Tofik Yusuf - Shafaye || ቶፊቅ ዩሱፍ - ሸፈዐዬ (Official Music Video)

Описание к видео Tofik Yusuf - Shafaye || ቶፊቅ ዩሱፍ - ሸፈዐዬ (Official Music Video)

Watch Tofik yusuf music video ‘’ Shafaye ሸፈዐዬ ‘’ ቶፊቅ ዩሱፍ
connect with Tofik Yusuf:
Tiktok:   / tewfiq225  
Instagram:   / tofikyusufm  
Official Youtube:    / @tofikyusuf  
Facebook:   / tofikyusufm  
Official Website: http://www.tofikyusuf.com
Credit:
Lyrics: Zahid Iqbal
Melody: Tofik Yusuf
Mixing & Mastering: Mohammed Raju
Special Thanks:
Husni Abdela ( Drilis Restaurant)
Al Bukhari Brand Collection
Roza Mohamed Idris (ንግስት)

Lyrics:

[…ሸፋዓዬ ነቢ ዋሴ ጠበቃዬ…ያ ረሱለሏህ!
አስታራቂ ኖት ሸምጋዬ …ያ ሐቢበሏህ]
**

ሁሉም በጭንቀት ሲናወጥ
ሲተረማመስ መኽሉቁ፣
ግለቱ በላብ ሲያጠመቀው
የማሕሸር ነዲድ ለበቁ።
ያን’ቀን ነው ወዳጅ ሚከፋው
በቂያም በፍርዱ ሜዳው፣
ወንድም ወንድሙን የሚሸሽ
እናትም ልጇን ምትከዳው።

የሰው ዘር መቆሚያ ሲያጣ
ቢጋፋም ስፍራው ሲጠበው፣
አይተርፍም ከፀሃይ ግለት
እንደ’ሳት ከሚለልበው።
አታውጋው የኻሊቅ ቁጣው
ያ’ንቀን ማን ቀርቦ ሊያባብለው፣
ማን ማንን ዞሮ ሊያስተውል
ሁሉም "ዋ ነፍሴን" ነው ሚለው።
(ሁሉም ሰው ነፍሴን ነው ሚለው)


በፍርሃት ስጋት ተይዞ
ሲኳትን መላ ፍለጋ፣
አማልደን ብሎ ሊማፀን
አደም ጋር ሔዶ ቢጠጋ።
ስልጣኑ የለኝም ብለው
እያለቀሱ በነደም፣
አሏህ ፊት ደፍሮ መቆምን
አልችልም! ይላሉ አደም።

**
አልበቃም እና ለማስታረቁ፣
እኔን ትታቹ ኑሕን ጠይቁ።
ኑሕ’ም ሲጠሩ ዋስ እንዲቆሙ፣
ወደ ኢብራሒም ነው ሚጠቁሙ።

የለኝም ብለው ኸሊል መላውን፣
ከሊሙ ዘንዳ ልከው ዙምራውን።
ጓጉቶ ሲጠይቅ ከሊሙን ሙሳ፣
ተጓዝ ይሉታል ወደ’ነቢ ዒሳ።

በቂያም ሸንጎ በ’ለተ ፍርዱ፣
አወይ ስቃዩ ውጣ ውረዱ።
አንዱ ሌላው ጋር ብሎ ሲመራው፣
አቤቱ ያን’ቀን መኽሉቅ መከራው።
****
ምልጃ ቢጠሩ ዒሳ’ብኑ መርየም፣
አልችልም እኔ ስልጣኔ’አይደለም።
በማለት ሸሽተው ይመክሯል ሌላ፣
ሙሐመድ ጋር ነው የሁሉም መላ።

በሙሐመድ ነው የፍጥረት ምልጃ፣
በሙሐመድ ነው ያለው ፈረጃ።
አሕመድ’ጋር ሒዱ መላን አያጣ፣
ካለሱ አይበርዱም የዚ’ቀን ቁጣ።

(ለሌላው ከብዶ የማይወጣው፣
ለሙሐመድ ያደለው እጣው።
ሙሐመድ እንጂ የለም ገላጋይ፣
ከኻሊቅ ቁጣ ፍጥረቱን ሸምጋይ።)
****
ረሒሙ ነቢ
መርሓባን እንጂ እምቢን ማያውቁት፣
"እኔ’ኣለሁ "ብለው
ኸልቁን ተኻሊቅ ሊያስታርቁት።
ንግስናቸውን ባ’ዘሉ ሸንጎ ፊት የፈረደው፣
አስታራቂ_ያችን…
ዋስ ሲቆሙ ነው ቁጣው ሚበርደው።
…………
በ’ለተ ፊትናው ችግር ሲከፋ፣
ጉድ ሲፈነዳ ሸምጋይ ሲጠፋ ።
የከውኑ ዳኛ ሱጁድ አድርገው፣
ኸልቁን በማርታው እንዲፈውሰው።

ቀና በል ውዴ እራስህን አንሳው፣
አንተ ጠይቀህ የለም ምሳሳው።

ፊት የተባሉት ጠይቅ ያሻህን፣
ያይማፀኑታል ብለው ማርታህን።

ጌታዬ አደራ…
በቁጣህ ማ’በል እንዳልቀሰፍ፣
የነቢ ወዳጅ …
ሆኜ ልሰለፍ፣
አደራ አደራ…
ካ’ዛብ እንድተርፍ።

አደራ ራህማን…
እንዳያነደኝ ያን’ቀን ግለቱ፣
አደራ ረሂም…ሸፋዓነቱ፣
አደራ ወዱድ… ብያለሁ ላንተው፣

መከራው ሲጦፍ በማሕሸር ሜዳ፣
ቁጣው ሲባባስ ጉድ ሲፈነዳ፣
ነፍሴን ነፍሴን ሲል ወዳጅ ሲከዳ፣
አደራ ……አደራ
እኔን አድርገኝ ሰይዲ ዘንዳ።

……………………
( ዛሂድ ኢቅባል… …ረመዷን 2015…… አለቀ)
©️Tofik Yusuf 2024

Комментарии

Информация по комментариям в разработке