Chicken Soup የዶሮ ሾርባ

Описание к видео Chicken Soup የዶሮ ሾርባ

የዶሮ ሾርባ

የዶሮ ሾርባውን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እና የማጣፈጫ ቅመሞች አይነት እንዲሁም መጠን
ዶሮውን ለመቀመም
2 በቀጭኑ ስላሽ የተከተፈ የዶሮ መላላጫ
በቡና ማንኪያ ልኬት ግማሽ ፡
ጨው ፣ ቀረፋ ፣ ጥቁር ቁንዶ በርበሬ ፣ ሮዝሜሪ ፣ ፓፕሪካ እና የነጭ ሽንኩርት ዱቄት
4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
ዶሮው ላይ ቅመሞቹን ከጨመራችሁ በሃላ በሚገባ በማንኪያ እንዲሁም እጃችሁ በደንብ ማሸት፤ የበለጠ ጣፋጭ እንዲሆን ከፈለጋችሁ በክዳን ከድናችሁ ከ 3-6 ሰዓት ማቀዝቀዣ ውስጥ ማቆየት ትችላላችሁ

ዶሮውን ለመጥበስ ፡
1 ሾርባ ማንኪያ የገበታ ቂቤ
ግማሽ የሾርባ ማንኪያ ዘይት
ዶሮውን በሁለቱም በኩል ወርቃማ ይዘት እስኪይዝ ድረስ በደንብ መጥበስ
በአንደ በኩል ከ3-4 ደቂቃ በከፍተኛ ሙቀት መጥበስ ገልብጦ ከ2-3 ደቂቃ ድረስ መጥበስ፤ ነገር ግን ይህ ልኬት እንደምድዳጃችሁ አይነት ይወሰናል

የአትክልት ግብዓቶች
እዛው ዶሮ የጠበስንበት ድስት ላይ
2 ራስ ደቆ የተከተፈ ቀይ ሽንኩርት
1 ባሮ ሽንኩርት እና
5 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
ጨምሮ አትክልቱን መጥበስ፤ቅባት ካነሰው ትንሽ ዘይት ወይም የገበታ ቂቤ ጠብ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡የአትክልት ግብዓቶቹ በድንብ ከተጠበሱ በሃላ
1 የሾርባ ማንኪያ የፉርኖ ዱቄት መጨመር እና በደንብ ከአትክልቱ ጋር ማሸት
2 የሾርባ ማንኪያ የቲማቲም ድልህ መጨመር
1 ብርጭቆ ወተት ጨምሮ ማቀላቀል ፤ ከወተት በተጨማሪ ክሬም መጠቀም ትችላላችሁ
ወተቱን ጨምራችሁ መንተክተክ ሲጀምር
1 የዶሮ መረቅ 1 ብርጭዎ ውሃ በጥብጣችሁ መጨመር
የዶሮ መረቅ ከሌላችሁ ጨው መጠቀም ትችላላችሁ
ዶሮውን ቀምማችሁ ያስተረፋችሁትን ቅመም አሁን ትጨምራላችሁ
2 ተልጦ ታችቦ የተከተፈ ድንች
ያዘጋጃችሁትን ዶሮ በሹካ በደንብ ሸርክታችሁ ማስገባት
ትንሽ ጨው ቀምሳችሁ መጨመር
እንደ ምርጫችሁ የምትፈልጉትን ያህል ቺዝ መጨር (ሞዞሬላ/ፕሮቮሎኔ)

Комментарии

Информация по комментариям в разработке