የበገና መዝሙር “በከመ ምህረትከ” ዲ/ን አቤል ተስፋዬ

Описание к видео የበገና መዝሙር “በከመ ምህረትከ” ዲ/ን አቤል ተስፋዬ

በከመ ምህረትከ ወአኮ በከመ አበሳነ
አምላካችን ሆይ እንደቸርነትህ ነው እንጂ
እንደ በደላችን አይሁን
.....
ከአስሩ አንዱ ድንገት ቢጠፋባት
ድሪሟን ፍለጋ ሴቲቱ ተነሳች
ቤቷን ስታጸዳ አብርታ መብራቷን
ከቆሻሻ መሀል አየችው ድሪሟን
ያድሪም እኔ ነኝ በቃልህ ማልገኝ
በቤትህ ውስጥ ሆኜ በቤትህ ማታውቀኝ
ከቆሻሻ መሀል ከምታገኛቸው
አገልጋዮች መሀል እኔ ነኝ ዋነኛው
.....
የሰበከውን ቃል በህይወቱ ነዋሪ
የጠፋው እርሱ ነው ሞልቷል ተናጋሪ
በክፋ ስራዬ በኔ ተነቅፈሃል
የስም ብቻ አገልጋይ መች ያስደስትሃል
ቅርብ ነው አንደበቴ ልቤ ግን የሸሸ
ማንነቴ ባዶ በቃልህ ያልታሸ
ዛሬ አስተካክለኝ ልታነጽ በቃልህ
በኔ አይሰደቡ ቅን አገልጋዮችህ
....
አገሪቱ ረስታ መጎብኘቷን ወራት
እንባህን አፍስሰህ ለሷ አለቀስክላት
ዛሬ ብትመጣ በልቤ ከተማ
አዝነህ ታለቅሳለህ በኔ ምግባርማ
በመቅደስህ መሃል ድፍረቴ የበዛ
ልቤ ለዓለም እንጂ ላንተ ያልተገዛ
የስም ብቻ አገልጋይ መሆኔን ታውቃለህ
ድሮስ ከኔ አይነቱ ምንስ ታገኛለህ
.....
የቃየል መስዋዕት ከመቅደስህ ገብቶ
አንድነት ተረስቶ ሁሉ ተለያይቶ
እንክርዳዱን መስዋዕት ቁራ በትኖታል
ፍቅር አልባ መስዋዕት መች ያስደስትሃል
ይቁም በመቅደስህ መሸጥ መለወጡ
አፍኒንና ፍንሃስ ከመቅደስህ ይውጡ
ሳሙኤልን መሰል ቅን አገልጋዮችህ
በመቅደስህ ይብዙ ተናገር ይበሉህ
.... አዲስ የበገና ዝማሬ ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ አላማዉን ይደግፉ አመሰግናለሁ

Комментарии

Информация по комментариям в разработке