Apostolic Songs | A.A Gofa Apostolic Church | Apostolic Church Of Ethiopia | Apostolic choir Mezmur

Описание к видео Apostolic Songs | A.A Gofa Apostolic Church | Apostolic Church Of Ethiopia | Apostolic choir Mezmur

አዲስ አበባ ጎፋ አጥቢያ
የቃሊቲ እና የአቃቂ ጥምር ንዑስ ሰበካ

አውቃለው የሚሳን እንደሌለህ
አውቃለው የሚያቅት እንደሌለህ
አውቃለው ሁሉንም ትችላለህ
አውቃለው የኔ ጌታ
አውቃለው እየሱስ ነህ
አውቃለው ኤልሻዳይ አምላክ እንደሆንህ

ተራራው በፊትህ መቆሙ ምንድነው
ልታፈርሰው መዶሻው በእጅህ ነው
ጨለማውም ቢሆን ትርጉም አልባ ነው
በብርሃን ይተካል ስትናገርህው

ያለቀውንና የተቆረጠውን
ዳግም የምትቀጥል ተስፋ የታጣለትን
እምነት የምትሆን የምትጨብጥ
ለሞተው ህይወትን ደግመህ የምትሰጥ

አውቃለው...

ጥቂት በጥቂቱ ጠብ ጠብ እያለ
ነገሬ ተባርኮ ሞልቶ ይህው አለ
ባንተ የእኔ ጌታ ሆነልኝ ነገር
ልቤን ደስ አሰኘው

ከጥንትም ጀምሮ ክንድህ የታወቀ
ሀያል እና ብርቱ ጠላትን ያደቀቀ
እኔም በዘመኔ አይቼዋለው
አልጠራጠርም እታመናለው

#abenezerfekadu #Apostolicsongs #apostolicchurchmezmursongs

Комментарии

Информация по комментариям в разработке