ዲጄ እና ዲኮር
ፏ ዲኮር
መንሱር በድሩ
ቶፊቅ ዩሱፍ
ሀምዛ ኸድር ሀሰን
ማሂር አማን
አብዱልሀቅ`
ሳላህ ጅብሪል
መሳይ ሀይሉ
ረደላህ መሀመድ
አልፈሪድ መንሱር
ሙኒብ ሙሳ
ሰሚራ ናስር
ሃቢባ
ለተሳተፋቹ በሙሉ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке