የበገና መዝሙር ያንተ ይሁን ምርጫዬ መምህር አቤል ተስፋዬ

Описание к видео የበገና መዝሙር ያንተ ይሁን ምርጫዬ መምህር አቤል ተስፋዬ

ከኔ ሃሳብ ይልቅ ይንተ ሃሳብ ይበልጣል
ሚጠቅመኝን ነገር ካንተ ውጪ ማን ያውቃል
ስራህ ትክክል ነው አምናለው ጌታዬ
የኔ ይቅርና የአንተ ይሁን ምርጫዬ
...
ይጠቅመኛል ምለው መጥፊያዬ ይሆናል
ያለአንተ የያዝኩት ከእጄ ይበተናል
ምንም ብዘገይም ገብቶኛል ምስጢሩ
በአንተ እንጂ በራስ አይቻል መኖሩ
. .
የሰማይ አዕዋፋትን አይቼ ይደንቀኛል
የዕለት ምግባቸውን ከአንተ አግኝተዋል
ሳይዘሩ ሳያጭዱ በአንተማ ከኖሩ
ለኔ ምን ይጠቅመኛል በጭንቀት መኖሩ
.....
በማይጠቅመው ነገር ሲባዝን ይውላል
አልሳካ ሲለው ለምን ለምን ይላል
ሚሳካው በአንተ ነው እቅድና ህልሜ
በማንስ ሆነና ዛሬ ላይ መቆሜ
.....
በአንተ እየተሰጠኝ የዕለት እንጀራ
ታድያ ለምንድን ነው ልቤ እንዲ ሚፈራ
እምነት ጎሎብኝ ነው ባክህ ጨምርልኝ
በአንተ ፍቃድ እንጂ በራሴ መች ኖርኩኝ
...
መ/ሃይማኖት ብሩክ ባይለየኝ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке