Abduselam - ዓለል መዕሱም ﷺ - ዓብዱሰላም | Alel Meesum | على المعصوم - (نشيد /مديح سوداني/فرقة الصحوة

Описание к видео Abduselam - ዓለል መዕሱም ﷺ - ዓብዱሰላም | Alel Meesum | على المعصوم - (نشيد /مديح سوداني/فرقة الصحوة

#abduselam
#amharicnasheed
#ethiopianneshida
#neshida
#newneshida
#ethiopia
#mezamir
#madad

ዓለል መዕሱም ግጥም - መሀመድ ኢድሪስ ካሳ
ዓረብኛ - ሱዳን ህዝባዊ

على المعصوم صلي ياذا الطول
والانعام عد ما قيل قول
ቃሌን በመድሁ የሾምከው ጌታ
ሰላምታ ኣስፍን በጦይባው ሽታ
--------

እሱ ነው ኩሌ ኑሩ ሚዘልቀው
ዘመን ቢሳደድ ፈድሉ ማያልቀው
የሁቡ ንፋስ ነፍስ የሚያደምቀው

በፍቅሩ ግዞት ልቤን ሞሽሮት
የዙልምን ጎሳ በተውሂድ ሽሮት ።

ገላዬ እንደጨርቅ የቀረው ነትቦ
ቀለሜ ኣይደርቅም ሲፋውን ከትቦ
ሲያነሳው ቢያድር ሲያዜም ቢውልም
የፍቅሩ ድባብ ፈቀቅ ኣይልም ።

መድሁ እንደሰንደቅ የተነገበው
የፍቅሩ ቀለብ ልብ የሚያጠግበው
ነፍሴን እንደእሳት ኣንገበገበው
ምነው የረውዳው ደጁን ብቀርበው ።

ልቡ የፈካው በወህይ ደምቆ
ነፍሱ የላቀው በሃላል ታጥቆ
እሱን ሲጠራ የኑር ድባቡን
ሁቡ ዘመተ ፈጀው ሙሂቡን ።

——————————
على المعصوم صلي ياذا الطول
والانعام عد ما قيل قول
ቃሌን በመድሁ የሾምከው ጌታ
ሰላምታ ኣስፍን በጦይባው ሽታ

ኣንዴ ኣይቼው የፊት ጸዳሉን
ድምጹን ሰምቼ ያን የኑር ቃሉን
ላንዴ ኣውዶኝ ገላው መዓዛው
ከረውዳው ደጃፍ በደፋኝ እዛው
——————————

ስሙ ቢነገር ገድሉ ማይላላ
ልቡ የጸናው በተውሂድ ባላ
የኣንደበቱ ቃል ለጽልመት መላ
ሩሄ ባበቃች በሱናው ውላ ።

ነግሶ ዘለቀ ባዘል ተመርጦ
በኑር በጀላል ጅስሙ ታንጦ

እኔም ናፈቅኩት ገዛት ሩሄን
ለፍቅሩ ግርማ ሰዋኋት ለውሄን
ምናል በስሙ መዴን በዋጀሁ
ረውዳው ዘልቄ ኡምሬን በፈጀሁ ።

የናፍቆቱ መውጅ ነፍሴን ሸመረው
እንዴት ነው ጅስሙ በጧት ያመረው
እንዴት ነው ሩሁ የኑር ማዒዳው
እንዴት ነው ቃሉ የኣዘል መከዳው
እንዴት ነው ሁቡ ወዳጅ ማይከዳው

ቀን ሌቱን ታጥቆ የላላው ክንዱ
ጧት ማታ ናውዞ ወዝውዞት ውዱ
መንሰቅሰቅ ኾኗል ያፍቃሪ ገዱ

ይበሰከሰካል ሁቡ
ኣንጀቱን እያላወሰው
እምባው በህር ኾኖ
ሓገርሁ ጦይባ ካላደረሰው

——————————
على المعصوم صلي ياذا الطول
والانعام عد ما قيل قول
ቃሌን በመድሁ የሾምከው ጌታ
ሰላምታ ኣስፍን በጦይባው ሽታ

ኣንዴ ኣይቼው የፊት ጸዳሉን
ድምጹን ሰምቼ ያን የኑር ቃሉን
ላንዴ ኣውዶኝ ገላው መዓዛው
ከረውዳው ደጃፍ በደፋኝ እዛው
——————————

የርሱን ልቅና ሌላ ኣይቅጣጨው
ለዳዒም ሹመት ባዘል የታጨው
በቁርዓን ምሪት ተጣጥቦ ልቡ
እሱ ነው እርቁ የመዳን ባቡ
እሱ ነው ኣጥር ለጽልመት ካቡ ።

ልቤን በፍቅሩ ሰኪና ኣውርሶት
የጽልመት ጉዱን በተውሂድ ክሶት
የሒዳያ ኑር ሩሄን ኣልብሶት
የጨለማን ካብ ባፍታ የናደው
ልወደደው'ንጂ እንዴት ኣልወደው ።

ሁብሁ በልቤ ፍሙን ለኩሶ
ቀልቤ በሀሳብ ጦይባ ገስግሶ
የፍቅሩ ታጁ ነፍሴ ላይ ነግሶ
ደብዳቤ ላከ በእንባ ለውሶ
--------------

——————————
على المعصوم صلي ياذا الطول
والانعام عد ما قيل قول

የጸጋ ባለቤት የሆንከው ጌታ
ሰላምን አውርድ በዓለሙ ዓይነታ

ኣንዴ ኣይቼው የፊት ጸዳሉን
ድምጹን ሰምቼ ያን የኑር ቃሉን
ላንዴ ኣውዶኝ ገላው መዓዛው
ከረውዳው ደጃፍ በደፋኝ እዛው
——————————

ከመጾም ከመስገድ መቼ ይታገዳል
ዙህድ ነው ቀለቡ ኣዛብ ይጋርዳል
ፍቅሩ ልቤ ዘልቆ እያለዋወሰው
መዲና መሬት ላይ በሞትኩኝ እንደሰው ።

ኣንዴ ኣይቼው የፊት ጸዳሉን
ድምጹን ሰምቼ ያን የኑር ቃሉን
ላንዴ ኣውዶኝ ገላው መዓዛው
ከረውዳው ደጃፍ በደፋኝ እዛው

صلى الله عليك
ياشمس الضحى
صلى الله عليك
،، بدر الدجى
صلى الله عليك
،، يا نور الهدى
صلى الله عليك
،، مصباح الظلم
صلى الله عليك
،، سيد الكونين
صلى الله عليك
وشفيع الثقلين
صلى الله عليك
،، سيد العرب والعجم
صلى الله عليك
،، نبي الحرمين

   • Abduselam - ዓለል መዕሱም ﷺ - ዓብዱሰላም | Ale...  

Follow me
YOUTUBE    / abdslm  
INSTAGRAM   / iamabdslm  
FACEBOOK   / iamabdslm  
TELEGRAM https://t.me/abduaberam

Nashida,Nasheed,Amharic Nashida,Arabic Nasheed,Arabic Music,Arabic Songs,Ethiopian Islamic Songs,Ethiopian nashida,Awakening Covers,Abdu,abdusselam,ነሺዳ,አማርኛ ነሺዳ,ኢስላማዊ,አብዱ,አብዱሰላም,غناء,أناشيد,نشيد,نشيد إسلامي,الموسيقى الإسلامية,أناشيد إسلامية,أغاني إسلامية,تلاوة,تلاوة قرآنية,قرآن,فرقة الصحوة,ኢትዮጵያ,ሀበሻ,ፊርቃ ሳህዋ,Abduselam neshida,neshida,nasheed,Islamic nasheed,adis neshida,habesha,Ethiopia Mezamir,abdu abera,alel meesum,sudani

Комментарии

Информация по комментариям в разработке