#MUAZ

Описание к видео #MUAZ

#MUAZ HABIB /ባህሪ/-ሶፋ//medh መድህ #ሙዓዝ ሀቢብ //bahri_sofa// NEW ETHIOPIAN MENZUMA
⤵️⤵️⤵️➖➖⤵️⤵️➖➖⤵️⤵️
በYoutube:    / muazhabibofficial  
በFacebook:   / muazhabibofficial  
በTelegram:
t.me/MuazHabibOfficial

ከላይ በተጠቀሱት አድራሻዎች Subscribe Like እና Join በማድረግ የስራዎቼ ተከታታይ ይሁኑ!

ሙዓዝ ሐቢብ ነኝ እወዳችኋለሁ !

ባህሪ ሶፋ ግጥም ዑስታዝ ሰዒድ አህመድ ዜማ ሙዓዝ ሀቢብ ከሰይድ ሙዓዊያ ሀድራ የተወሰደ መድህ ከሸይኽ በድሩዲ መንዙማ

ግጥም


።።።።
ጦይባ ማዶ መጣ ንፋሷ
ረፍት አጣሁ ተይዤ በሷ
ከመምጣቷ ነው ከመድረሷ
መቆስቆሷ ናፍቆቴን ጭራ
።።።።

ባሳብ ሰጋር ሲጋልብ ወዳንቱ
ልጓም አልባ ሆኖ ናፍቆቱ
መሸ ሳይል ይነጋል ሌቱ
ባያይሁ ነው መንከራተቱ
ካየማ አንቱን ሞትም አይፈራ
።።።።

ዛሬ ብሶ ካምና ካቻምና
ናፍቆታችሁ እንዲ ሲጠና
መገናኘት ነውና ጤና
ልዮት እንጂ ለኔም ይምጡና
ዓይነል ሙና ታጁል ኩበራ
።።።።

ተባብሶ ሸውቁ ሲይዘኝ
የፍቅር ህመም ሲወዘውዘኝ
ሩህ አካሌን ሲመዘምዘኝ
ሲያናውዘኝ ሲያጥመዘምዘኝ
እንዲያግዘኝ ስምኩን ልጣራ
።።።።።

ያይኔ ስስት ሰይድ አህመዱ
ካቅም በላይ ሆኖ መውደዱ
ትንሽ ትልቅ ሴት በለው ወንዱ
መች ሊወርዱ ከፍቅር ጎራ
።።።

ግጥም ዜማ የማያዘልቀው
ሰርፆ ውስጤን ያጠራቀቀው
ይፋ ወቶ ሰው የማያውቀው
ስሜት አለ ልብ የደበቀው
እንዲህ ተብሎ የማይወራ
።።።።።

እሱ እኮ ነው ማረፊያ ያይኔ
ለሱ እኮ ነው ሌሊትም ቀኔ
በሱ እኮ ነው የኔ ማመኔ
ስለርሱ ነው ምፅፍ ማወራ
።።።

ይገርመኛል የፍቅር ነገር
አፍቃሪውን እንደ ማሻገር
እዬራራ እንደ መሆን ገር
ምን ይሉታል ወዳጅ ማስቸገር
ምን ይባላል ከቶ እንዲ መግረር
ወዳጅ ሆዬ ቀረ ሸውቅ አገር
ለማን ይንገር የፍቅርን ስራ
።።።

ቢፈነቅል ቢክብ ቢያፈርስም
በወዳጅ ላይ ሃዘን ቢያደርስም
ዳኛ ዘንዳ አይከሰስም
ዳኛ እሱ ነው ምንም ቢሰራ
።።።።።

ለሩህ ገላ ጤና ባይሰጥም
እያስራበ ቢገልም በጥም
ተዳፋኙን ቁስል ቢገልጥም
እጅ አልሰጥም ያሻውን ይስራ
።።።።።።

ጨረቃ አልፎ በልጦ ንጋቱን
የሚያበራ በሻሻ ፊቱን
ፈገግ ሲል እንደው ድንገቱን
ባዬው ጥርሱን ካሮ ፍንጭቱን
ወይ ብሰማ ለዛ አንደበቱን
ከሊማቱን አፉ ሲያወራ
።።።

ካልመጡልኝ ወይ ካላሉኝ ና
ናፍቆት ደፍቶኝ እንዴት ልቃና
ያይኔ ስስት የቀልቤ ሙና
አንቱን ሳላይ መች አለኝ ጤና
።።።

ካይኔ ርቀው የሩህ መውደዴ
ድንገት ደርሶ ይባባል ሆዴ
ሳስቶ አንጀቴ ላልቶ ጀሰዴ
ሰበበኛ አርጎኝል ባንዴ
ኑልኝ ውዴ ሰምተሁ ስጣራ
።።

ሙዘሚሉን የኔን ሙስጦፋ
የትከሻው መሃሉን ስርፋ
እስካላዬሁ ያይኔን ማረፊያ
ህመም በርቶ አፊያ እየጠፋ
እንዳላዝን እንዳልከፋ
ስጡኝ ተስፋ ዘይኔዋ አደራ
።።።።።

።።።።።
።።።።።።።

የውነት ወዳጅ ለሱ ተመርጠው
ከልጅ ወላጅ እሱን አብልጠው
ማ ይ ደ ራ ደ ሩ እሱን መርጠው
እንግለጠው የነሱን ሲራ
።።።።።

የልጅየው ወቶ መቅረቱ
አሳስቦት ወላጅ አባቱ
በፍለጋ ተንከራተቱ
ገደል ሜዳ ዘልቆ ተራራ
።።።።

እንቅልፋ አቶ ሃዘን ሲወርሰው
እንባው ፈሶ ጅስሙን ሲያርሰው
ኑሮ መሮ ሲያልፈሰፍሰው
ልጁ እንዳለ ወሬ ደረሰው
ሙሀመድ ሚባል ሰው ጋራ
።።።

አቆራርጦ በዱር በሜዳ
ቶሎ ቢደርስ ጧት በማለዳ
ምንድን ልርዳህ ቢሉት አህመዳ
ዘይድ ልጄ ብሎ ተጣራ
።።።።

ዘይድ ልጄ ነውና አንቱ ጋ
ስጡኝ ልውሰድ ከፍዬ ዋጋ
ቃሉን ሰምተው ዓዲሉ ሸጋ
አባሸሩት እንዲረጋጋ
።።።።

ፊት ቀረበ ዘይድ ተጠራ
አዛኙ ሰው ያ ኸይረል ወራ
ካባትህ ጋ ወይ ከኔ ጋራ
ምረጥ አንተ ምንም ሳትፈራ
።።

ዘይድም እንባ እየፈሰሰው
እንዲህ ነበር ሲል የመለሰው
አባት ይሁን ማንኛውም ሰው
መች አለና ካንቱ ማደርሰው
ምርጫ አይቀርብም ካንቱማ ጎራ
።።።።

ያየችውን አይታለች ዘይኔ
እንኳን ዛሬ በድሜ ዘመኔ
ካንቱ በቀር አልመርጥም እኔ
አንቱ እያሉ ሌላው ለምኔ
አባት እናት ሁሉም ኖት ለኔ
ብሎ አወራ እንባ እየዘራ
።።።

በልጅ ምላሽ ተገርሞ አባቱ
ምንድን ይበል ጠፋው ቃላቱ
ሁሉን በልጦ ከሁሉ ነግሶ
የሚፈቀር የለም እንደርሶ

።።።።።
ከቀን በቀን ብሶ እየጋለ
ዘይድ ፍቅሩ ስለሃዬለ
ሂቡ ረሱሊላህ ተባለ
ነቢን ያለ ፋዘ ቢል ቡሽራ
።።።

።።።።።
።።።

የሲዲቅ ልጅ አብዱረህማኔ
ያመነ ለት በነቢ ዘይኔ

በድር ሜዳ ስወጣ ያኔ
አንቱን ከሩቅ አይቼ ባይኔ
መግደል ሳስብ ጠፋብኝ ወኔ
ውድ አባቴ ነሁና ለኔ
ተውኩኝ እኔ ልቤ እየፈራ
።።።።

አቡበክር አይነታው ገበር
እንዲህ ሲሉ መልሰው ነበር
እንደው አይኔ አይቶህ በነበር
መች እንዳንተ እተውህ ነበር

ሚመጣብኝ በልብ ወዳጄ
ጠላቴ ነው ቢሆንም ልጄ
ምከተለው በሄደው ሄጄ
መች እንደሱ ሰውን ወድጄ
የኔን ምላሽ ሰማህ ወይ ልጄ
ማመንህ ነው ያዳነህ ከጄ
።።።።።።።

ሰላት ሰላም ይውረድባቹ
የኔ ነቢ የምወዳቹ
በአስሀባ በቤተሰባቹ
በናታችሁ በአባታቹ
በሰባቱም በልጆቻቹ
በምትወዱት በሚወዳቹ
ሰላምታዬን ያው ላኩላቹ
አንቡብልኝ እስኪ ባካቹ
ጌታዬዋ አደራ አደራ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке