ዋ እኔን የንስሐ መዝሙር በ መሪጌታ ፍቅሩ ሳህሌ (ከግጥም ጋር) Zelesegna song by Merigeta Fikeru Sahele ( lyrics video)

Описание к видео ዋ እኔን የንስሐ መዝሙር በ መሪጌታ ፍቅሩ ሳህሌ (ከግጥም ጋር) Zelesegna song by Merigeta Fikeru Sahele ( lyrics video)

ዋ እኔን x3
በደለኛውን ማን ያስታርቀኛል አዳኝ አምላኬን
በመስቀል ላይ ውሎ የታደገኝን በበደል ላኖሩኩት
መላ ዘመኔን ይኸው አለቅሳለሁ እዩት እንባዬን
ማን ያስታርቀኛል አዳኝ አምላኬን
በአለም ፍቅረ ነዋይ ንክሻ ስቆስል ስለኔ አልቅሳ
ማርልኝ የምትል እኔ የምመካባት አለችኝ ደግ እናት
እስቲ ሂጄ አልቀሼ ለድንግል ልንገራት
የአማኑኤል እናት ስለ እናትነትሽ ይቅርታ እንዲሰጠን
አማልጂን ከልጅሽ የድንግል ትምክህት የአለም ሁሉ ንግስት
አደራ እመቤቴ ሰዓሊ ለነ ቅድስት
ፀሐይ ስትጨልም ጨረቃ ደም መስላ ውለታ ሲመልሱ
ጋርደው የአምላክ ገላ ግዑዝ ሲመልስ ለጌታ ውለታ
ምን ይዤ እቀርብ ይሆን የተጠራሁ ለታ
የትምክህት መንገድ ያላችሁ ስለ በጎ ስራው ገደሉት ብላችሁ
እስቲ የእመቤቴን ሀዘኗን አስታውሱ ወዬ ወዬ በሉ
ጠዋት ማታ አልቅሱ
በማእከላዊ ግርማ ሰማይ ሲፈራርስ መሬት ያኖረውን በግርማ ሲመልስ
በስላሴ ዙፋን በፍርድ ስጠራ ክርስቶስ አቁመኝ እባክህ አደራ
ዋ እኔን
በደለኛውን ማን ያስታርቀኛል አዳኝ አምላኬን
ልጅሽን ለማዳን ይዘሽ ሀገር ለሀገር ስትንከራተቺ በበረሀ በዱር በዚያ
በግብፅ ሀገር ማን አፅናናሽ ይሆን ድንግል እመቤቴ እኔ አፈር ልሁን
ጌታዬ አርመኝ ክፉ አመሌን አንተ ታውቃለህ ሰውን መበደሌን ፍቅረ ነዋይ ይዞኝ
ግራ እየተነዳሁ አቤቱ ይቅር በለኝ ለነፍሴ ተጎዳሁ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке