አሚር ሁሴን//ሩኸል ከዉኒ// አዲስ መንዙማ 2016//AMIR HUSSEN//RUHEL KEWNI NEW MENZUMA2024

Описание к видео አሚር ሁሴን//ሩኸል ከዉኒ// አዲስ መንዙማ 2016//AMIR HUSSEN//RUHEL KEWNI NEW MENZUMA2024

ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️ 
@alfarukmultimediaproduction
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️ 
      @AMIRHUSSEN-official
ሰብስክራይብ ያርጉ 👇⬇️ 
    @SelehadinHussen-official   



ማዲህ
👉🏻አሚር ሁሴን

ግጥም
👉🏻አብዱል ማሊክ ላሊ(ጎራዉ)

ዜማ
👉🏻የጅማ ሀድራ

ተጨማሪ ዜማ
👉🏻አሚር ሁሴን

ሲኒማቶግራፍር እና ካሜራ
👉🏻ሰዒድ ሙሀመድ

ረዳት ካሜራ
👉🏻ሀምዱ አወል እና ሙሀመድ

መንዙማ ቅንብር እና አሬንጅመንት
👉🏻ኑሩ ዑመር (ቦርከና ስቱዲዬ)

ሚክስ እና ማስተሪንግ
👉🏻ሰለሞን በላይ ( ሀመር)

ኤዲቲንግ እና ከለር
👉🏻አሊ ሙሀመድ (አሊፍ)

ሞሽንግራፊክስ
👉🏻አሊ ሙሀመድ (አሊፍ)

ፕሮዲውሰር
👉🏻አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን
ፕሮዳክሽን

ማኔጀር ፋሩቅ ጋሊብ
አሰላም ዐለይኩም ያቁረተል ዐይኒ

አበል ቃሲም ዘይኔ
❤ሳደቲ❤ሩኸል ከዉኒ

ቢስሚላሂ ብዬ
ላመላልሰዉ ስሙን
የዐለም ኢማሙን
የቀመሠ ያዉቀዋል * ጥፍጥናና ጣሙን
መሐመድ አሚኑን ❤ ተናፋቂዊን ዘይኔ

ቁርዐን ነበረ
ምግባሩም ሀለቱ
ደሞም የእዝነቱ
ሀሉ ተመሳሳይ ለዉጭም ከቤቱ
አለች አይሸቱ ❤ወስፉን ስትገልፀዉ ያኔ

❤❤❤❤

አይሻ ሆይ አሏት ዘይኔ * ሩኸል ከወኒ
በሩጫ ካንቺና ከኔ
ብንሮጥ ብንወዳደር
ማንይቀድማል በፉክክር

መርሀባ ብላ በፍቅር
አይሻም አለች እንጀምር
ሮጣ አብራ በዉጤቱ
ተቀደመች አይሸቱ

በሌላኛዉ ግዜ አዉቀዉ ቀስ አሉላት❤❤
   ሮጣ ቀደመች አይሻም ደስ አላት

❤❤❤ ❤❤

ላወድሶ እንጂ
እያልኩኝል ጃማሌ
ወርቃማዉ እድሌ
አንቱን ነዉ ዉዴዋ እኔ መከጀሌ
ዛሬም ነገም ሁሌ ❤ናፍቆቴ ሠመመኔ

ዋስሁነኝ አለችዉ
ተጨንቃ ሚዳቆ
ግንዱም አሱን ናፍቆ
አትለዩኝ አለ # በእንባ ተንፈቅፍቆ
ደረጃዎን አዉቆ ❤ መቃምሆን ዘይኔ

❤❤❤

ትመስክር ያቺ ወፊቷ * ሩኸል ከወኒ
ከጎጆዋ ርቅ ላፍታ
ብትመለስ ወደ ቤቷ
ተወስደዋል ጫጩቶቿ

ጫጩቶቿን በማጣቷ * ሩኸል ከወኒ
ወደ ዐለማቱ ዐይነታ
ሄዳ ወዳሉበት ቦታ
ለነቢ አወጋች ስሞታ

ልጆቼ ተወስደዉ አጥቻለዉ መላ
አንቱ አስመልሱልኝ አለች ረሡለላ

❤❤❤❤

❤ በጀማል ኑር ነዉ ያስጌጠዉ * ሩኸል ከወኒ
ላዩ ዉስጡን ያልበለጠዉ
ዙፋን አልባ ንጉስ መሪ
ምስጉን ባሪያ ነዉ ታታሪ

በልቅናዉ ያልዘነጠዉ * ሩኸል ከወኒ
እዝነቱ ማይቋረጠዉ
ደግ ሹም ነዉ የማያዳላ
አስታራቂ ነዉ ከመዉላ

የራህመቶች ራህመት ነዉ የእዝነት እራስ
እንኳን ለሰዉ ቀርቶ ለአዉሬ የሚዋስ


❤❤❤❤✍️#
ሠላም ዐለይኩም ያዘይኔ
ሐያተል ዐለም ሸምሰል ከዉኒ

አበልሐሠኑ
አህመዱ ዑመር
የራህመቱ በር
ለነፍሴ ፀሀይ ኖት ጀምበር
አልፋኮ ሰላሜም አማኔ

የልብ ምቴም
ስሞ ሙሐመድ
ስመሄድ ስራመድ
ልቤ ካንቱ ሌላ አይለምድ
ናፍቆቴ አንቱ ኖት ሰመመኔ

ፍቅር ነዉ ራሡ
መዉደድ ነዉ ራሱ
ሲፋዉ ልስልሱ
ጀማሉ ሀይባዉ ሞገሱ
ትዉስ እያለኝ ጠና ሀዘኔ

ዉበተ ብርሀን ❤❤❤❤
   ስብናዉ መልካም
     ልበሎ ሰላም
  እያደር ሚናፈቅ በጣም
   በህልምም ቢሆን ደሞ በዉኔ

ማማር ዉበቱ
ማርኮኝ ሲፈቱ
ማርኮኝ ሀለቱ
ምንስ ቃል ይገልፃል አንቱን
ቃል አጥቻለዉ ላንቱ እኔ

ወዙ ሚሸተዉ
ከሚስክም አንበር
ጉድ አጂብ ነበር
ምቹ ነዉ ሲፋዉ ገራገር
ከቶ ማን አለ እንደ ዘይኔ

ቢገጠም ግጥም
ቢዜም በዜማ
ለአበልፋጢማ
ናፍቆቱ ልብ የሚያደማ
ሁሉም ሰዉ ሚለዉ የኔ የኔ

የዐይኔ ዉበቴ
ኖት መስታወቴ
ክብሬ ኩራቴ
የነፍሴ ረሀብ ስስቴ
ማያዬ አንቱ ኖት ብሌን ለዐይኔ

  መዉደዴን ፍቅሬን❤❤❤❤
      ገልፆ ለማዉራት
       በአንደበት ቃላት
    ያጥረኛል  ሰባቱም ቀናት
    ያሳጣል ብርታት አቅም ወኔ



ይህን ቪድዮ ያለ ፍቃድ ሌላ ቦታ ላይ መልቀቅ የተከለከለ ነው!
Unauthorized distribution and re-upload of this content is strictly prohibited

Copyright © 2024 @alfarukmultimediaproduction

Комментарии

Информация по комментариям в разработке