አሚር ሁሴን//ሰይዲ የዘላለሜ/አዲስ መንዙማ 2016AMIR HUSSEN SEYEDI YEZELALEME NEW MENZUMA2024

Описание к видео አሚር ሁሴን//ሰይዲ የዘላለሜ/አዲስ መንዙማ 2016AMIR HUSSEN SEYEDI YEZELALEME NEW MENZUMA2024

ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️ 
‪@alfarukmultimediaproduction‬
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️ 
        ‪@AMIRHUSSENofficial‬
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️ 
      ‪@SelehadinHussenofficial‬

 
=======================


ረቢ ሰሊ ዐላ በድሪል ከማላ
ሙስጠፋ ነብየል ጀማል
ሀቢበል መዉላ

ወደ ፍቅር ጉዞ ❤
ወደ ፍቅር ዐለም
ነቢን በማለም * ያን የኑር ገላ

@ በተዉሒዱ ጮራ
አላህን አናጥራ
አይከጅልም በል * ከቦታ ስፍራ

እስኪ እንጥራዉ ስሙን
በግጥም በዜማ
በአንድነት እንበል አበል ፋጢማ

❤❤❤

ስማኝ ወዳጄ ❤ ነቢን ጠርቼ
አፍሬ አላቅም ❤ ከቶም አልወድቅም
ሐድራን አለቅም

ካንቱ ዉጪ ያለ * ፍቅር በሙላ
ትርፉ ህመም ነዉ ያረሡላላ
አንቱ ኖት የዘላለሜ
ሰይዲ የዘላለሜ
አንቱ ኖት የዘላለሜ
ሰይዲ የዘላለሜ


❤❤❤

የአምቢያት ሁላ መርህ ነዉ ፈለግ
ኸይርን ክጀላ ተበሩክ ማድረግ
ፀጉራቸዉን ተላጭቸዉ ጠሀ
ሰጡት ፀጉሩን ለአባ ጠለሀ
አዘዙ * ያረሡለላ
እንዲሰጥ ለአስሀባዉ ሁላ
አዘዙ * ያረሡለላ
እንዲሰጥ ለአስሀባዉ ሁላ

❤ የወዱ ፀጉር የረሡለላ
ተከፋፈለ ለዐስሀባዉ ሁላ
ማንስ አገኘ ማንስ ደረሠዉ
እንኳንስ መሳም ምነዉ ብጉረሰዉ
የነቢን የዐለሙን ጀንበር
ፀጉሩን ታቅፌዉ ልደር
የነቢን የዐለሙን ጀንበር
ፀጉሩን ታቅፌዉ ልደር

✍️በል ዘንበል ዘንበል ነቢ ነቢ በል
ነቢ ሲጠሩ አትሂድ ገደል
እዉነት ነዉ ፍቅር አይደበቅም
በፍቅር ገላ ዉሸት አይዘልቅም

❤❤
ረቢ ሰሊ ዐላ በድሪል ከማላ
ሙስጠፋ ነብየል ጀማል
ሀቢበል መዉላ

ከአረንጓዴ ቁባዉ
ደርሼ ከረዉዳዉ
ምናል በደፋኝ ጀማሉ ሀይባዉ

ፍቅሮን እንደ ደም
ለሚለግስ ሰዉ
ብትወቅስ አይገርመዉ ብታሞግሰዉ

አስነኩኝ ፀጉሩን
ቀሚሱን ወይ ልብሱን
የዉዱ ዘይኑን የነካ ገላ


❤❤❤

ስማኝ ወዳጄ ❤ ነቢን ጠርቼ
አፍሬ አላቅም ❤ ከቶም አልወድቅም
ሐድራን አለቅም

ካንቱ ዉጪ ያለ * ፍቅር በሙላ
ትርፉ ህመም ነዉ ያረሡላላ
አንቱ ኖት የዘላለሜ
ሰይዲ የዘላለሜ
አንቱ ኖት የዘላለሜ
ሰይዲ የዘላለሜ

❤ ያቺ ዑሙ ሱለይም ትናገር ታዉራ
ተኝየዉ ሳሉ ሰይደል ወራ
ሰዉነታቸዉ ላብ አልቧቸዉ
ሲፈስ ብታይ ከመኝታቸዉ
የነቢን ላብ ልትቀዳ
አመጣች ብልቃጥ ከጓዳ
የነቢን ላብ ልትቀዳ
አመጣች ብልቃጥ ከጓዳ

❤ የነብዩን ላብ በስስ በጨርቆቿ
አየጨመቀች በብልቃጦቿ
እስከሚበቃት አኖረች ሞልታ
የዉዱን ነቢ በረካ ሽታ
* ቢያዩዋት ነቢ ሲነቁ
ምን አረግሽ ብለዉ ጠየቁ
ቢያዩዋት ነቢ ሲነቁ
ምን አረግሽ ብለዉ ጠየቁ

ያቺ ዑሙ ሱለይም መለሠች ብላ
ላቦን አኖርኩት ያረሡለላ
ብለዉ መለሱ የዐለሙ ጀማል
ዑሙ ሱለይም ሆይ ጥሩ ሰርተሻል


(መጨረሻ)

ስማኝ ወዳጄ ❤ ነቢን ጠርቼ
አፍሬ አላቅም ❤ ከቶም አልወድቅም
ሐድራን አለቅም

ካንቱ ዉጪ ያለ * ፍቅር በሙላ
ትርፉ ህመም ነዉ ያረሡላላ
አንቱ ኖት የዘላለሜ
ሰይዲ የዘላለሜ
አንቱ ኖት የዘላለሜ
ሰይዲ የዘላለሜ

ሠይዲ የኔ ዐለሜ
ላንቱ ነዉ ሚፅፍ ቀለሜ

ፈዋሼ ኖት ለህመሜ
ጠቢቢ የኔ ሀኪሜ

መሪዬ የኔ ኢማሜ
ናፍቆቴ ርሀቤ ጥሜ

አማኔ የኔ ሠላሜ
ነቢ ኖት የዘላለሜ  



ይህን ቪድዮ ያለ ፍቃድ ሌላ ቦታ ላይ መልቀቅ የተከለከለ ነው!
Unauthorized distribution and re-upload of this content is strictly prohibited

Copyright © 2024 ‪@alfarukmultimediaproduction‬

Комментарии

Информация по комментариям в разработке