ስላንተማ Silantema ቤተልሔም ወልዴ Bethelehem Wolde

Описание к видео ስላንተማ Silantema ቤተልሔም ወልዴ Bethelehem Wolde

Gospel song by singer Bethelehem Wolde. I have alot to say for what you have done for me and human being. Lord Jesus you laid down your life to save ours.
“ስለ አንተማ”
በዘማሪት ቤተልሔም ወልዴ

እንታነጽበት ዘንድ አቅራቢ ወንድም ሶካ

ስለ አንተማ (ብዙ የምናገረው አለኝ) 2
የትኛውን አንስቼ የትኛውን እተዋለሁ
ጌታዬ ስራህ እኮ ከአዕምሮዬ በላይ ነው

እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም
ደካማን በመጣል አንተ አትታወቅም
ከጥንት የሰማነው በዓይናችን ያየነው
ጻድቅነትህንና ሰውን መውደድህን ነው /2

ስለ አንተማ ብዙ ምናገረው አለኝ …

ጥንት አባቶቻችን ስራህን አወሩ
ድንቅ ታምራትህን እየመሰከሩ
ስራህ እግዚአብሔር ሆይ ከአዕምሮ በላይ ነው
እኔ ምስክር ነኝ በዓይኔ አይቻለሁ /2

ስለ አንተማ ብዙ ምናገረው አለኝ …

የማወራው አለኝ የምመሰክረው
ስለአንተ ምህረት ፍቅር የምናገረው
ስለ ሰው ልጅ ኃጢአት ልጅህን ሰጥተሃል
በእውነተኛ ፍቅርህ እኛን አድነሃል /2

[ከአምሮ በላይ ነው ፍቅርህ
እኛን መውደድህ] 4

ክበር እንጂ ሌላማ ምን እንላለን
በላይ በላይ ምስጋና እንጨምራለን
በላይ በላይ ክብርን እንጨምራለን

ንገስ እንጂ ሌላማ ምን እንላለን
በላይ በላይ ምስጋና እንጨምራለን
በላይ በላይ ዝማሬን እንጨምራለን

ልነሳና ልነሳና
ላክብርህ ምክንያት አለኝ
ብዙ ብዙ ምክንያት አለኝ ክበር

ምስጋና ላንተ ነው
ክብርም ላንተ ነው
አምልኮ ላንተ ነው
ስግደትም ላንተ ነው

ያረክልን ብዙ ነው ጌታ /2
ያረክልን ብዙ ነው አዎ /2

ውዳሴ ላንተ ነው
ቅዳሴም ላንተ ነው
ጭብጨባ ላንተ ነው
ዕልልታም ላንተ ነው

ያረክልን ብዙ ነው ጌታ /2
ያረክልን ብዙ ነው አዎ /2

Комментарии

Информация по комментариям в разработке