ሁሉን ሰው ለማስደሰት አትታገሉ || Dr. Eyob Mamo || በዶ/ር ኢዮብ ማሞ || "ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ከፈለጋችሁ ..."

Описание к видео ሁሉን ሰው ለማስደሰት አትታገሉ || Dr. Eyob Mamo || በዶ/ር ኢዮብ ማሞ || "ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ከፈለጋችሁ ..."

ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ትታገላለህ?
ራስህን መዝነው
1. ሌሎች ሰዎች ስለተሰማቸው ስሜት አንተ ሃላፊነት ይሰማሃል?
2. አንድ ሰው በአንተ ላይ እንደተበሳጨ ወይም እንዳዘነ ስታውቅ ከልክ ባለፈ ሁኔታ በስሜትህ ላይ ጫና ያስከትልብሃል?
3. ሰዎች እንደፈለጉ ወዲህና ወዲያ የሚያደርጉህ አይነት ሰው እንደሆንክ ይሰማሃል?
4. በአንድ ጉዳይ ላይ ከሌሎች ሰዎች ተቃራኒ ሃሳብ እያለህ እንኳን ተቀባይነት አጣለሁ በሚል ሰበብ ያንን ሃሳብህን ከመናገር ይልቅ መተባበር ይቀልሃል?
5. ብዙ ጊዜ ግልጽ የሆነ ጥፋት እንዳልሰራህ እያወከው እንኳን ይቅርታ የመጠየቅ ዝንባሌ አለህ?
6. አለመግባባት እንዳይፈጠር ለማድረግ ከአቅምህ በላይ ስትታገል ራስህን ታገኘዋለህ?
7. ሰዎች ስሜትህን ሲጎዱት ስለሁኔታው ለሰዎቹ በግልጽ ማውራት ይከብድሃል?
8. ሰዎች አንድን ነገር እንድታደርግላቸው ሲጠይቁህ ማድረግ ባትፈልግም እንኳን ካለብህ የመገደድ ስሜት የተነሳ እሺ የማለት ዝንባሌ አለህ?
9. ሌሎች ሰዎች የሚፈልጉትን ነገር ስታይ ከዚያ በመነሳት እነሱን ለማስደሰት ስትል ሁኔታህን፣ ተግባርህንና ባህሪህን ትለዋውጣለህ?
10. ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸው አመለካከት ጥሩ እንዲሆን ብዙ ስትሯሯጥ ራስህን ታገኘዋለህ?
ከላይ ለተጠየቁት አስር ጥያቄዎች ከግማሽ በላይ ለሆኑት “አዎ” የሚል መልስ ከሰጠህ በዚህ ምእራፍ ለተጠቀሱት ነጥቦች አስፈላጊ ትኩረት በመስጠት ለውጥን ለማስተናገድ ጥረት አድርግ፡፡

መንስኤው
አለመግባባትን ፍርሃት
የአስተዳደግ ሁኔታ
ቅድመ-ልምምድ

መዘዙ
የዋጋ ተመንን ማውረድ
በሰዎች መጎዳት
የውስጥ መራቆት

መፍትሄው
ራስህን አደላድል
ሰዎችንለይተህ እወቅ
ገደብህን አስምር



#selfimprovement #selfawareness #happiness

Комментарии

Информация по комментариям в разработке